“የክርስቲያን አገር በሆነችው ሙስሊሞች ሊነግሡባት ነው” ህወሓት ለአሜሪካ እንደራሴዎች

 • የአስራ ሰባት ታዋቂ ኦሮሞ ሙስሊሞችን ስም ለማስረጃነት አቅርቧል
 • ከዝርዝሩ ውስጥ የዶ/ር አቢይ አህመድ ስም ይገኝበታል

ህወሓት ከፊቱ የተጋረጠበትን የፖለቲካ ቀውስና ቀውሱን ተከትሎ ከጌቶቹ የተነሳበትን ተቃውሞና ግፊት አቅጣጫ ለማስቀየር ሃይማኖትን የተንተራሰ ስልት ተግባራዊ ማድረጉ ተሰማ። የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ አገሪቱን ለእስልምና አክራሪ አሳልፎ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ህወሓት በወኪሉ በኩል ስም ዘርዝሮ አቅርቧል።

የጎልጉል ዲፕሎማት የመረጃ አቀባዮች ከዋሽንግቶን ዲሲ እንዳስታወቁት ህወሓት አሁን የተነሳበትን ዙሪያ ገጠም ተቃውሞ ከእስልምና አክራሪነት ጋር በማቆራኘት የአስራ ሰባት ኦሮሞ ሙስሊም ታዋቂ ፖለቲከኞችን፣ የመብት ተሟጋቾችን፣ ወዘተ ስም ዘርዝሮ ነው ያቀረበው።

ዙሪያው ገደል የሆነበት ህወሓት የስም ዝርዝሩን ባቀረበ ጊዜ ራሱን የክርስቲያን መንግሥት አድርጎ ለማሳየት ሞክሯል። ይህቺ አገር የክርስቲያን ደሴት ነች፤ እስካሁን ኢትዮጵያን ከመሩት ሁሉ ለሃይማኖት ነጻነት የሰጠነው እኛ ነን፤ የክርስትና እምነታችንን በመጠበቅም ከሆነ እንደ እኛ እስካሁን በትጋት የሠራ የለም፤ ሙስሊሞች ይህችን የክርስቲያን አገር ሊቆጣጠሯት ቆርጠው ተነስተዋል፤ ይህ ካልተገታ አገሪቱ ትበታተናለች – ሃይማኖቱም ያከትምለታል የሚሉ አቅጣጫ የማስቀየሪያ ማስፈራሪዎችን የሎቢ (ውስወሳ) ሥራ በሚያከናውንለት ድርጅት አማካኝነት ህወሓት አቅርቧል።

እነዚህን በአገር ውስጥና በውጪ የሚገኙ ታዋቂ ኦሮሞ ሙስሊሞችን ስም በመዘርዘር፤ የማምለጫ ሰነድ በማዘጋጀት፤ በቀጠራቸው ሎቢስቶች አማካይነት የውስወሳ ሥራ የጀመረው ህወሓት ጉዳዩ በጣት በሚቆጠሩ እንደራሴዎች (የኮንግሬስ አባላት) ዘንድ ይሁንታ እንዳገኘለት የመረጃ ምንጮቹ አመልክተዋል። ህወሓት የፕሮፓጋንዳ ዒላማውን ያነጣጠረው ወግአጥባቂ በሆኑ፣ በኢትዮጵያ ለዘመናት ሙስሊምና ክርስቲያን እንዴት በሰላምና ፍቅር እንደኖሩ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ በሌላቸው እንደራሴዎች ላይ መሆኑን የጎልጉል መረጃ አቀባዮች አረጋግጠዋል።  በግምባር ቀደምትነትም የህወሓት ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ ኢትዮጵያ ድረስ እስኪሄዱ ያደረሰ የውትወታ መካሄዱ የሚታወስ ነው።

እነዚሁ ክፍሎች እንዳሉት ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ተስፋ የተጣለባቸውና የክርስትና (የፕሮቴስታንት) እምነት ተከታይ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቢይ አህመድም (ዶ/ር) በስማቸው ብቻ ሙስሊም ከሆኑ ታዋቂ ኦሮሞዎች ጋር በመቆራኘታቸው ለኃላፊነት እንደማይበቁ ከአስራ ሰባቱ ስም ዝርዝር ጋር ተካትተው ቀርበዋል።

የዋልድባን ገዳም ከማፍረስ ጀምሮ መንኩሴዎችን፣ የጸሎት ሰዎችን፣ የእምነት መሪዎችንና ህዝብ የሚያከብራቸውን የእምነት እሴቶች እያወደመ ያለው ህወሃት፣ አሁን ለክርስትና ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረቡ ያስገረማቸው፣ “አሁን የተመዘዘው የነፍስ አድን ካርድ ነገሮችን እጅግ ሊያወሳስብ ይችላል። አርፈው የተቀመጡና በዜግነታቸው ብቻ ለውጥ የሚጠይቁትን የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደማይሆን መንገድ እንዳይገፋቸው እንፈራለን” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከዚህ አኳያ ትግሉን እየመሩ ያሉ ይህንን የህወሓት መሠሪ አስተሳሰብ አስቀድመው ተረድተው አንድነት፣ ኅብረት፣ አብሮነት፣ መደመር ላይ አበክረው እንዲሠሩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ከማግኒትስኪ ሕግ ጋር ተጋብቶ የቀረበው HR 128 በሕዝብ ላይ አስከፊ ግፍ ሲፈጽሙ የነበሩትንና በጠራራ ፀሐይ ሕዝብን ሲዘርፉ የኖሩትን የህወሓት ሹሞችና ቤተሰቦች መግቢያ ያሳጣ ሆኗል። ይህ ረቂቅ ሕግ በአዋጅ እንዳይወጣ ሲከላከል የነበረው ህወሓት፤ በቅርቡ በወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” አማካኝነት አልሸባብን ማስፈራሪ አድርጎ ለአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ማቅረቡ ይታወሳል። እኛ ሥልጣኑን ካልቀጠልን አልሸባብ መላውን የአፍሪካ ቀንድ ባጭር ጊዜ ውስጥ ይቆጣጠራል በማለት በመለስ ስልት ለመጫወት ያቀደው ሳይሳካለት ወደመጣበት መመለሱ የሚታወስ ነው።

በቅርቡ ለውይይትና ለድምፅ ይቀርባል የተባለውን HR 128 የህግ ረቂቅ ለማምለጥ ሁሉንም ዓይነት ካርድ ሲስብ የኖረው ህወሃት፣ ስልታዊ መፈንቅለ መንግስት ካካሄደ በኋላ በአስቸኳይ አዋጅ ስም ከውስጥ በጥይት፣ አፈናና የጅምላ እስር፤ ከውጭ በፍረጃ ለማምለጥ በወስዋሾቹ አማካይነት ድጋፍ እያሰባብሰበ መሆኑን ጎልጉል ከሌሎች ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ክፍሎች አረጋግጧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በቡድን ለማ ሥር የአቢይ አህመድ ለጠ/ሚ/ር ሥልጣን ይበቃል የሚለው አስተሳሰብ እያየለ በመምጣቱ በተለይ በአገር ውስጥ በህወሓት በጀት በሚቆረጥላቸው ደጋፊ የማኅበራዊ ገጽ ሚሊሺያዎችና ካድሬዎች የአቢይን ስም የማጥፋት ዘመቻ መክፈታቸው ከሰሞኑ እንቅስቃሴያቸው ለመረዳት ይቻላል።

ህወሓት እገዛዋለሁ የሚለው ሕዝብ ከከዳው በኋላ ባለቀ ሰዓት የከፈተው ይህ አጀንዳ እንደጠበቀው የበርካታ እንደራሴዎችን አመኔታ አላገኘም። በተለይ ከ“ድምጻችን ይሰማ” የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጀምሮ የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ ነባር እንደራሴዎች፤ ጥያቄያቸውን በሰለጠነና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሲቀርቡ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ የህወሓት ታጣቂዎች የፈጸሙትን ኢሰብዓዊ ግፍ በማስታወስ ይህንን የህወሓት ማምታቻ ከመስማት ባለፈ ለመደገፍ የማይቻልና በቂ ማስረጃ ያልቀረበበት መላምት አድርገው በመውሰድ ይበልጡኑ በHR 128 ላይ እየሠሩ መሆናቸውን ጎልጉል ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Comments

 1. የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ! ቂ ቂ ቂ
  የትግሬው ወያኔ እስካሁን ሲጫወትበት የነበረው የመጨረሻው ካርድ፡”እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች፣ አብሮ መኖራችን ለግድያ ካበቃን ትግሬን እንገነጥላላን” ብለው ባለቀ ሰዓት በትግሬው ወያኔ ጋዘጠኛ ከመቀሌ በዳዊት ከበደ አጋፋሪነት፤ በዉጭ ደግሞ ደደቢቶች ባሠለጠኗቸው የትግረወ ወያኔ Facebook ሮች ሲያስተጋቡ፡ አብዛኛው ህዝብ እፉፉፉ ጥርግ በሎ ብቻ አገራችንን ኢትዮጵያንና ህዝቦችን ለቀቅ አድርጉልን አሏቸው። ከህዝቡ ይሄንን ሲሰሙ “ዘይትና ዉሃ ወይም እሳትና ጭድ ” እንዴት አንድ ላይ ሊቆሙ ቻሉ ብሎ የፎክረው ፌንጣ እና የትግረው ወያኔ ነገረ ፈጅ ጌታቸው ረዳ «እረ እኛ ምን በወጣን ፤ ከኢትዮጵያስ ተግንጥለን ምንስ ልንበላ፡…..?» የዘረፍነውነና በትግራይ ጎተራዎች የሞላናቸዉን እህሎች ለመብላት እኮ ኢትዮጵያ ታስፈልገናለች ፤ ያለ ኢትዮጵያማ ምን ልንበላ ኤርትራን ያዬ ተቀጣ እንዲሉ ብሎ “አንገነጠልም ” ብሎ ማስተባባዬ መሰል ነገር በ EBC ሲሰጥ አዬነው። ወይ መጨነቅ!
  አንችው ታመጭው አንቸው ታሮጭው አለ ጎይቶም ቂ ቂ ቂ ቂ

  • ስለ ሻዕቢያ የተባለ አንድም ቃል ሳይኖር ምነው ስለ ሻዕቢያ ይህን ያህል አቶ «ሙሉጌታ አንዳርጌ»?

 2. ሰዎች!! ግመል በጣም በጣም በጣም ብልጥ እንስሳ ናት!!! ሻብያ ኣሰልጥኖ ለብዙ ክፋት ነገሮች ይጠቀምባቸዋል። ለምሳሌ፤ እንደ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ማጓጓዝ፣ እንደ ትጥቅ መሳሪያዎችን በተፈለገው ቦታ ማድረስ፣ ያውም በኣንድ ሰው ብቻ በመመራት ይከናወን ነበር። ይህን በዓይኔ ኣይቼ፣ ታዝቤ፣ ግመል ምን ያህል ቅን፣ ታዛዥ፣ ብርቱና ቀልጣፋ እንሰሳ እንደሆነች ተመልክቻለሁ። ኢትዮጵያውያን ኣፋሮች፣ ስለ እኛ ኢትዮጵያዊነት፣ ግመሎቻችንም ሳይቀሩ፣ ባንዲራዋን ጭምር ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ የሚል ኣባባል ኣላቸው። ቂቂቂቂ!!! እኛ የምናወራው፣ ስለ ዕኩልነት፣ ሻቢያና ኣቀንቃኞቿ የሚያወሩት፣ ስለግመሎቻቸው ሆነ!!! ገና ለገና ግመል ኣገልጋይ ነውና፣ የባቡር ሃዲዱን ሰልጥኖ ሲዘጋብን እያየን እንለፍ??? ቂቂቂቂ!! ኣፋሮች እኮ ብዙ ግመሎች ኣሏቸው!! እስላሞችም ናቸው። ባንዲራዋን ለብሰው፣ ሃዲዱ ላይ እንዲወዘቱ መፍቀድ ተገቢ ነው??? ወያኔ ኣንድም ቀን፣ ስለ ዕምነት ልዩነት ሰብካ ኣታውቅም!! ባይሆን ግመሎች እያወኩን ነው። እነሱም እስልምናን ተሰብከው ይሆን??? መቼም ክርስትናውን ማርቆስ ሰው ልኮልን ይሆናል!!! ቂቂቂቂ!!! ይህቺ በግ ከታረደች፣ ኣትበቃንም። ይልቅ ግመሏን እንረዳት!!

 3. TPLF is using this analysis to win the war on diplomacy by blaming OPDO.
  They have put one article infront of their diplomacy page an on top unusual.

  Some people say though anti TPLF, Mikael works with CIA or some EU intelligence or some organization They are using his analysis , which because it’s coming from opponent, makes it more credible for playing a religion card in their diplomacy. TPLF is cruel.

  http://www.ethiopianforeignpolicy.com

  They changed their strategy of diplomacy after reading the analysis by Mikael Arage. It’s the only card that’s working for them at the moment. HR.128 won’t pass because US gov is convinced by now that OPDO has been hostile to Christians. Though TPLF used reglion as a weapon of division, it’s using it now to win diplomacy.

 4. ደርቤ ኣየለ - ወያኒ ገዳይ says:

  እኔ የሚያሳዝነኝ መሳቂያና መሳለቂያ ከመሆን እንዴት ውያኔ ከ5 ሚሊዮን ሕዝብ መሀል ሁለትና ሶሰት ብቃት ያላቸው ኣንቱ የሚባሉ ሰዎች ትግሬዎች ኣግኝቶ ስልጣን ላይ ማስቀመጥ ተሳነው። የተማር ትግሬ-ውያኔ ተገኘ ተብሎ ጌታቸው ረዳን ኣምጥተው ሊሸከመው ቀርቶ ሊያስበው በማይችለው ቦታ ላይ ኣስቀመጡት። ሁልዪ ንግግሩ የበቀቀን ነው። በዚያው በተብታባ ኣንደብቱ ” እንዴት እሳትና ጭድ የሆነ ህዝብ ሊስማማ ይችላል፤ ኦሮሞና ኣማራውን ማለቱ ነው፤ ይህ ማለት በቂ ስራ ኣልሰራንም” ኣለ፤ በኣደባባይ። በቂ ስራ ኣልሰራንም የሚለው በኣርሲ የቆመውን ” የኣኖሌ ሀውልት” ኣይነት በየከተማው ማቆም ነበረብን፤ እንደ ኣርባጉጉ ኣይነት ጭፍጨፋዎች በየግዜው ባኦሮሞ ስም ማረግ ነበረብን ወዘተ ማለቱ ነው።እንኩዋን ከመኣት ሊያወጣቸው ጭራሽ መቀመቅ ከተታቸው። ወያኔ፥ ኣየደለም ከሌሎች ስህተት፥ ከራሱ ስሀተት መማር የሚባል ነገር ኣያውቁም፤ጌታቸው፥ ኣሁንም የቁም-ሬሳው ቡድን ኣፈ ቀላጤ ሆኖ መጥቱዋል። የቸገረው እርጉዝ ያገባል እነዲሉ።

  ሌላው ደንባራው በቅሎ፤ ወርቅነህ ገበየሁ (በውልደቱ ትግሬ፤ በመታውቂያው ደበትሩ- ኦሮሞ)የሆነው ነው። ከሶስት ኣስር ኣመታት በፊት ከኣ.ኣበባ ዩንቨርስት የውጣ ሰው፤ ክዚያም ኣነሰም ኣደገ በውያኔ ባልስለጣንነት በተለያዩ መ/ቤቶች የሰራ ሰው የተጻፈለትን ጽሁፍ እንኩዋ በትክክል በወጉ ማንበብ ኣይችልም፤ ኣይደልም ጉዳዩን ተገንዘቦ በቃሉ ሊገልጽ ሊያስረዳ ይቅርና። ማፈሪያዎች።!! ለማረጋገጥ ከተፈለግ “ዩትዩብ” ገብቶ ጉዱን መመልከት ነው።
  በዘር ሀረጋቸው ትግሬ ሆነው ኢትዮጵያዊ ስሜት ያላቸው ጥቂት ምሁራኖች ኣሉ። ለምሳሌ ዶ/ር ሀይሉ ኣርኣያ። ውያኔ ይሞታል እንጂ እንደነዚህ ኣይነት ስዎች ወደ ስልጣን ኣያመጣም። ዛሬ ስለረፈደ እንደነዚህ ኣይነትም ስዎች ቢያመጣ ከመሞት ኣይድንም።ነቀርሳ ይዞት መታከም በማይችልበት ደርጃ ላይ ያለ ስርኣት ነውና መድህን የለውም፤ ከሞት ሌላ።!!!

  ዋናውን ርእሰ ጉዳይ በተመለከት ማለት የሚቻለው፥ ውያኔውችን የሞዕራቡ ኣለም ለ27 ኣመት እሹሩሩ ሲሉት የነበረው የሚፈጽሙትን ወንጀል ስለማያውቁ ኣልነበረም፥ ኣይደለምም። ነጮቹ እንደምናውቀው ሁልግዜ ብሄራዊ ጥቅማቸውን ስልሚያስቀድሙ ነው። ዛሬም የውያኔን ውትወታ የማይሰሙትና ነገሩን በሌላ መለኩ ለማስኬድ የፈለጉት ዛሬ ላይ ያለውን የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ ስለተገነዘቡና ከኣሁን ወዲያ ወያኔ ኣገሪቱዋን በምንም ኣይነት መልኩ ኣረጋግቶ መምራት እንደማይችል በመርዳታቸው እነሱን መደገፉ ሀገሪቱዋ እነዲህ በቀላሉ የማትወጣበት ኣዘቅት ውስጥ ልትገባ እንደምትችልና የኣሜሪካ ብሄራዊ ጥቅም እና ደህንነት ኣንደሚነካ ግምት ውስጥ በማስጋብት ይመስለኛል።
  ወያኔ ኣልተሳካለትም እንጂ በክርስቲያኑና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀከል ብዙ ግዜ ቅራኔዎችን ለመፍጠር ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። ውያኔዎች ያልተረዱት ወይም ሊረዱት ያልፈልጉት ነገር ኢትዮጵያውያን ከነሱ በኣስተሳሰብ እጅግ በጣም ቀድመው የሄዱና የራቁ መሆናቸው ነው። ነገር ግን ሌላ በቅጡ የተረዱት፥ የተገነዘቡትና የሚያውቁት ነገር ኣለ። ይህውም፦

  ሀ) የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማያከበራቸው፤
  ለ) እንደማይወዳቸው፤
  ሐ) እንደማይፈራቸው፥እነደሚንቃቸው እና እንደሚጠየፋቸው።

  የሄ በጣም ሊድን የማይችል ሀኪም የሌለው ስነልቡናዊ ችግር ፈጥሮባቸው ይገኛሉ። በዚህ ኣለም ላይ ከነገሩ ሁሉ ቀላል ምክር መምከር ነው። ልመክራቸው ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ለማይሰማ ሰው መምከር “ድንጋይ ላይ ውሀ ማፍሰስ ነው” ይላልና ያገሬ ሰው “ስራችሁ ያውጣችሁ” ብያቸዋለሁ።
  ትግሉ ይቀጥላል!!! ወያኔን እሽሩሩ ማለት የለም፤ ቀብረን በመቃብራቸው ላይ እንዳይነሱ ድጅኖ እንቀረቅርበታልን። ሰላም ሁኑ!!!

 5. ለወስላቶች ፈዋሽ መድሃኒት ተገኝቶ አያውቅም። ሞት ግን ሁሉን እኩል የሚያረግ የተፈጥሮ ህግ ነው። ለዛም ነው መሰል የሩሲያው አባባብል “ሙሉ መስማማት ያለው መቃብር ሥፍራ ነው” የሚለው። ወያኔ አማራና የኦርቶዶክስ እምነትን ካጠፋን ለመቶ ዓመት እንደሚገዛ አምኖ ሚዛን ባጣ ግፍ ህዝባችንን ከበረሃ እስከ ከተማ እያሰቃየ አሁን እምነትን ሽፋን አርጎ የስልጣን እድሜን ለማራዘም መጣር ጅልነት ነው። ዛሬ መንገድ የሚዘጉት/ወያኔ ይውረድ ብለው በከተማ የሚፋለሙት በራሱ ሥርዓት ተወልደው ያደጉ ወጣቶች ናቸው። ይህ ለወያኔ ትልቅ ትምህርት ሊሆነው ይገባ ነበር። ወያኔ ግን የሚያስበው በጠበንጃ አፈሙዝ በመሆኑ እሳትና የጠራ እይታ አብረው ሂደው አያቁምና የሚራመደው በደንበር ገተር ነው። ወያኔ መተካት እንጂ መታደስ አይቻለውም። ያረጀ/ያፈጀ ድርጅት ነው።
  የክርስቲያን ሃገር በሆነችው ሙስሊሞች ሊነግሱባት ነው ማለትም ተጨፈኑና ላሞኛችሁ ማለት ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያ የእስልምና እና የክርስትና እንዲሁም የሌሎች እምነት ተከታዮች የሚኖሩባት ምድር ናት። ወያኔ የከተማ አለቃ ከሆነ ነው ህዝባችን መተገንና በቅጥር ማሰብ የጀመረው። ለኢትዮጵያ የሞቱላት ሁሉም ናቸው። ሼኩ ከመስጊዱ፤ ከርስቲያኑ ከመቅደሱ ተጣምረው ነው ደማቸውን አፍሰው ከወጭ ወራሪ ጠላት የታደጓት። የወያኔ በህዝባችን ላይ መቀለድ ሊያበቃ ነው። በግድም ሆነ በውድ ለውጥ መምጣቱ አይቀሬ ነው። ይሁን እንጂ ያ ለውጥ ምን ዓይነት መልክ ይኖረዋል የሚለውን መተንበይ አይቻልም። ጠብቆ ማየት ነው።

 6. What really surprising me in life is how some people like our own ‘brothers’ from TPLF keep being wicked against their own Ethiopian family people only just for the sake of their own comfortable life. Based on this, how can we say them human? Actually, whether we accept it or not, behaviour of anyone can be based on the kind of the spirit that governs him, Holy Spirit or Evil Spirit. So, expecting good things from those who are governed by the Evil Spirit is like expecting Chicken from the egg of Snake.

 7. ትቃዣለህ ልበል says:

  ምነው ያ ጠርሙስ የሚጠባው ስብሃት የሚባል አጋሰስ ኦርቶዶክስንና አማራውን አከርካሪውን ገንጥለነዋል ሲል አልነበረም እንዴ ቆሻሻ የባንዳ ልጅ

Speak Your Mind

*