መንግሥት ህወሃትን ቀስ በቀስ ሥሩን እየቆራረጠ ቢቆይም አብዛኞች ባለመረዳትና በተገዙ ኃይሎች ውዥንብር ዕድሜው ሊራዘም እንደቻለ ለህወሃት ቅርበት ያላቸው እየገለጹ ነው። በተቀነባበረ ዕቅድ ሃጫሉ እንዲገደል ተደርጎ መንግሥትን ለመገልበጥ የታቀደውና የመጨረሻ የተባለው ሤራ መክሸፉ ህወሃት መንደር ግራ መጋባት መፍጠሩ ተስምቷል። የዐቢይ አስተዳደር እንደሚባለው ደካማ እንዳልሆነም አንዳንዶቹ በይፋ ሲናገሩ ተደምጧል። ለውጡን ተክትሎ ከህወሃት አሰልቺ የስብሰባና የግምገማ (ምይይጥ) ባህል በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፍጥነት መጓዛቸውና ለህወሃቶች ከጅምሩ የማሰቢያ ጊዜ የከለከለ ነበር። የጎልጉል ታማኝ የመረጃ ምንጭ እንደሚሉት፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ሲነጋ ልክ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ ከፍተኛና አዳዲስ ውሳኔዎችን ይሰማሉ። በዚህም እነርሱ ለአንዱ ጉዳይ አንድ ወር ሲሰበሰቡና … [Read more...] about ህወሃት “የመጨረሻ” ያለው ሤራ መክሸፉን መቀበል አቅቶታል
Archives for July 2020
ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!
“ሃጫሉን የገደሉት ነፍጠኞች ናቸው፤ መላው የኦሮሞ ህዝብ የምኒሊክን ሃውልት አፍርሰህ ወደ ቤተመንግሥት ገስግስ!” ይህንን የዘር ዕልቂት የተናገረው የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ቡድን እነ ጃዋር መሃመድን በቁጥጥር ሥር ከማዋሉ በፊት በሕወሃት የደም ገንዘብ የሚቀለበው ሕዝቅኤል ጋቢሣ አሜሪካ ቁጭ ብሎ ሕወሃት ባደራጀው ዲጂታል ሚድያ በመጠቀም ሲያውጅ ነበር። “በደረሰን መረጃ መሠረት፤ የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ነፍጠኞ ሳይሆኑ ሥልጠናና ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የመጡ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ናቸው፤ እኔ በደንብ አውቃለሁ እነማን እንደገደሉት፤ ምን ዓይነት ሚሊተሪ ፐርሶኔል እንደተሳተፈም አውቃለሁ፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን አይደሉም፤ ኤርትራውያን ናቸው" ይህን የተናገረው ደግሞ በጎጥ አስተሳሰብ እጅግ የጠበበው መርዘኛው ፀጋዬ አራርሳ ነው። ፀጋዬ አራርሣ፤ ሃገር መምራት የማይችል ደካማ ነው፤ … [Read more...] about ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!
የስብሃት ነጋ ወንድም በሌብነት ተያዘ
አቤሴሎም ነጋ የተባለውና ነዋሪነቱ በአውስትራሊያ የሆነው ስብሃት ነጋ ወንድም 4 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር (2.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) በማጭበርበርና በመስረቅ መከሰሱን Herald Sun ዘገበ። እኤአ ከ2008 – 2019 ባሉት ዓመታት የ54 ዓመቱ አቤሴሎም ነጋ የተለያዩ የፋይናንስ ወንጀሎችን በመፈጸም ነው 4.2 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ወደ ግል የባንክ ሒሳቡና iEmpower በሚል ለሚመራው የግል ድርጅቱ ሒሳብ እንዲገባ ያደረገው። ወንጀሉ ስርቆት ብቻ ሳይሆን በኑሯቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሚሰጠውን (የዌልፌር) ገንዘብን አጭበርብሮ መውሰድም የሚጨምር ነው። አቤሴሎም ከዘረፈው ገንዘብ ውስጥ $25,300 የሚሆነውን ያጭበረበረው ከሕግ ጋር ችግር ያለባቸውን የአፍሪካ ወጣቶችን ለመርዳት ከተቋቋመ ድርጅት በመስረቅ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አቤሴሎም የቪክቶሪያ … [Read more...] about የስብሃት ነጋ ወንድም በሌብነት ተያዘ
አርቲስት ሃጫሉ ለምን ተገደለ?
https://www.facebook.com/goolgule16/videos/856526528088415 … [Read more...] about አርቲስት ሃጫሉ ለምን ተገደለ?
ሕልመኛና የቆሰለው አውሬ ጃዋር [እና] ዋኤል ጎኒም
[ጁን 8፤ 2010] ዋኤል ጎኒም (ዕድሜ 28) እንደወትሮው ዜናዎችን ለመቃረም፣ ከዘመድና ወዳጅ ጋር ለመወያየት ዱባይ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተቀምጦ በፌስቡክ መስኮት ወደ ትውልድ ሀገሩ ግብጽ ዘለቀ፤ በዚያን ዕለት ያነበበው ዜና እና የተመለከተው ፎቶ ስሜቱን አወከው፣ እረፍት ነሳው፣ ዜናው አሌክሳንድሪያ ውስጥ በሙባረክ የጸጥታ ሀይሎች በግፍ ስለተገደለው ካሊድ ሰይድ (ዕድሜ 28) ነበር፡፡ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የነበረው የካሊድ አስከሬን በዐይን ለማየት ይከብዳል፡፡ “በዛ አሰቃቂ የካሊድ ፎቶ ውስጥ ራሴን አየሁት፣ በካሊድ ቦታ እኔም ልሆን እችል ነበር ብዬ አሰብኩ” ይላል ዋኤል በዚያች ቅጽፈት የተሰማውን ስሜት ሲገልጽ፣ ከቁጭትና ንዴት ባለፈ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት አሰበ፤ ጊዜ ሳያጠፋ ማንነቱን ደብቆ "We are all Khaled Said/ሁላችንም ካሊድ ሰይድ ነን" … [Read more...] about ሕልመኛና የቆሰለው አውሬ ጃዋር [እና] ዋኤል ጎኒም
ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለ
ከየአቅጣጫው ከተለያዩ ምንጮች ገንዘብ እንደሚለገሰውና የውክልና ፕሮፓጋንዳ እንደሚሠራ ይፋ የተደረገበት ኢትዮ 360 ሚዲያ ይህንኑ ለማስተባበል የገንዘብ ችግር አንቆናል፤ ዋናው ችግሬ ብር ነው እርዱኝ ሲል ባወጣው መግለጫ የልመና ድምጹን አሰማ። በተለይ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በውስጥ በተከሰተ መከፋፈል ምክንያት የተለያዩ ምሥጢሮች እየወጡበት የተቸገረው ኢትዮ 360 አሁን ካለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ራሱን መገምገሙን በመግለጫው ጠቁሟል። ቅዳሜ ዕለት መግለጫው እንደወጣ በዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ (በተለምዶ ዲኤምቪ በሚባለው) የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያነጋገረችው የጎልጉል መረጃ አቀባይ እንዳለችው መግለጫው ሌላ ገንዘብ የመሰብሰቢያ ስልት ነው በማት አስተያየት ሰጪዎች መናገራቸውን ገልጻለች። “ሁሉንም እኮ እናውቃቸዋለን፤ ኮትና ከረባት አሳምረው ሲታዩ … [Read more...] about ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለ
ሕግን በሕግ እናስከብራለን!!
ዘረኛ ፋሺስቶችን ለፍርድ እናቅርብ
የፋሽስታዊው አመለካከት ያላቸው (ethno-fascists) የጸጋዬ አራርሳ፣ የህዝቄል ገቢሳ፣ መሰሎቻቸው፣ እንዲሁም የትግራይ ሚዲያ ሀውስ መርዘኛ፡ ሃሰተኛ ቅስቀሳዎችና ትርክቶች የብሄር ለብሄር፣ የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) ከማድረሳቸው በፊት በአለም ዙሪያ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ ሆነው የተደራጀ፣ የተቀናጀ፣ የተናበበ ስራ መስራት ይገባል። ባልተናበበና በተበታተነ ሁኔታና እንቅስቃሴ ውጤት ለማምጣት እጅግ አዳጋች ይሆናል፣ ሁሉም ባለው መሰለፍ ይገባል፣ የመጣውን ኣደጋ ለመከላከል እንደ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በጋራ መቆም የግድ ነው። የፖለቲካ አመለካከት ወደ ጎን አድርጎ በአንድ ላይ፣ በጋራ መቆም ወሳኝ ይመስለኛል። የሁላችንም ሀገር የሆነችው ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ አዝማዶች፣ ወገኖችና፣ ባጠቃላይም ህዝባችን የሚኖርባት ሀገረ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ ፍጹም ወደ … [Read more...] about ዘረኛ ፋሺስቶችን ለፍርድ እናቅርብ
ጃዋር በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ
ሐሙስ ዕለት በተለያዩ ወንጀሎች ተከስሶ ፍርድ ቤት የቀረበው ጃዋር የባህላዊ ሽምግልና እና ዕርቅ ከመደበኛው ፍርድ ቤት በፊት እንዲሞከር ጥያቄ አቀረበ። እጅግ መረን ከለቀቀና ከተደንደላቀቀ የቅምጥል ኑሮው ወጥቶ ወደ አዲስ “ዓለም” የገባው ጃዋር መሐመድ ያቀረበውን ጥያቄና ተማጽንዖ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አድርጎ ክሱ እንዲቀጥል ቀጠሮ ሰጥቶ አሰናብቶታል። ጃዋር በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የሚያስጠረጥረውን በርካታ መረጃዎች ተከትሎ፤ በኔትወርክ ሊያደርግ ያሰበው የመንግሥት ለውጥ በመክሸፉ፤ በተለይም በአስከሬን ባለቤትነት የተፈጠረው ግብግብ ከፍተኛ ተቃውሞ ስላስነሳበት የሽምግልና አካሄድ እንደሚያዋጣው በመረዳት ጥያቄውን ሐሙስ ለዋለው ችሎት ማቅረቡን በቅርብ ሂደቱን የሚከታተሉ ለጎልጉል ተናግረዋል። ጎልጉል ቀደም ሲል የሽምግልና ሃሳብ እንዳይጨናገፍ በማለት ያላተመውን … [Read more...] about ጃዋር በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ
ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ
ከኢሣት ከተባረሩ/ፈቃዳቸው ከመልቀቁ በኋላ “ኢትዮ 360” የሚል የቱቦ (የዩትዩብ) ቲቪ የተከፈተው “ሚዲያ” የወያኔ መሆኑ ተረጋገጠ። በኢትዮጵያ ለውጥ ከተካሄደ በኋላ በርቀት የተመኙት የውሃ ሽታ ሆኖ ሲቀርባቸው በዶ/ር ዐቢይ ላይ ፍጹም ጭፍን የሆነ የጥላቻ ዘገባ በመሥራት ከህወሃት በላይ አገር በማፍረስ ተግባር ተጠምደው የነበሩት ቀዳሚው አገልግሎታቸው ለህወሃት እንደነበር አብሯቸው ሲሠራ የነበረው አጋልጧል። (ጎልጉልም ይደርሰው ከነበረው መረጃ በመነሳት ሚዲያው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተነሱ ኃይሎች እና ከጽንፈኛ ቡድኖች የቀጥታና ተዘዋዋሪ የጥቅም ተካፋይ እንደሆነ መዘገቡ አይዘነጋም) ሁለቱ የህወሓት አገልጋይ የነበሩት ኤርምያስና ሃብታሙ ከኢሣት አፈንግጠው ከወጡ በኋላ በኢትዮ 360 እስካሁን ያላቋረጠ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በዶ/ር ዐቢይ ላይ እንደከፈቱ ነው። ሃብታሙ … [Read more...] about ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ