የኢትዮጵያ መንግሥት ባፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ተብሏል ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትሕነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ። መረጃው የአፍሪኮም አዛዥ ከጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከተመካከሩ በኋላ መውጣቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት ብቻ ሳይሆን አቅጣጫ ጠቋሚም ነው ተብሏል። “ከባድ ሚስጥራዊ መረጃ፡- ጄ/ል ሳሞራ ዬኑስ በሱዳን 8ሺህ ወታደር እያሰለጠኑ ነው!” በማለት Ethiopian Think Thank Group የተሰኘው ድረገጽ ዛሬ ባስነበበው መሠረት መረጃው የተገኘው ከደኅንነት ሠራተኛ መሆኑን ተናግሯል። … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከአፍሪኮም ዕዝ አዛዥ በተነጋገሩ ማግስት አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ
Archives for November 2019
ችግራችን አጼ ምኒልክ ከሆኑ እውነቱን ተነጋግረን እኛም አርፈን ሕዝባችንን አናሳርፍ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ ያሳስበኛል፤ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሚረከቡን ልጆችና ልጆቻቸው ጭምር ሳስብ የሀገራችን ፖለቲካ እንዳልተፈጠረ ሰው ቢታሰብ ደስ ይለኛል፤ ምክንያቱም በመኖሩ የሚፈይደው ከሌለ፡ አለመኖሩ እጅግ የሚሻል ነውና:: ነገር ግን ወደንም ሆነ ሳንወድ ተፈጥሯልና ስለእርሱ (ስለፖለቲካችን) ማሰብ ግድ እንደሚልም አምኛለሁ። በዚህ ዓለም ያሉ ምሁራን ፖለቲካ የአንድን ሰው ሕይወት የሚነካና ሰውም ከፖለቲካ ርቆ መኖር የማይችል ፍጡር ነው ይላሉ። እውነትም ፖለቲካ ብትርቀውም ተከትሎህ ባለህበት ይነካሃል፤ ብትቀርበውም ደግሞ የበለጠ ይነካሃል። በመሆኑም ምሁራን ያሉት ትክክል ነው ብየ ማሰብን ጀመርሁ። እንግዲያስ ፖለቲካ ዝም ብንለውም፣ ብንርቀውም፣ የማይለቀንና የማይተወን ከሆነ ስለ እርሱ መነጋገርና ማሰብ ግለሰባዊም ቡድናዊም ግዴታ ነው ማለት ነው፤ በዚህ ከተስማማን … [Read more...] about ችግራችን አጼ ምኒልክ ከሆኑ እውነቱን ተነጋግረን እኛም አርፈን ሕዝባችንን አናሳርፍ
ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!
የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር “አለማወቅ” ነው። ይህን ስል ለአንዳንዶች ንቀት አሊያም እብሪት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ስለ እኔ የሚኖራችሁ ስሜት ያነሳሁትን ሃሳብ ቅንጣት ያህል አይቀይረውም። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ያለው መሰረታዊ ችግር አላዋቂነት ነው። አዋቂ ማለት ጠያቂ ነው። ምንም ነገር ሲሆን “ምን? የት? እንዴት? ለምን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳል። ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ሲያገኝ እርምጃ ይወስዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጥያቄ የሚጀምረው ከድርጊት በኋላ ነው። በተለይ የዛሬ ትውልድ የፊት ገፅታሀን የሚያጣራው አንገትህን በሜንጫ ቆርጦ ከጣለ በኋላ ነው። ለምሳሌ አቶ ጃዋር መሃመድ በፌስቡክ ገፁ ላይ “ተከብቤያለሁ” ብሎ ሲፅፍ በዚያ ውድቅት ሌሊት ወጣቱ ድንጋይና ፌሮ ይዞ መሮጥ ከመጀመሩ በፊት “ጃዋር ማንና የት ነው? ጃዋር ለምንና እንዴት … [Read more...] about ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!
የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል
ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት 30 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፋለች! ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ መሸሸቱንና ገንዘቡንም ለማስመለስ መንግሥት ከባድ ሥራ ከፊቱ እንደሚጠብቀው ምሁራን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሀገር የሸሸውን ገንዘብ ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት ቢጠይቅም መንግሥት ጉዳዩን እንደሚከታተለው አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዳልታዬ ምሁራኑ ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ እንደገለጹት በኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ ሀገራት በሙስና እና ማጭበርበር የሸሸው ገንዘብ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ በጥናት ተረጋግጧል፤ ገንዘቡም በወቅቱ የኢትዮጵያን የስድስት ዓመት ተኩል በጀት መሸፈን የሚችል … [Read more...] about የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል
መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
የዐቢይ ንግግር አምቦን ወደ ቀልቧ መልሷታል የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት/ትህነግ) መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ከ300 በላይ ዜጎችን/በብዛት ኦሮሞዎችን/ ጨፍጭፎ በአንድ ጎድጓድ በቤተመንግሥት ቀብሯቸው እንደነበር ታወቀ። አጽማቸው ተለቅሟል። ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአምቦ የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ካነጋገሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ቀልቧ፤ ሕዝቡም ወደ ልቡ መመለሱ ተሰማ፡፡ የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ህወሓት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና ባብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች በመለስ ውሳኔ ተገድለው በአንድ ጉድጓድ አፈር ተመልሶባችዋል። የእነዚህ ዜጎች አጽም የተገኘው ሆን ተብሎ በተካሄደ ቁፋሮ ሲሆን እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ከአጽሙ ጋር መረጃ ሰነዶችም ተገኝተዋል። በዘመነ ህወሓት ለሚዲያ ፍጆታ ደርግ … [Read more...] about መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!