ከጥቂት ቀናት በፊት በደሴ ከተማ አንድ የሰባት አመት ታዳጊ ለቀናት ከጠፋች በኋላ፤ ተገድላ መገኘቷን ተከትሎ የተቆጡ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር። በወቅቱ ታዳጊዋ ከመገደሏ በፊት መደፈሯን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተያያዘ ታዳጊዋን አስገድዶ በመድፈር የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል። አሰቃቂ ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ቀደም ሲል የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በርካቶች ሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ። በርካታ ቁጥር ያላቸው የደሴ ከተማዋ ነዋሪዎች የሰባት ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል እርምጃ እንዲወሰድበትም ትላንት በአደባባይ ጠይቀዋል። የሟች ህጻን በጸሎት ብርሃኑ እናት ወይዘሮ አበባ ሙህዬ … [Read more...] about የሰባት አመቷ ህፃን በፀሎት ብርሃኑ – ተሰርቃ፣ ተደፍራ በግፍ የተገደለች‼
Archives for November 2018
አዲሷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዜግነት ካናዳዊት ናቸው
በዚህ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል። ሹመታቸውም በሥራ ላይ ያለውን ሕግ የሚጻረር ነው ተብሏል። ወ/ሪት ቢልለኔ ለማስተርስ ዲግሪ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሁፍ “Transformative Spaces: Enabling Authentic Female Leadership Through Self Transformation - the Association of Women in Business” ወደሚል መጽሐፍ ቀይረው ባሳተሙት ገጽ 16 ላይ በትውልድ ኢትዮጵዊት በዜግነት ግን ካናዳዊት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከዚህ አንጻር ከታየ ሹመታቸው የሕግ ጥያቄ እንደሚስነሳ የሪፖርተሩ ዳዊት እንደሻው ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ይናገራሉ፤ “አዋጅ ቁጥር 270/1994፣ ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በትውልድ … [Read more...] about አዲሷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዜግነት ካናዳዊት ናቸው
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሹመት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ መሠረት ነገ ጠዋት 1:30 አዲስ አበባ ~ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ይደርሳሉ። ተወልደው ባደጉበት አዲስ አበባ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ሠፈር ለብርቱካን ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። ሪፖርተር በዘገበው መሠረት ብርቱካን “በመንግሥት ጥሪ ወደ አገር ቤት ጠቅልለው ከተመለሱ ምናልባትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር፣ ወይም የፌዴራል የመጀመርያ ወይም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ተደርገው ሊሾሙ እንደሚችሉ ከወዲሁ ትንበያዎች እየተሰሙ ነው” ብሏል። ወ/ሪት ብርቱካን ወደ አዲስ አበባ ከመብረራቸው በፊት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በሰጡት አስተያየት “አገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ለመርዳት ማንም ሰው የሚችለውን ነገር ለማድረግ ወደ ኋላ የሚልበት ጊዜ አለመሆኑን በመረዳት እኔም በበኩሌ … [Read more...] about ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሹመት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ
ሽመልስ አብዲሳ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ
ለበርካታ ወራት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ፍጹም አረጋ ወደ ቀድሞ መሥሪያ ቤታቸው የኢንቨስትመንት ጽ/ቤት እንደሚመለሱ ከተነገረ ወዲህ ቦታቸውን የሚተካው ማን እንደሚሆን እስካሁን አልታወቀም ነበር። ዛሬ ከተለያዩ ምንጮች የተሰራጨው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ሽመልስ አብዲሣ የፍጹም አረጋን ቦታ ተክተው እንደሚሠሩ ታውቋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በአዲስ መልክ በተደራጀው “ፕሬስ ሴክሬተሪ” ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀኑ በ8:00 ላይ በጽ/ቤቱ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ሹመቱም በዚሁ ጊዜ ይፋ እንደሚገለጽ ይነገራል። አቶ ሽመልስ አረጋ በቡድን ለማ (ቲም ለማ) ውስጥ ቁልፍ ቦታ የነበራቸው የለውጡ አካል ሲሆኑ የኦዴፓ እና ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባል ናቸው። አቶ ሽመልስ በኦሮሚያ ክልል የኮንስትራክሽን ቢሮ … [Read more...] about ሽመልስ አብዲሳ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ
በሟቹ ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ያስከተለው እሰጥ አገባ
“በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በጎፈንድሚ የተሰበሰበውን 73 ሺህ 9 መቶ ዶላር ወደ አካውንት ለማስገባት ፈቃደኛ አይደለሁም። ምክኒያቱም በኮሚቴው እምነት የለኝም” አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ። “በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በጎ ፈንድሚም ሆነ በማናቸውም መልኩ የተሰበሰበው ገንዘብ በስሙ ወደተከፈተው የባንክ አካውንት መግባት አለበት” የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የህክምና ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ። ይህ እሰጣ አገባ የተካሄደው ቅዳሜ ጥቅምት 24 በአፍሮዳይት ሆቴል የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የህክምና ገቢ ለማሰባሰብ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ኮሚቴ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ኮሚቴው ለሁለት የተከፈለበትን ጉዳይ አንስቶ ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንደገለጸው በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ጉዳይን አስመልክቶ የተጓዘባቸውን ርቀቶች ዘግቧል። ከአርቲስት ፍቃዱ … [Read more...] about በሟቹ ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ያስከተለው እሰጥ አገባ
ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ
ተጠናቀቀ በተባለው የጋምቤላ ክልል ግምገማ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ለመሾም የገንዘብ ኃይል ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረገ መሆኑ ተሰማ። ግምገማውን እንዲመሩ የተመደቡት ግለሰቦች የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ምደባ በተመለከተ ከሌሎች ጋር በመሆን በገንዘብ ኃይል የሚፈልጉትን ለመሾም ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተነገረ ነው። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” ማለታቸውን ጠቅሶ በክልሉ የተንሰራፋውን ግፍና ሙስና (ሌብነት) በተመለከተ ሰፋ ያለ ዘገባ ካወጣ በኋላ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ለመሾም በታቀደው ድብቅ አጀንዳ ላይ ችግር መፈጠሩ ተሰምቷል። ለአሥር ቀናት የተካሄደውን ግምገማ የመሩትን በተመለከተ ጎልጉል ዘገባውን ሲያቀርብ “ግምገማውን እንዲመሩ ከፌዴራል መንግሥት የተወከሉት ፈቃዱ ተሰማ እና ተፈራ … [Read more...] about ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ
“ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
ላለፉት ሰባት ዓመታት የጋምቤላ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) ሊቀመንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ጋትሉዋክ ቱት ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው “በፈቃዳቸው” ለቅቀዋል። ከእርሳቸው ጋር አብረው ምክትላቸው ሰናይ አክዎርም ከፓርቲው ምክትል ኃላፊነታቸው እንደዚሁ በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። በምትካቸው የክልሉ የሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኃላፊ ዑመድ ዑጁሉ ሊቀመንበር፤ የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትና የክልሉ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ታንኩዌይ ጆክ ሮምን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የክልሉ ነዋሪዎች ምርጫውን “የቀድሞ ደጃዝማቾች ካባቸውን አውልቀው ለሚፈልጉት በመስጠት እንደሚሾሙት ጋትሉዋክም ለዘመዱ የስልጣኑን ካባ ያጎናጸፈበት ቀልድ ነው” ሲሉ አውግዘውታል፤ ይልቁኑም ጋትሉዋክ ቱት በበርካታ ወንጀሎች የሚጠረጠሩ ስለሆነ ሌሎቹንም አመራሮች ጨምሮ ሁሉም “ለፍርድ መቅረብ … [Read more...] about “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች