ለበርካታ ጋዜጠኞች ከሥራ መፈናቀል፤ ከአገር መሰደድ ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅነት የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ የነበረው ዘርዓይ አስገዶም ከሥልጣኑ ተነስቷል። አንደበቱ በቅጡ ያልተገራና ፍጹም የህወሓትን ዓላማ በአደባባይ በማስፈጸም የሚታወቀው ዘርዓይ፤ ከዚህ እንደፈለገ ከሚነዳው መ/ቤት መልቀቁ በሚዲያው ማኅበረሰብ ዘንድ እንደ ታላቅ አዎንታዊ እርምጃ ተወስዷል። አንዳንድ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በላይ በቀለ፣ መሠረት አታላይ፣ ዮናስ ዲባባ፣ አስካለ በላይ፣ ካሳሁን ፈይሳ፣ እና ሌሎችም የሙያው ሰዎች በዚሁ የህወሓት ተጋዳላይ ትዕዛዝ ከሥራቸው እንዲለቁ መገደዳቸው ይታወቃል። ዘርዓይ በሥልጣን በቆየባቸው ዓመታት ሦስት ብቻ በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦች የነበሩ ሲሆን በክልላዊ ነጻነት የሚንቀሳቀሱትን የአማራ ሚዲያና የኦሮሚያ … [Read more...] about የሚዲያው “እንቦጭ” ዘርዓይ አስገዶም ተነቀለ
Archives for May 2018
ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
የራሱ የሆነ ገንዘብ ሳይኖረው “ልማት አከናውናለሁ” በማለት መሬት ሲወስድ፣ አጥር አጥሮ ለዓመታት ባዶ መሬት ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ፣ በወሰዳቸውና ፋብሪካ ከፈትኩባቸው በሚላቸው ድርጅቶች አለአግባብ ከመበልጸግ አልፎ ተገቢውን ግብር ባለመክፈል፣ እንዲከፍል ሲገደድ ደግሞ የህወሓት ወንበዴ ሹመኛዎችን በመደለል፣ ኪሳቸውን በማደለብ፣ የሕዝብ ተቀባይነትን ለማግኘት ታዋቂ በሆኑ ግለሰቦችና ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ከሰበሰበው ሃብት ፍርፋሪውን በመጣል “የሕዝብ ልጅ” በመባል፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሐብት በጨበጣ ኪሱ ያስገባው አላሙዲ በለገደንቢ የወርቅ ምርት እንደ ስንዴ በመሰብሰብ የአገርና የሕዝብ ሃብት ሲዘርፍ በወገን ላይ ያስከተለው ጉዳት ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ነው። የአላሙዲ ሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢን ምድር ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ አካባቢውን የዕርግማን ምድር፤ ቦታውን “የእርም” መሬት … [Read more...] about ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”
ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል። ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል። የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ … [Read more...] about በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”
የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
በእርግጥ ፖለቲካ ማለት ልክ "Bicycle" ነው። ሁልግዜም በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሽከርከር አለበት። ለውጥና መሻሻል ከቆመ ልክ እንደ "Bicycle" ፖለቲካዊ ስርዓቱም ተንጋሎ ይወድቃል። ህወሓት የማይለወጥ የፖለቲካ ቡድን ከመሆኑም በላይ ሌሎች እንዳይለወጡ የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ ቡድን ነው። ስለዚህ ይህ ቆሞ-ቀር ቡድን የሌሎችን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመታከት ጥረት ያደርጋል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥና መሻሻል ጠፍቶ መንግስታዊ ስርዓቱ ለመውደቅ እየተንገዳገደ ባለበት ወቅት እንኳን ህወሓት በኦህዴድ መሪነት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ላይ-ታች ሲል ነበር። አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንደመጣ የወሰደው የለውጥ እርምጃ ፀረ-ለውጥ አቋም ከሚያራምደው የህወሓት ቡድን ራሱን ማላቀቅ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ … [Read more...] about የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!