Archives for November 2016

ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል

የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ ረቡእ ማምሻውን በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ለማረጋገጥ ችለናል። በዛሬው እለት ፕ/ር መረራ ጉዲና መኖርያ ቤት በደህንነቶች እና ከባድ መሳርያ በታጠቁ የአጋዚ አባላት ተከብቦ መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብእር ብቻ ለያዘ አንድ ሰላማዊ ሰው ይህን ሁሉ ሃይል ማሰማራት ስርዓቱ ምን ያህል እንደተብረከረከ የሚያሳይ መሆኑን እማኞቹ ጨምረው […]

Read More...

ዲያስጶራዎቻችን

(የሙሉቀን ተስፋው ምልከታ)

ዲያስፖራ (ዲያስጶራ) የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹ብትን /የተበተነ›› ወይም በአጪር አነጋገር ከትውልድ አገሩ ውጭ ተበታትኖ ያለ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ በዚህ ትርጓሜ ከኢትዮጵያ መቶ ሜትርም ይሁን አንድ ሺሕ ማይል ይራቅ ከድንበር ማዶ ያለ ሁሉ ዲያስፖራ ነው፡፡ የምንገኝበት አገር፣ የትምህርት ደረጃችን፣ የወጣንበት መንገድ፣ ሃይማኖታችን ወይም ብሔራችን ዲያስፖራ ከመሆን (ከመበትን) አያድነንም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በአውሮፕላንም ይሁን በመርከብ፣ ጥገኝነት ጠይቆም […]

Read More...

“የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው…” “BBN (አቶ አብዲረሂም አህመድ)

በኦሮሞ ስም እየተደረጉ ያሉትን አብዛኛዎቹን ስብሰባዎች ላስተዋለ ሰው፣ የኦሮሞ ጎሳ ብቻ ሳይሆን በአመዛኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ስብስብ እየመሰለም (“ሆኗል” አለማለታችን ይያዝልን) ሄዷል። አቶ ጃዋር ሙስሊም ከመሆኑ እና ራሱን የኦሮሞ የፖለቲካ ተወካይ/ተጠሪ አድርጎ በየመድረኩ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኦሮሞ ተውላጅ ልሂቃን፣ አቶ ጃዋርን “በሜጫ አንገት የመቁረጥ” ፉከራው ጋር አዝለው፣ አንድም ጊዜ በአደባባይ ይቅርታ […]

Read More...

የኢትዮጵያን ፍላጎት ያልተረዳ መንግስት ኢትዮጵያን ሊመራ አይችልም

(ገለታው ዘለቀ)

በቅርቡ ፋና ብሮድካስት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ “ኢሕአዴግን” የወከሉት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ምክትል ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን  ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ጥቂት ለመወያየት ነው የዛሬው አሳቤ። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ እኚህ ሰው የተናገሩት ብዙው ነገር ከተለመደው የተለየ ባይሆንም በተለይ የኢትዮጵያን ፍላጎት በተመለከተ የፓርቲያቸው አመለካከትና ጥናትና ምርምር ምን መሰረታዊ ችግር እንዳለበት መመርመር የዚህን መንግስት መሰረታዊ […]

Read More...

የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር

31 ሚሊዮን፣ 7 ሚሊዮን ወይስ 50 ሚሊዮን!

መግቢያ ያለፉትን 40 ዓመታት ፖለቲካችንን ለመረመረ አገርን በሚመለከት የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ወይም የሚሰጡት ትንተናዎች ሁሉ ሳንይሳዊ ይዘት ይኑራቸው አይኑራቸው የሚጠይቅ የለም። በተለይም ፖለቲካ ፍልስፍናዊ መሰረት ያለው ታላቅ ፅንሰ-ሃሳብ መሆኑ ግንዛቤ በሌለበት አገርና፣ ማንኛውም ህብረተሰብንና የአገርን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት ረገድ የግዴታ ሳይንሳዊ ትንተና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቶ ስሜት ዋናው መመሪያ በሆነበት አገር የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ትክክል መሆናቸውንና አለመሆናቸውን […]

Read More...

የሽግግር ሃሳብ

[ሽግግሩ ካንዱ መከራ ወደሌላው የሚያስወስደን መሆን የልበትም]

“. . . ገብረሕይዎት በመንግሥት እና የህዝብ አስተዳደር መፅሃፉ መቅድም ላይ እንዲህ ይላል፤ «ሕዝቦችን ሁሉ የሚፈጥር አንድ አምላክ ነው። ይህም አምላክ የምንለው የሕዝቦች ፈጣሪ ሕዝቦችን ሁሉ ትክክል አንድ አድርጎ ፈጥሮ ላኗኗራቸውና ለልማታቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ከሙሉ ፈቃድና ስልጣን ጋር በእጃቸው ሰጥቷቸዋል። ስለዚህ ማናቸውም ህዝብ ቢለማም ቢጠፋም በገዛ እጁ ነው። ሕዝብ የሚጠፋበት አንዳንድ ምክንያት ቢያገኝ ያውም […]

Read More...

የዐማራ ድምፅ ሬድዮን እንርዳ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

በአሁኑ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉ ነገር እያለው ሁሉንም ያጣ ዜጋ ዐማራው ነው ቢባል የተጋነነ ነው ሊባል አይችልም። በግልጽ እንደሚታወቀው፣ ዐማራው ቋንቋው አማርኛ ነው። ይህንን ቋንቋውን ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎች ቋንቋዎች ጋር አጣጥሞ በማሳደግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ መግባቢያ እንዲሆን አበርክቷል። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ጊዜ የአማርኛ ቋንቋ ለዐማራው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተለይቶ መከበሪያው መሆኑ ቀርቶ መጠቂያው ሆኗል። በአማርኛ ቋንቋ […]

Read More...

የግርማ ይፍራሸዋ ፒያኖ ኮንሰርት በዋሺንግተን ዲሲ

ከ25 ዓመታት በላይ የፒያኖ ድርሰቶችን በመጻፍና በመጫወት የአገራችንን ስም በማስጠራት የቆየው ኢትዮጵያዊው ዜማ ደራሲ እና ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በአሁኑ ቅዳሜ November 26 ምሽት ከ6:30 ጀምሮ በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ ለሚገኙት አድናቂዎቹ ግሩም የሆነ የፒያኖ ሙዚቃ ትርኢት Washington Ethical Society አዳራሽ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል። ግርማ የሙዚቃ ትምህርቱን የጀመረው በልጅነቱ ክራር በመጫወት ነበር። በመቀጠልም በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት (1975-1978 […]

Read More...

ህወሃት እጅ ላይ የንጹሃን ደም እየተንተከተከ ነው!! የምትኮሩ በዚህ ኩሩ

ሁሉም ደጅ እሳት አለ!!

ህወሃት የታሪኩ ካስማና ማገር ከአስከሬን ጋር የተጣበቀ ስለመሆኑ የሚመሰክሩበት የሩቅ ሰዎች አይደሉም። አብረውት በበረሃ የነበሩ፣ አብረውት አመራር ሲሰጡ የኖሩ፣ “በሚያራምዱት አቋም” ከድል በፊትና በኋላ የተለዩት በተለያዩ ሚዲያ ላይ እንደመሰከሩት ህወሃት ደም ምሱ፣ አስከሬን ትራሱ ነው። በነዚሁ የቅርብ ሰዎቹ የተሰሙት ምስክርነቶች ስም፣ ቦታ፣ ጊዜ በመጥቀስ በወቀቱ እዚያው እንደነበሩ በማረጋገጥ እንጂ እንዲሁ በመላ አልነበረም። እነሱ ለአብነት ተነሱ […]

Read More...

በጅዳ ሽሜሲ በር ላይ ወድቃለች የተባለችው እህት ጉዳይ!

በሳውዲ ለተቸገሩት ተወካዮቻችን በቀዳሚነት ሊደርሱልን ይገባል

ከትናንት ጅዳ ውስጥ በጠና ታማ እሷና ልጇ አደጋ ላይ አሉ ስለተባ ለችው እህት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ደርሶኛል። መረጃውን በዝርዝር ያገኘሁት ከሊያ ሾው ነበር፣ ታመመች የተባለችውን እህት በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ እንደደረሰኝ ወደ ጅዳ ቆንስል ደውዬ ለማጣራት ሞክሬ ነበር! በጅዳ ቆንስላ መረጃ ለማግኘት ከባድ እየሆነ መጥቷ ል፣ አንዳንዶች ኃላፊዎች ከዚህ ቀደም በማቀርባቸው ተጨባጭ ሂሶች አኩርፈው መረጃ ላለመስጠት […]

Read More...