የአገራችን አንድነትና ብሎም ሕልውና በቋፍ ባለችበት በዚህ ቀውጢ ወቅት ውይይቱ ሁሉ ማተኮር ያለበት ለሥጋቶቹ ምንጭና ምክንያት ስለሆኑት ስለ ዴሞክራሲ ደብዛ መጥፋት፣ ስለፍትህ መቅጨጭ. በብሔረሰቦች መካከል ስለሚታዩት ጥላቻና ግጭቶች እነዚህን የወለደው ሥርዓት ስለመለወጥ ብቻ መሆን አለበት ሌላው ሁሉ ገብስ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውጭ በሆኑ ጉዳዮች መነጋገር ሥርዓቱን ለውጦ ዴሞክራሲና ፍትህ ለማስፈን በሚደረገው ትግል ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደመቸለስ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሆኖም ዘላቂ የአገር ጥቅሞችን መዘንጋት የኋላ ኋላ ሕልውናን ወደ መፈታተን ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ አገር ከሌለ ዴሞክራሲ ምን ሊፈይድ ፍትህስ ምን ሊረባ? ምናልባት የአገር ሕልውናን እስከመፈታተን ሊደርሱ ከሚችሉ ከዋነኛ የአገር እሴቶች አንዱ የባህር በር አለመኖር ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሁኔታ በማይጨው … [Read more...] about ከድጡ ወደ ማጡ፣ አሰብ በአረቦች እጅ ገባች
Archives for March 2016
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
አድዋ! 120 ዓመት!
“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195 … [Read more...] about አድዋ! 120 ዓመት!
ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…
የዓለም ህዝብ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ድል ያደረገውን የጥቁር ጦር መሪ አጤ ምኒልክን ለማወቅ እጅግ ጓጓ፡፡ ምስላቸውን ለማየት ተቁነጠነጠ፡፡ ሙሉ ታሪካቸውን ለመስማት ተንሰፈሰፈ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም፤ "እንኳንም ደስ አለዎት" ለማለት ከቁጥር የበዙ ደብዳቤዎች ይጎርፉላቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በፖስታ ቤት በኩል የኢትዮጵያ ቴምብር የተለጠፈበት መልስ እንዲላክላቸው ይጠይቁ ነበር፡፡ ለምን… ? ቴምብሩ ላይ ያለውን የምኒልክን መልክ ለማየት፡፡ ባለ ብዙ ዝናና ክብር ባለቤት የሆኑትን የምኒልክን ጥቁር ፊት ለማየት፡፡ የሰው ሀገር ሰው ሁሉ፤ "ዝናውን እንደሰማሁ መቼ ሄጄ ባየሁት"፣ "በጀግንነቱ እንደ ተማረኩ መች ተጉዤ ባገኘሁት"፣ "ካሁን ካሁን ፈቅዶልኝ ወታደር ሆኜ ባገለገልኩት" ያለላቸው አጤ ምኒልክ የኛ ናቸው፡፡ በዓለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ያንበረከከ … [Read more...] about ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…