… ቋንጣ ዜና አመጣሽ አትበሉኝና፤ ሰሞኑን ከፌስቡክ ጠፍቼ በከረምኩበት ወቅት የአራት አመት ከስድስት ወር ልጅ የደፈረው ዋልጌ በአራት ወር "ሲቀጣ"፣ ምስር ወጥ የሰረቀው ሰው ደግሞ አመት ከአራት ወር እስር ተፈርዶበታል ሲባል ሰምቼ በንዴት ስንተከተክ ከርምኩ፡፡ ከዚያ ደግሞ እነ አብርሃ ደስታ ሲፈቱ በደስታ ተፍነከነኩ፡፡ …ልጅ ሆኜ እናቴ ሰው ቤት ይዛኝ ሄዳ ለየኔ ቢጤ ምግብ ለመስጠት የሚሰስት ሰው ስታይ፤ "አበስኩ ገበርኩ…!ደግሞ ለሞተ…ለበሰለ ምግብ መስቆንቆን ምንድነው!" ትል ነበር፡፡ እነሆ ፍትሃችን፣ "የበሰለ" እና "የሞተ" ምግብ ለሰረቀው ሰውዬ ፣ አመት ከአራት ወር! "ያልበሰለች" እና "ታዳጊ" ልጅ ለደፈረው ሰውዬ፣ አራት ወር ሆኗል፡፡ እነሆ ፍትሃችን፣ እንዲህ እንዲህ የሌሎችን መብት ግጥም አደርጎ የሚጥስን ማበረታቻ በሚመስል የአራት ወር "ቅጣት" … [Read more...] about እነሆ ፍትሃችን
Archives for August 2015
በአፋር የተከሰተው የዝናብ እጥረት ያስከተለው ጉዳት
በሚሌ ወረዳ የሀርሲስ ቀበሌ ነዋሪዎች በድርቅ መጎዳታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ጋብሩ በአፋር ክልል ተዘዋውሮ ዘግቧል። ነዋሪዎቹንና የአፋር ክልል የመንግስት ባለስልጣኖችንም አነጋሯል። የሞቱ እንስሳት እንዳየና በህይወት የተረፉትም በምግብና በውሀ እጥረት ምክንያት እጅግ የተዳከሙ መሆናችውን ግርማይ ገብሩ ገልጾልናል። መንግስት በበኩሉ ምግብና ውሀ እያቀረበ መሆኑን በሰመራ የክልሉ የአደጋ ዝግጁነትና የምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ዐይሻ መሐመድ እንደገለጹ በዘገባው ጠቅሷል። (ሰሞኑን ከውጭ የመጡ ኢትዮጵያውያንን እያግባባ ያለው ኢህአዴግ የድርቁ ጉዳይ አሳስቦታል። ድርብ አሃዝ ዕድገት እየተባለ ሲሰበክ የነበረው ሁሉ ማጣፊያው ከመጠን በላይ አጥሮዋል። "ዴሞክራሲያዊ ፍትሃዊ እና ተዓማኒ የነበረውን ምርጫ" እንዳያበላሽ የተፈራው ድርቅ አፍንግጦ ወጥቶዋል። … [Read more...] about በአፋር የተከሰተው የዝናብ እጥረት ያስከተለው ጉዳት
ይህ ረሃብ “ፖለቲካዊ ችጋር” ነው!!
ህወሃት ለአገራችን የቀመመው የበቀልና የተላላኪነት ፖለቲካ ገና ጦሱ አልጀመረም። ግን ሊመጣ ግድ ነው። በንጉሡ ወቅት ተርበናል። በደርግ ጊዜ ተርበናል። ኢህአዴግ ከመጣ ጀምሮ የታዩት ርሃቦች ግን ለየት ያሉ ናቸው። ስለዚህ ርሃቡም ሆነ ችጋሩ ፖለቲካዊ ነው ቢባል ያስማማል። ኢሣ የግጦሽ ሳር ሲያጣ ወደ ጎረቤቶቹ ያመራ ነበር። አፋር ተመሳሳይ ችግር ሲገጥመው ከብቶቹን እየነዳ ችግርን አሳልፎ ይመለስ ነበር። መጠነኛ አለመስማማት /በግጦሽ መሬት/ ከመፈጠሩ ውጪ “እገሌ ነህ” በሚል ጎጥ ለይቶ ሲጋደል አልተሰማም። ዛሬ ህወሃት ሌሎችን እንደራሱ ለማሳነስና ለመበጣጠስ ሲል በዘርና በጎሳ መባላትን በአዋጅ ደንግጎ፣ በህግ አጽድቆ፣ ባገር ሚዲያ ጥላቻን እየሰበከ ተፋቅረው የኖሩትን አባልቷቸዋል። እያባላም ነው። ብዙ ሳይቆይ ራሱንም ጨምሮ የሚበላውን እሳት በየቀኑ እያጋመውም ይገኛል። እናም ሰሞኑን … [Read more...] about ይህ ረሃብ “ፖለቲካዊ ችጋር” ነው!!
በአፋር በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች ይሞታሉ
* እንደተለመደው ኢህአዴግ የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም እያለ ነው ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት የድርቅ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት የፈጠረ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የዝናብ እጥረት ቢኖርም የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም ብሏል፡፡ በአፋር ክልል ግን ሁኔታው ተባብሷል፡፡ በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች በመኖና በውሃ እጥረት እየሞቱ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ የአፋር ክልልን አቋርጠው ወደ ጅቡቲ ወደብ ከሚጓዙ ሹፌሮች አንዱ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፤ በመንገድ ዳርና ዳር በርካታ በጎችና ፍየሎች ሞተው ይታያሉ፡፡ በክልሉ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዝናብ የጣለባቸው ቀናት በጣት የሚቆጠሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የድርቁ ሁኔታ እየተባባሰ ቢሆንም በመንግስት … [Read more...] about በአፋር በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች ይሞታሉ
የመድረክ አስቸኳይ ጉባዔ
በቅርቡ የተካሄደውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሂደትና ውጤት እንደማይቀበለው ተቃዋሚው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ጉባዔ በይፋ አስታውቋል። “ኢሕአዴግ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጧል” የሚለው የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አነጋገር አምባገነኖችን ያበረታታ ነው፤ ሲልም መድረክ ተችቷል። በሙስሊሙ ኅብረተሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ በሌሎች የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላትና በጋዜጠኞች ላይ በቅርቡ የተላለፈውን ፍርድ ፍትሐዊ ያልሆነ፤ ኢሕአዴግ በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ጣልቃ እንደሚገባ የሳየ ነው ብሏል መድረክ፡፡ ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያስታወቁት የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከሚቀጥለው ጉባዔው በኋላ መድረክ እንደሚዋሃድ ጠቁመዋል። ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡ (ምንጭ፦ ቪ.ኦ.ኤ) … [Read more...] about የመድረክ አስቸኳይ ጉባዔ
ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ…!
* የ4 ዓመት ከ6 ወር ህጻን የደፋረን በ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል? * ወላጆቿ "ወላጅ ይፍረደን፣ ህዝብና ሀገር ይፍረደን!"ይላሉ የኢፌዴሪ ህገ መንግሥት ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በሕገ-መንግሥቱ እኩል መብትና ጥበቃ እንዲሰጣቸው ይደነግጋል። ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም … [Read more...] about ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ…!
ታሪክ የማይረሳው የኮሚቴዎቹ ስቅየት
የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፈንታ አጨልመን እንድናይ ከሚያስገድዱን ሁነቶች ውስጥ ለእስልምና ሃይማኖት የትኞችም አይነት ጥያቄዎች በአገዛዙ በኩል እየተሰጡ ያሉ አሉታዊ ምላሾች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሐምሌ 27/2007 ዓ/ም የተላለፈው “የፍርድ ውሳኔ” ኢሕአዴግ የሚል ገዥ መደብ እስልምናን በምን ያህል መጠን አፍኖ እየገዛ እንዳለ የአደባባይ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል፡፡ በኮሚቴው አባላት ላይ የተላለፈውን “የፍርድ ውሳኔ” ከሃይማኖታዊ መነጸር ባሻገር ጉዳዩን ከፍትህና ከሞራል ልዕልና አኳያ ማየት ተገቢ ነው፡፡ የዚህ አጀንዳ ቀዳሚ ጉዳይ የኮሚቴውን አመሰራረት በማስታወስ የፍርድ ሂደቱን በመጠኑም ቢሆን በመቃኘት የኮሚቴ አባላቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ በተመለከተ ሦስት የሚሆን እድል (Scenarios) በማስቀመጥ ማሳየት ይሆናል፡፡ የንቅናቄው … [Read more...] about ታሪክ የማይረሳው የኮሚቴዎቹ ስቅየት
የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር የባንክ ሒሳብ ውስጥ የተገኘው 675 ሚሊዮን ዶላር የማን ነው?
የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጂብ ራዛክ የግል የባንክ ሒሳብ ውስጥ 675 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህም ገንዘብ ከየት እንደተገኘ የአገሪቱ የፀረ ሙስና ኮሚሽን በምርመራ እንዲያጣራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተፅዕኖ እያደረጉ ናቸው፡፡ ኮሚሽኑ ባለፈው ሰኞ እንደገለጸው፣ 675 ሚሊዮን ዶላር ያህል ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ራዛክ የግል ሒሳብ ተዛውሯል፡፡ ይህም ገንዘብ በዕርዳታ የገባ እንጂ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚመራው የአገሪቱ የኢንቨስትመንት ፈንድ የወጣ አለመሆኑን አመልክቷል፡፡ በአገሪቱ ውዝግብ ያስነሳውና የጠቅላይ ሚኒስትሩን መንግሥት ያንቀጠቀጠው ይኼ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ፣ በአገሪቱ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በዕርዳታ የመጣ ነው ቢባልም፣ ኮሚሽኑ ዕርዳታውን የሰጠውንም ሆነ በባንክ አካውንቱ ያስቀመጠውን ግለሰብ ወይም አካል አላሳወቀም፡፡ በመሆኑም ኮሚሽኑ ሊያድበሰብስ … [Read more...] about የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር የባንክ ሒሳብ ውስጥ የተገኘው 675 ሚሊዮን ዶላር የማን ነው?
በሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፀረ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃውሞ ተደረገ
ሰሞኑን ህወሃት/ኢህአዴግ በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውሳኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ አርብ ኦገስት 7 2015 ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል። ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት ይህ ታላቅ ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደ ነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱ የትግሉ አንድነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በአገዛዙ ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተዋል፡፡ ሲቀጥሉም ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥ ትግሉን በበሰለና በሰለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም … [Read more...] about በሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፀረ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃውሞ ተደረገ
ኢህአዴግ በኤርትራ አራት አቅጣጫዎች ጥቃት ሊሰነዝር አስቧል
ኢህአዴግ በአራት አቅጣጫዎች የጦር ጥቃት ለመሰንዘር ማሰቡ ተሰማ፡፡ ይኸው ሃሳብ ለአሜሪካ ቀርቦላታል፡፡ በቅርቡ የተጠናከረ እንቅስቃሴ የጀመረው የአርበኞች ግንቦት ፯ ኃይል በተደጋጋሚ በሚያወጣው መረጃ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ማድረሱን በይፋ ቢገልጽም ኢህአዴግ ጥቃቱን በቀጥታ ለማስተባበል እስካሁን አልወደደም። ይሁን እንጂ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ “ህዝብ አስፈቅደን” ሲሉ ኤርትራን እንደሚወጉ ይፋ አድርገዋል። አብዛኞች እንደሚስማሙበት ዛቻው ግጭት ስለመኖሩ የሚያረጋግጥ ነው። በሌላው አንጻር ደግሞ ይህንን የሃይለማርያም ንግግር የኤርትራው ሹም በዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የተለመደ የህወሃት/ኢህአዴግ ማስፈራሪያና ዛቻ በማለት አጣጥለውታል፡፡ የግጭቱን ደረጃና በኢህአዴግ ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ኢሳት ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ኤርትራን መውቀሰና ማስፈራራት የጀመረው ኢህአዴግ፣ … [Read more...] about ኢህአዴግ በኤርትራ አራት አቅጣጫዎች ጥቃት ሊሰነዝር አስቧል