ስለ ሳሙኤል ግድያ ብዙ ነገር ተብሏል፡፡ ብዙዎች ቁጭታቸውን ገልፀዋል፡፡ ለእኔ ከሳሙኤል አወቀ ግድያ ምን እንማራለን? የሚለው ነው ትልቁ ቁም ነገር፡፡ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ንግግር ተናግረው የተገደሉ ሰዎች ጋር የሚመደብ ሰው ነው፡፡ የሳሙኤል ትውልድ አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ እንደገሚገሉት እያወቀ፣ ነገር ግን ያ ሞቱ ከንቱ እንዳይሆን አስፈላጊውን መረጃ አስቀምጦልናል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስተምረው ህዝቡ ለጣሊያን እንዳይገዛ ሰብከው ተገድለዋል፡፡ ለዚህም ሀውልት ቆሞላቸዋል፡፡ ይህ መታሰቢያ ለኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ልዕልና እና የአልበገሬነት ምልክት ሆኖ ለዘላለም ይኖራል፡፡ የአቡነ ጴጥሮስን ታሪክ ተማሪዎችም ይማሩበታል፡፡ የሳሙኤልን ንግግርም ወደፊት እድሜ ከሰጠን እኛ እናየዋለን፡፡ እኛ ባንደርስበት እንኳ መጪው ትውልድ … [Read more...] about “የሳሙኤል ግድያ ለታጋዮችም ለገዳዮችም ትልቅ ትምህርት ነው!”
Archives for July 2015
በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ
በኤርትራ ላይ የሚካሄደው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ የሚጠረጠረውን በሰብዕና የሚፈፀም ወንጀል እንዲያካትት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትናንት ወስኗል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እንዲመረምር የተቋቋመው ልዩ አጣሪ ኮሚሽን ሥራውን በአንድ ዓመት እንዲያራዝም የተስማማው አርባ ሰባት አባላት ያሉት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ክትትል አካል ነው፡፡ ምርመራው ሙሉ ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ እንዲካሄድ የምክር ቤቱ ውሣኔ አክሎ አሳስቧል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ይፈፀማል የተባለውን ጅምላ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ በአጀንዳነት እንዲያዝ ጥያቄ ያቀረቡት ጅቡቲና ሶማሊያ እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የምርመራውን ጊዜ መራዘም “ኤርትራ ውስጥ እየተፈፀሙ ያሉ” ያላቸው የሰብዓዊ … [Read more...] about በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ
“የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” !
ሰሞኑን ኦባማ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው በሚል፤ ከባህር ማዶ ጫጫታ፤ ከወደ አገር ቤት ደግሞ የጆሮ ብራና የሚጠልዝ ከበሮ ድለቃው ተጧጡፏል:: ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” !
ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት
አቶ አንዱአለም ተፈራ ከገዢው መደብ የምንለይበት በሚል ርእስ ባስነበቡን ጽሁፍ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚለውን አጠራር ለምን እንደመረጡ ያስረዳሉ፡፡ መጠሪያው ለወያኔ የማይገባው በመሆኑና አቶ አንዱዓለም መጠሪያውን ለመጠቀም ያአስቻለኝ ብለው ያቀረቡት ምክንያት በቂና ተገቢ ሆኖ ስላልተሰማኝ ይህችን አስተያየት ጻፍሁ፡፡ ትግሬ ስንል የኢትዮጵያ አንድ ክፍል በሆነው ትግራይ የተወለዱና ትግረኛ ቋንቋ የሚናገሩ ወይንም የወላጆቻቸው ስር ከዛ ሆኖ የትም ይሁን የት የተወለዱና ቋንቋውን ሊናገሩም ላይናገሩም የሚችሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ስለሆነም የትግሬ ነጻ አውጪ ስንል ወያኔ ትናንትም የታገለው ዛሬም ሥልጣን ላይ ሆኖ የሚሰራው እነዚህን ነጻ ለማውጣት ነው፣ እነርሱም ነጻ አውጪነቱን አውቀውና አምነው የተቀበሉት ነው ወደሚል አንደምታ ይወስዳል፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ … [Read more...] about ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት
የጅዳ ቆንስላው ግቢ “ጅቦች”
* የጅዳ ቆንስል ለባላቴናው መሀመድ ፍትህ ይትጋ * የጅዳ ቆንስል የስደት ያሰናከለውን ወንድም ይሸኝ * "ጅቦቹ!" የአንባሳደሩን ተሀድሶ ያኮላሹት ይሆን? የማለዳ ወጌ መነሻ መድረሻ ከወራት በፊት ለኦማኗ ተገፊ ለአልማዝ እና ሰሞኑን እርዳታ ስናሰባሰብለት ለሰነበትነው ወንድም ወጣት አባወራ ለመሀመድ ስላደረጋችሁለት ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ ነው። በላዩ ላይ የአልማዝ እርዳታ ሀገር ቤት በእንክብካቤ ለያዛት ለሜቅዶንያ የማስረከባችን መረጃ አካፍየ በሳምንት እድሜ ለመሀመድ ሁሴን ከ10 ሽህ የሳውዲ ሪያል ወይም ወደ 60 ሽህ የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ ገንዘብ በላይ ማሰባሰቤን መረጃ ከማቅረቡ ጋር ምስጋናየን ለማስተላለፍ ነበር። ለዚህ መረጃ አቅርቦት ስሰነዳዳ በተዛማጅ ስለ ዜጎች መብት ጥሰትና ስለመብት ማስከበሩ ጭብጥ አስተምሮት እናገኝ ዘንድ አንድ መረጃ አገኘሁ። ምስጋናየን ወደ … [Read more...] about የጅዳ ቆንስላው ግቢ “ጅቦች”