የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምፕዩተሬ ላይ “የስለላ ማልዌር ልኮብኝ ሲሰልለኝ ቆይቷል” ሲሉ ኪዳኔ ተብለው የተጠሩ አሜሪካዊ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ወረዳ ፍርድ ቤት ክሥ መሥርተው ጉዳዩ ትናንት ዳኛ ፊት ቀርቧል፡፡ የከሣሽና የተከሣሽ ጠበቆች ረዥም ክርክር አድርገዋል፡፡ የግለሰቦችን የግል ሕይወት ወይም ገመና መዳፈር፣ የስልክ ንግግሮቻቸውን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጥለፍ፣ ኢሜሎቻቸውን ማንበብ ከአግባብ ውጭ፤ እንዲያውም ሕገወጥ የሆነ አድራጎት ነው ተብሎ ይበየንልን ሲሉ የኪዳኔ ጠበቃ ኔት ካርዶዞ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ጠበቃ አድራጎቱን ፈፅሟል የተባለው የውጭ ሉዓላዊ መንግሥት በመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት ክሡን የማየት ሥልጣን የለውም ስለዚህም ችሎቱ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሃኪንግቲም የሚባለው ጣልያን የሚገኝ የስለላ … [Read more...] about ኢህአዴግ በኢንተርኔት ስለላ ተከሰሰ
Archives for July 2015
ሰቆቃ በማዕከላዊ
‹‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡›› አበበ ካሴ እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት … [Read more...] about ሰቆቃ በማዕከላዊ
የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ
እንደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አህዛዊ መረጃ በመዲናዋ ውስጥ 1671 የሚሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ መረጃው ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ኮሌጅ መሰናዶ ድረስ ያሉትን የግል ትምህርት ቤቶች የሚያጠቃልል ሲሆን ፤ ትምህርት ቢሮው በ2006 የትምህርት ዘመን መጨረሻ ወራት ላይ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፣ በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የሚሆኑ ተማሪዎች ይማራሉ፡፡ ትምህርት ቢሮው የ2007 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ አህዛዊ መረጃ አጠናቅሮ በድረ ገፁ ይፋ ባያደርግም ቁጥሩ ካለፈው የትምህርት ዘመን ሊልቅ እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም ከሚጠናቀቀው የሚሊንየሙ የልማት ግቦች አንዱ የሆነውን ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ዕድሜቸው ለትምህርት ለደረሱ ህፃናት የማዳረስ ዕቅድ ያላት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሚሊንየሙን የልማት ግቦች … [Read more...] about የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ
“የክስ መቋረጥ” ወይስ የኦባማ ጉብኝት?
"ክሴን አቋርጫለሁ" ከማለት ባለፈ ምክንያቱን ከመናገር ተቆጥቧል ከአንድ ዓመት በፊት ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በድንገት ተይዘው ከታሰሩ በኋላ፣ በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸውና የሰነድና የሰው ማስረጃ ቀርቦባቸው፣ ለብይን የተቀጠሩበትን ቀን እየተጠባበቁ ከነበሩት አሥር ተከሳሾች መካከል አምስቱ በድንገት ሐምሌ 1 እና 2 ቀን 2007 ዓ.ም. መፈታታቸው እያነገጋገረ ነው፡፡ ለተከሳሾቹም ሆነ ወክለዋቸው ለሚከራከሩላቸው ጠበቆቻቸው ምንም ዓይነት መረጃ ሳይደርሳቸው በድንገት፣ ‹‹ዓቃቤ ሕግ ክሱን አቋርጣል፡፡ በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ከእስር ተለቃችኋል፤›› የተባሉት ተከሳሾች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያን ዘለዓለም ክብረትና ማህሌት ፋንታሁን ናቸው፡፡ ክሱ እንደተቋረጠ በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ከማወቃቸው … [Read more...] about “የክስ መቋረጥ” ወይስ የኦባማ ጉብኝት?
የኢህአዴግ ዉሸት – እስካሁን ደህና ነኝ ማለት
እሙሩ ብሪታንያዊ የምርመራ ጋዜጠኛ ኒኮላስ (ኒክ) ዴቪስ የብዕሩ ሞገስ ይደርጅለትና ዕውነት እንዳንናገር፣ ሀቅ እንዳንዘረዝር የሚያደርጉን ሠለስቱ ቀታሊያን ሥህተቶች፣ ሦስቱ ገዳይ ድክመቶች:- "1) የምንመርጣቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዕውነታውን በመሠረታዊ መንገድ የሚያፋልሱት እንዲሆኑ በማድረግ ዋናውን ጭብጥ ማሳት፣ "2) በተደጋጋሚ የምንጠቀምባቸውን ኢተአማኒ፣ አንዳንዴም ፈጽሞ ውሸት፣ የሆኑ ጭብጦች ደጋግመን በመጠቀም ዕውነተኛ ማስረጃዎች እንዲመስሉ ማድረግ፣ "3) ከአካባቢው ህብረተሰብ መካከል ኃይለኛ ጉልበት ያላቸውን ወገኖች የሚያደምቁ ዕሴቶችን የማያቋርጥ አሻራ እንዲኖራቸው ፖለቲካዊና ሞራላዊ ውትወታን ማብዛት፣ ናቸው" ሲል የጣፈው ቀልብ የሚማርክና ለአብነት የሚጠቀስ መንደርደሪያ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ማለፊያ አስተዉሎት ነው መቼም። ታድያ ይህን የኒኮላስ ዴቪስን ሓቲት ባስታወስኩ … [Read more...] about የኢህአዴግ ዉሸት – እስካሁን ደህና ነኝ ማለት
ክብሩ የተነካው የክብር ዶክትሬት
እንደብዙዎቹ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ዩኒቨርሲቲው በየጊዜው የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር እንዲከፍቱ ለመረጣቸው ታላላቅ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ይሰጣል፡፡ እ.ኤ.አ. 2009 ላይ ግን የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር ለከፈቱት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የክብር ዶክትሬት ላለመስጠት መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፕሬዚዳንቱ ልምድና የሥራ ውጤት ለክብር ዶክትሬት ጣሪያ አልደረሰም የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ጉዳዩ በተወሰነ መልኩ ውዝግብ አስነስቶ የነበረ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የመክፈቻ ንግግር አድራጊዎችንና የክብር ዶክትሬት የሚሰጣቸውን ግለሰቦች የሚመርጥበት የራሱ ነፃ የሆነ ሒደት እንዳለው፤ የክብር ዶክትሬቱ የሚሰጠውም ለትልቅ ስኬት መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ በወቅቱ ዲግሪው የክብር ከመሆኑ አንፃር ዩኒቨርሲቲው አሠራሩን መሠረት በማድረግ በውሳኔው … [Read more...] about ክብሩ የተነካው የክብር ዶክትሬት
የግፍ ሠንደቅ ወረደ!
በአሜሪካ የደቡብ ካሮላይና ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ የሸንጎ ሕንጻ ላይ ከ50 በላይ ሲውለበለብ የነበረው ሠንደቅ አርብ ወረደ፡፡ “ውሸት ለዘላለም መቆየት አይችልም፤ የዘረኝነት ምልክት እና ዘረኝነት መፍረስ ይገባቸዋል” በማለት የሠንደቁን መውረድ የደገፉ ተናገሩ፡፡ በእንግሊዝኛው አጠራር “የኮንፌዴሬት” ሠንደቅ የሚባለው በአሜሪካ የእርስበርስ ጦርነት ወቅት ከኅብረቱ ለመለየት የፈለጉ ግዛቶች የራሳቸውን ፕሬዚዳንት መርጠው ከኅብረቱ ደጋፊዎችና አብርሃም ሊንከን ጋር ጦር በገጠሙበት የተጠቀሙበት ሠንደቅ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት አብርሃም በአሜሪካ ውስጥ የተንሰራፋውን በዘር ላይ የተመሠረተውን ባርነት ለመደምሰስ ህግጋትን እያወጡ በነበሩበት ወቅት በባሪያ ፈንጋይነት የሚታወቁት የደቡብ ጠቅላይ ግዛቶች የባርነትን መወገድ በመቃወም ከኅብረቱ ለመገንጠል በመፈለጋቸው በአሜሪካ የእርስበርስ ጦርነት … [Read more...] about የግፍ ሠንደቅ ወረደ!
ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና
ያልተዘመረላት፣ ያልተነገረላት ጀግና ኢትዮጵያዊት ሴት ናት። እንደሌሎች "እኔ ምን አገባኝ? አርፌ ልቀመጥ" ብላ፣ ባርነትንና ዉርደትን አሜን ብላ ተቀብላ፣ ሕሊናዋን ሸጣ፣ የገዢው ፓርቲ አዉደልዳይ ሆዳም ካድሬና አገልጋይ ሆና፣ በዘረኝንትና በጠባብነት በሽታ ተለክፋ መኖር ትችል ነበር። ግን አላደረገችውም። ከደቡብ ክልል ከወላይታ ሶዶ ናት። የወያኔ ቡችላው ሃይለማሪያም ደሳለኝ መጣሁበት ካለው። እንደ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሌሎች አሽከር አልሆነችም። እንደ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አልተንቦቀቦቀችም። እንደ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሕሊናዋን አልሸጠችም። የወላይታ ጀግና የሆነውን የንጉስ ጦናን ወኔ ተላብሳ፣ ለእዉነት፣ ለፍትህ፣ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለኢትዮጵያ አንድነት ቆመች። የወላይታ ሕዝብ በባህሉ፣ በቋንቋም በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ፣ መብቱ ሲደፈር የማይወድ፣ ታታሪ ሕዝብ ነው። ይች ሴት … [Read more...] about ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና
ያልተፈቱት “አሸባሪዎች”
1 - ተመስገን ደሳለኝ 2- እስክንድር ነጋ 3- ናትናኤል መኮንን 4- አንዳለም አራጌ 5- ውብሽት ታዬ 6- አበበ ቀስቶ 7- ሃብታሙ አያሌው 8- ድልንኤል ሺበሺ 9- አብርሃ ደስታ 10- የሽዋስ አሰፋ 11- ዘላለም ወርቅአገኘሁ 12- አቤል ዋበላ 13- ናትናኤል ፈለቀ 14- በፍቃዱ ሃይሉ 15- አጥናፍ ብርሃኔ 16- ፍቅረማርያም አስማማው 17- እየሩሳሌም ተስፋው 18- ብርሃኑ ተክለያሬድ 19- ኦልባና ለሌሳ 20- ቴድሮስ አስፋው 21- ማትያስ መኩርያ 22- ብሌን መስፍን 23- ተዋቸው ደምሴ 24- ንግስት ወንዳፈራሁ 25- ሜሮን አለማየሁ 26- ደሴ ካህሳይ 27- ናትናኤል ያለምዘውድ 28- ሰንታየሁ ቸኮል 29- ማስተዋል ፈለቀ 30- ንግስት ወንድይፍራው 31- ሂሩት ክፍሌ 32- እማዋይሽ አለሙ 33- ሰለሞን ከበደ 34- የሱፍ … [Read more...] about ያልተፈቱት “አሸባሪዎች”
ይድረስ ለገራፊዎቻችን – እኛ የፀናነው እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው!
"በምርመራው ወቅት የነበረው ድብደባ እና ክብረ ነክ ስድብ ወደ ምድር የመጣሁበትን ቀን እንድረግም አደረጉኝ፡፡ በተለይ ከአሁን በኋላ ልጅ መውለድ እንደማልችል እየዛቱ የውስጥ እግሬን ክፉኛ ገረፉኝ፡፡ . . . እኔም ልብሴን እንደማላወልቅ ነገርኳቸው፡፡ በዚህም ከአሁን ቀደሙ ለየት ያለ ከባድ ድብደባ አስተናገድኩ፡፡ ድብደባው ከአቅሜ በላይ ሲሆን ግን ከውስጥ ሱሪዬ ውጭ ያለውን ልብሴን ለማውለቅ ተገደድኩ፡፡ የውስጥ ሱሪዬንም እንዳወልቅ አዘዙኝ፡፡. . . " ሐምሌ 5/2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ የክረምት መግቢያ መባቻ፣ ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ደግሞ የፆም ሐዋሪያት መፍቻ ነው፡፡ በዚች እለት እኔም እንደወትሮዬ በአካባቢዬ በምትገኝ አንዲት ካፌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ከስርዓቱ አፈና የተረፉትን ጥቂት መጽሔቶች እና ጋዜጦች ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜናዎችን ማንበብ ተያያዝኩት፡፡ በዕለቱ … [Read more...] about ይድረስ ለገራፊዎቻችን – እኛ የፀናነው እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው!