ትናንት ኣመሻሽ ላይ፤ ከYohanes Molla ጋር ተቀጣጥረን ተገናኘን ፡፡ካልዲስ ገብተን እኔ ኣንድ ፍንጃል ቡና ሳዝዝ ፤ ዮሀንስ ሲያቀብጠው ኣንድ ቡና እና የባራክ ኦባማን ጆሮ የሚያህል ቦምቦሊኖ ኣዘዘ፡፡ በመጨረሻ ኣስተናጋጂቱ የእዳችንን ደረሰኝ ኣምጥታ ጠረጴዛው መሀል ላይ ኣኖረችው ፡፡እሱ እኔ እስክከፍል ሲጠብቅ እኔ እሱ ይከፍላል ብየ ስጠብቅ ካብ ለካብ እየተያየን በጣም እረጅም ጊዜ ተጎለትን፡፡ በመካከሉ የኢትዮጵያን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ርእሰ ጉዳይ ጨርሰን "ፌንጣ ስንት እግር ኣላት? ስድስት ነው ኣራት?" በሚል ጉንጭ ኣልፋ ክርክር ተጠመድን፡፡ ወሬ ኣልቆብን ካጠገባችን ከተቀመጡ ተስተናጋጆች ወሬ እየተበደርን ስናወራ ቆየን፡፡ በመጨረሻ ካፌው ጭርር ብሎ ኣስተናጋጆች እንድንወጣላቸው እግራችን ስር መጥረጊያ ኣስገብተው ይጠርጉ ጀመር፡፡ ድንገት በብሄረሰቦች ላይ የሚነገረው ቀልድ … [Read more...] about መቶ ብር ከየት ወዴት?
Archives for July 2015
ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
ለረጅም አመታት፣ ለብዙ ዘመናት፣ ፓርቲ ሲጠልዘኝ፣ መንግስት ሲረግጠኝ፣ ፖሊስ ሲነርተኝ፣ ሕጉ ሳይደግፈኝ፣ ዳኛው ቢፈርድብኝ፣ በቡድን ተካፍለው፣ በስም ተሸንሽነው፣ የሚጠልዟት ኳስ፣ የሚነርቷት ኳስ፣ ምትለጋዋ ኳስ፣ እኔ ራሴን መስላኝ፣ ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ። … [Read more...] about ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ . . .
"…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው። ጊዜው ተቀይሯል። ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም። ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ … " ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የተናገሩት የአስመራ ጉዟቸው ከመሰማቱ ጥቂት ቀናት በፊት ነበር። ንግግሩ ለብዙዎች ግርታ መፍጠሩ አልቀረም። ከቀናት በኋላ የኤርትራን ምድር ሲረግጡ "ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ..." ማለታቸው ግልጽ ሆነ። ከምርጫ 97 በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በፖለቲካ ስብእናቸው የሚታወቁት ለሰላማዊ ትግል ባላቸው የከረረ አቋም ነበር። በእስር ቤት ሆነው በጻፉት "የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፤ ..." መጽሐፋቸው ሰላማዊ ትግል ያለውን የሞራል፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ምሳሌ እያስቀመጡ ዘርዝረዋል። ለዚህም ነበር ከሰላማዊ ትግል ወጥተው "ሁለገብ … [Read more...] about የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ . . .
ብርሃኑ ነጋ “… ዱር ወጡ …”
* የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ብሏል ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሃደው የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የፓርቲው የአመራር አባላት የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ታጣቂዎቻቸው ወደሚንቀሣቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለው መሄዳቸውን የአመራር አባላቱ አስታወቁ፡፡ ብርሃኑ አስመራ መግባታቸው ከተሰማ በኋላ የሠራዊቱ ሞራል ከፍ ማለቱና ከአገር ውስጥ ግምባሩን ለመቀላቀል የሚፈልገው ሕዝብ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ቁጥራቸው ይፋ ያልተደረገ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአመራር አባላትን ይዘው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ኤርትራ ያመሩት ሌሎች አማራጮችን ጨምሮ በብረት ትግልና በሕዝባዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ገዥ ፓርቲ ለማስወገድ መሆኑን የአመራር አባላቱ ይናገራሉ፡፡ “ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ጓዶቻቸው ትግል ወደሚካሄድባቸው አባባቢዎች ያመራሉ” ሲሉ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል ዶ/ር ታደሰ ብሩ … [Read more...] about ብርሃኑ ነጋ “… ዱር ወጡ …”
“ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”
በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት ላይ ኅብረተሰቡ የሚያሰማው እሮሮ ኤሌክትሪኩ መጥፋቱ ብቻ አይደለም፡፡ መብራቱ ሄዶ ሲመጣ የሚያደርሰው ጥፋት የትየለሌ ነው፡፡ የኤሌክትሪኩ ኃይል መጠን ከመደበኛው ውጭ ከፍና ዝቅ ሲል የሚያደርሰው ጥፋት ቤት ይቁጠረው፡፡ ማቀዝቀዣው፣ ቴሌቪዥኑ፣ አምፖሉ፣ ልዩ ልዩ "ቻርጀሮች" የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ተቃጠሉብን የሚል የሕዝብ እሮሮ በየጊዜው ይሰማል፡፡ የሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፈጣን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አገልግሎት የማይሰጠውን "905" ላይ ደውላችሁ አስመዝግቡ ከማለት ያለፈ መልስ የለውም፡፡ "የኤሌክትሪክ ምሰሶው ሊወድቅብን ነው፣ ዘሟል፣ ኧረ ድረሱልን" እያሉ ለሚወተውቱም ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዳልተቻለም ማስረጃ ከሚሆኑ ትዕይንቶች (በፎቶዎቹ የሚታዩት) መካከል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 እንደራሴ አካባቢ ያሉ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች … [Read more...] about “ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”
ጀርመናዊው የገደላት ሰብለ ከአንድ አመት በኋላ በመኖርያ ቤትዋ ተቀብራ ተገኘች
ሰብለ (ሚሚ) ዲትሪች ለመጨረሻ ግዜ የታየችው እ.ኤ. አ. ጁላይ 10 2014 (ባለፈው አመት) ነበር። የሶስት ልጆች እናት የነበረች የዚህች ኢትዮጵያዊት በድንገት መሰወር ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል። ለአመት የጠፋችው ይህች ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሴት በህይወት እንደማትኖር በርካቶች ቢጠረጥሩም፣ ማንንም ሳታማክር በድብቅ ወደ ሃገርዋ ገብታለች የሚሉ አልጠፉም። አለም አቀፍ ፖሊስ በአለም ዙርያ ፍለጋውን ተያያዘው። በካናዳ ኪችነር ከተማ ቫንኮቨር ድራይቭ የተገኘው አጽም ግን የሁሉንም እንቆቅልሽ ፈታው። ሰብለ ህይወትዋ አልፏል። የሶስት ልጆችዋ አባት የነበረው ጀርመናዊው ስቴፋን ዲትሪች ገድሎ እዚያው መኖርያ ቤታቸው እንደቀበራት ፖሊስ ጠቁሟል። በፖሊስ እና በሰለጠኑ ውሾች ጥቆማ የተገኘው የሰብለ አስከሬን በቶሮንቶ ኮርነርስ ኮምፕለክስ ለጥናት ተልኮ የተገኘው ውጤት ሰብለ … [Read more...] about ጀርመናዊው የገደላት ሰብለ ከአንድ አመት በኋላ በመኖርያ ቤትዋ ተቀብራ ተገኘች
ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር
ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል። አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጸመው አለምሰት ሙጬ በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ለህክምና ወደ ኬንያ እየተጓዘች ባለችበት አውሮፕላን ነው። አውሮፕላኑ ዞሮ ከተመለሰ በኋላም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በደህንነቶች ተይዞ ከአውሮፕላኑ እንዲወጣ ተደርጓል። የህወሃት የደህንነት አባላት የቴዲ አፍሮን ፓስፖርት ቀምተው አሰናብተውት … [Read more...] about ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር
ወዴት እየሄድን ነው?
ዛሬ፣ የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ፣/ መኖሯን የማይሹ፣/ ከቻሉም የየራሳቸውን የጎጥ መንግስታት ለማቋቋም የሚፈልጉ ኃይሎች አጋጣሚው እስከሚፈጠርላቸው እየጠበቁ ነው። ዛሬ ኢህአዴግ በሚከተለው ፖሊሲ ኢትዮጵያ ለክፋ አደጋ እየተጋለጠች ነው። ዛሬ፣ በዘር የተደራጁ ኃይሎች አመቺ አጋጣሚ እየጠበቁ ናቸው። ዛሬ እነ አይሲስና መሰል ኃይሎች ምን እንዳዘጋጁልን አናውቅም። አርፈው እንደማይተኙ ግን የተረጋገጠ ነው። እናም/ ኢትዮጵያዊው ባለቅኔና ደራሲ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ በኢጣሊያን ወረራ ዘመን የቋጯትን ስንኝ ጠቅሼ፣/ ያለፈውን መሰረት ያደረገ፣/ የዛሬውን የሚመለከተውንና ስለነገው የሚጠቁመውን ንግግሬን እጀምራለሁ። አገሬ ተባብራ ካልረገጠች እርካብ፣ ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ፣/ የእንቧይ ካብ፣ ብለዋል። ከ40 አመት በፊት የተጀመረው የለወጥ እንቅስቃሴ ዛሬም ዕልባት … [Read more...] about ወዴት እየሄድን ነው?
ኢትዮጵያ ከ184 አገራት 171ኛዋ ደሃ አገር!
ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የአምስት ዓመታት አኻዝ ያካተተ የዓለማችንን ሃብታምና ደሃ አገራት ዝርዝር ሰሞኑን አውጥቷል፡፡ የዓለም የፋይናንስ መጽሔት ላይ የታተመው ይኸው ዘገባ እንደሚያሳየው በሃብታምና ደሃ አገራት መካከል ያለው ልዩነት በእጅጉ እየጨመረ እንደመጣ ነው፡፡ በዚህ የአምስት ዓመት አኻዛዊ ዘገባ መሠረት ከ184 አገራት መካከል ኢትዮጵያ 171ኛ ተራ ላይ የምትገኝ ስትሆን ይህም በድህነት ከሚጠቀሱት ቀዳሚ አገራት ቁጥር ውስጥ አስገብቷታል፡፡ ዘገባውን የተመለከቱ የኢኮኖሚ ባለሙያ የአንድ አገር ኢኮኖሚ በከተሞች ውስጥ በሚሰራ ፎቅ ብዛት እና የመንገድ ሥራ አይለካም ይላሉ፡፡ ሌላ የኢኮኖሚ ባለሙያ ደግሞ “ኢኮኖሚ ከቁጥር ሌላ ሥነ ልቦናዊ ጉዳይም ነው፡፡ የኑሮ ጉዳይም ነው፡፡ የጉሮሮ ጉዳይም ነው፡፡ በቁጥር ብቻ አይለካም፡፡ … የሕንፃ መሐንዲስ ቢሳሳት ሕንፃ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ከ184 አገራት 171ኛዋ ደሃ አገር!
Journalists Released; Religious Leaders Convicted
SMNE Press Release Washington, DC, July 14, 2015 The Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) strongly condemns the recent verdict of the Ethiopian Federal High Court Fourth Criminal Bench concerning eighteen Ethiopians of Muslim faith who were found guilty on counts of attempted terrorism, conspiracy and incitement on July 6, 2015. Those convicted include six members of the Ethiopian Muslims Arbitration Committee, eight scholars, two journalists, one artist and one student. They had … [Read more...] about Journalists Released; Religious Leaders Convicted