Archives for June 2015

የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው

(ገለታው ዘለቀ)

በድርጅት ከዚያም ከፍ ብሎ በመንግስት ደረጃና በሃገር ደረጃ ግምገማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉ ያምናል። የኣንድ ድርጅት ብቃትም በግምገማው ችሎታና ጥራት ሊለካ ይችላል።የኣንድ ሃገር የፖለቲካ መረጋጋት በፖለቲካ ለሂቆቹ የጠራ የሃገር የምናብ ስእልና ብስለት ሊለካም ይችላል። የፖለቲካ ቤቶች ሲኮለኮሉ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ ከፍ ያለ ግምገማን ይጠይቃል። ሃገሪቱ ያለፈችበትን የህይወት ጎዳና፣ የገጠማትን ችግር መንስዔና ውጤቶች በሰፊው መገምገም ለሚመሰረቱ […]

Read More...

… አልሞት አለኝ

(ወለላዬ)

በስራው ላይ ልፈላሰፍ ቅኔ ልቀኝ ግጥም ልጽፍ ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ የማደንቀው ሰው ነበረኝ ሳይሞትማ ሳይቀበር ስሙን ማንሳት እሱን ማክበር መስሎ ታይቶኝ ልምድን መስበር የማደንቀው ሰው እያለኝ ልጽፍለት ተቸገርኩኝ አቤት! ዕውቀት አይ! ቁመና ብልህ ደፋር ቆራጥ ጀግና ሀይማኖቱን አጠንካሪ ደግ ለጋስ ሰው አክባሪ ብዬ ልለው ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ ታሞ እያየሁ ዛሬ ቢያጣ ዛሬ ቢርበው በቁም ሆኖ […]

Read More...

የነፃነት መውጫው መንገድ፣ ታጋዩ፣ ሕዝቡን ጠንካራ ምሽጉ ማድረግ ሲችል ነው

የአንድ ለነፃነት የሚታገል ኃይል የመጀመሪያ ተግባሩ፣ ጠንካራ ምሽግ መገንባት ነው። ምሽግ ሲባልም መሬትን ጎርዶ ራስን መቅበር፣ ወይም ደግሞ በኮንክሪት መከታ እና ጠለላ ገንብቶ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወነጨፉ አውዳሚ የጦር መሣሪያ አረሮችን መከላከል አይደለም። ጠንካራ ምሽግ ሲባል፣ ታጋዩ ኃይል ነፃ አወጣዋለሁ የሚለውን ሕዝብ፣ ዓላማውን አሳውቆ፣ አሳምኖ እና አደራጅቶ የታጋዩ ኃይል የቀለብ፣ የመረጃ እና የሰው ኃይል ምንጭ ማድረግ […]

Read More...

“ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ይጋቡ” ጠቅላይ ፍርድቤት

የፈጣሪን ሥርዓት “ምድራዊ ፍርድቤት መለወጥ አይችልም”

* “ፍቅር ፍቅር ነው” ኦባማ ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ጋር ጋብቻ መፈጸም ይችላሉ፤ ለእነርሱ የጋብቻ ሠርቲፊኬት መከልከል ሕገመንግሥቱን ይጥሳል በማለት የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መጋባት እንደሚችሉ ወሰነ፡፡ ለጋብቻ ቅድስናና ክቡርነት የሚከራከሩ “የእግዚአብሔርን ሕግ ምድራዊ ፍርድ ቤት ይህን መለወጥ አይችልም” በማለት ውሳኔውን አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡ በምንም መልኩ ይገለጽ ፍቅር ፍቅር ነው በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ […]

Read More...

አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ

“የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል” አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም […]

Read More...

“የአማራ ክልል ዳኞች አቤቱታ”

ከአዘጋጆቹ፡- ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፌስቡክ ወዳጃችን “የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን” በማለት በውስጥ መስመራችን የላኩልንን ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ ጋዜጠኝነት “ወንጀል” በሆነባት ኢህአዴግ በሚገዛት አገራችን በስም የተጠቀሱትን ሹመኛ ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማረጋገጥ አንችልም፡፡ ሆኖም ግን መረጃው ስህተት ነው የሚል የኢህአዴግ አካል ምላሽ ከሰጠን ለሕዝብ እናቀርባለን፡፡ “የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን”!!!!! ደመወዝና ጥቅማጥቅም ስላነሰን ከእነ ልጆቻችን ተራብን፣ ተጠማን፣ […]

Read More...

“አንዳርጋቸው የነጻነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም”

የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች ታግተው ለዘረኛውና አፋኙ የወያኔ ቡድን ተላልፈው የተሰጡበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ደረጃ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በጁን 23/ 2015 በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት እልህና ቁጭት የተሞላበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። በሰልፉ ላይ ከተለያዩ […]

Read More...

ከገዥው ወገን የምንለይበት

እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለትግሬዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦሮሞዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአማራዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሶማሌዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአፋሮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦጋዴኖች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአኙዋኮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሲዳማዎች ጥብቅና […]

Read More...

“ደብረማርቆስና ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ልታደርጉ ነው የምትሄዱት” ፖሊስ

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ከሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ

• ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ለሌላ ለቅሶ በመሄድ ላይ የነበሩ ዜጎች ተደብድበው ተመልሰዋል የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አወቀ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው […]

Read More...

“ከ10 ሌባ መሀል አንተ ንጹህ ሆነህ ሙስናን መታገል አትችልም” የፍትህ መምሪያ ሀላፊ

“ህገ መንግስቱ አያድንህም፣ አንተን ማስደፋት ቀላል ነው”

* “ግድያው ከሟች የፖለቲካ አቋም ጋር የሚገናኝ አይደለም፤ የመንግስትም እጅ የለበትም” ህወሃት/ብአዴን/ኢህአዴግ * “ለሞት ያበቃቸው ክስተት ግን ግለሰባዊ ግጭት” የህወሃት/ብአዴን ሹመኛ * “የሰማያዊ ፓርቲ አባልነትህን የማታቋርጥ ከሆነ አንተን ማስደፋት ቀላል ነው!” የደብር ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ * “የሰማያዊ ፓርቲ አባልነቴን አንተ አታስቆመኝም፡፡ አገሬም ኢትዮጵያ ነው! ከኢህአዴግ ጋር ስታገልም ይህን ሁሉ አውቃለሁ፡፡ የፈለግከውን ማድረግ […]

Read More...