እንደ ዶክተር ጌታቸው በጋሻው አባባል ጤንነታቸው ከታወኩት ውስጥ ልደባለቅ እንጂ ከምዬ ኢትዮጵያ አንፃር ዛሬም ወያኔና ሻቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው። እብድ ልባል እንጂ ሁለቱም የኢትዮጵያ ሕዝብና ሀገር ላይ የተጫወቱና እየተጫወቱ ያሉ ናቸው። ወያኔን ቤተመንግስት ደጃፍ ድረስ ሸኝቶ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ የሰጠን ሻቢያ ገና “77 ዓመት ይቀረዋል”። ኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜት ከቶም እንዳያንሰራራ የሻቢያን የቤት ሥራ እያከናወነ ያለው ወያኔ ቢንገዳገድ ቀሪውን የሚቀጥል እየተዘጋጀልንና እየተደገሰልን ነው። አዎ ሻቢያን በኤርትራ፣ ወያኔን በኢትዮጵያ ለሥልጣን ያበቃቸው ከጋለባቸው ጋር እየተጋለቡ፣ ዛሬ ያሉትን ነገ እየካዱ፣ ትላንት የጣሉትን ዛሬ እያነሱ፣ ዛሬ ያቀፉትን ነገ እያረዱ፣ ሀገር ኢትዮጵያን እንዳሻቸው ሊጋልቡ፤ ሊታመን ከሚገባው በላይና ያለ ይሉኝታ እየተገለባበጡ … [Read more...] about ዝናብ አይፈሬ ታጋዮች
Archives for May 2015
“አልመች አለው ጎኔ!”
ጥበብ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ስሜት የሚገለጽባቸው ቀዳሚው እያዝናና የሚያስተምር ዘርፍ ቢሆንም አሁን አሁን ግን ያ እየሆነ አይታይም። የማፍር፣ የምኮራባቸው ጥበበኞች ጉዳይ አሁን አሁን ያሳስበኝ ይዟል ... እናም የጎልማሳው አቀንቃኝ የጃኪ "አልመች አለው ጎኔ!" ጣዕመ ዜማ ውስጥ ስሜቴን ቢነካካው፣ የማፍር የምኮራባቸው፣ ጥበበኞች ... ብየ ጀመርኩት! የጥበብ ሰዎች በግል እንደ ተራ ዜጋ የፈቀዱትን ፖለቲካ አቋም የመያዝ መብታቸውን የማከብር ቢሆንም ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ከእውነተኛ የህዝብ መብት ጥያቄና ስሜት ሳይሆን ለሆዳቸው ሲያድሩ ማስተዋል ስሜትን ይጎዳል። በተለይም ደግሞ የጥበብ ሰዎች ለሆዳቸው አድረው ከገዥ አንባገነኖች ጋር ወግነው የህዝብ ድምጽ ሳይሆን የፖለቲካ ፖርቲዎች ቱልቱላ ሲሆኑ ማየት ያማል። ያለመታደል ሆኖ በእኛ ኢትዮጵያ ከጥቂት የጥበብ ሰዎች በስተቀር … [Read more...] about “አልመች አለው ጎኔ!”
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬
የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ "እኚህ ሰው ማናቸው?" በሚል ርዕስ ግሩም ዝግጅት ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። ይህንን ዝግጅት በጥያቄና በግጥም መልክ የሚያቀርቡት እንደመሆኑ ምላሹም በግጥም እንዲሆን አንባቢያንን እርሳቸውም እኛም እናደፋፍራለን። ወለላዬ ከተለያዩ የግልና መሰል የህይወት ውጣውረዶች በኋላ አሁን ዝግጅታቸውን እንደገና ጀምረዋል። ጎልጉልም በደስታ እንኳን ደህና መጡ ይላቸዋል። የመጨረሻው "እኚህ ሰው ማናቸው?" ፲፫ኛው ነበር የዚያን መልስ ከአዲሱ ጥያቄ ጋር አቅርበናል። ወዳጃችን ወለላዬ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ ምስጋናችን ይድረስዎ። ከዚህ በፊት ኮሎኔል ታምራት ይገዙን አቅርቤ መልስ ሳልሰጥ አቋርጨ ነበር። አሁን ከመልሱ ጋር አዲስ ልኪያለሁ መልስ ይዘን የቀረብነው ምስላቸውን በፊት ይባሉ ነበረ ኮሎኔል ታምራት ኮሎኔል ታምራት ታምራት … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬
እውነቱ ይውጣ!
ሴቶችን በወንዶች ፊት፣ ወንዶችን በሴቶች ፊት ልብስ እያስወለቁ የአካላቸውን ክፍሎች ሁሉ ለማየት የሚያስችል እንቅስቃሴ አንዲሠሩ ማስገደድ በሽተኞችን ያስደስታል፤ የምርመራ ዘዴ ግን አይደለም፤ ውርደት እንዲሰማቸው ከሆነ በወራዶች ሰዎች ፊት የምን መዋረድ አለ? ወራዶች እነሱ ደረጃ ላይ ከእነሱ ጋር ያስተካክላሉ አንጂ አያዋርዱም፤ በሌላ አነጋገር ወራዶች አያዋርዱም፤ ወራዶቹ ደንቆሮዎችም ሆነው ነው እንጂ ልብስ የሚያስወልቁ እነሱ ብቻ አይደሉም፤ ሀኪሞችም ልብስ አስወልቀው፣ አጋድመው በጣታቸውም ሆነ በመሣሪያ የፈለጉትን የአካል ክፍል አንደፈለጉ ያደርጉታል፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ከሚያደርጉት የሀኪሞቹ የሚለየው ሀኪሞቹ ሰዎችን ለማዳን ሲሉ ነው፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ግን የራሳቸውን ሱስ ለማርካት፣ የራሳቸውን ህመም ለማስታገስ ነው፤ ወራዶቹንና ደንቆሮዎቹን ከመለዮአቸው አራቁቻቸዋለሁ! ከነውር … [Read more...] about እውነቱ ይውጣ!
ከጩኸት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ?
የውጭ ጠላቶቻችንና የውስጥ ገዢዎቻችን በአንድ ድምጽ የሚሰሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ አይተናል። በጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ማተኮሩን እንተወው፤ አስጠቅቶናል፤ አሳፍሮናል፤ አድክሞናል። በገፍ ለሚሰደደውና ለሚዋረደው ብዙ ሚሊየን ወጣት ትውልድ እንደምናስብ አምናለሁ። እምነት፤ ጩኸት፤ ፀሎት አስፈላጊ ቢሆኑም አንገት ቆራጭ ሽብርተኞችን አይከላከሉም። አፋኝ፤ አግላይና ራሱን አገልጋይ የሆነ የመንግሥት ስርዓትን አይለውጡም። ሁለቱንም አብሮና ተባብሮ ለመለወጥ ይቻላል የሚል እምነት አለኝ [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ]። … [Read more...] about ከጩኸት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ?