Archives for May 2015

መሸነፍን በአሸናፊነት የተቀበሉ መሪዎች

“ሕዝብን መታዘዝ ይገባል!”

በቅርቡ በሥልጣን ላይ እያሉ በምርጫ መሸነፋቸውን ባመኑበት ጊዜ ሥልጣናቸውን ያስረከቡት የናይጄሪያው ጉድላክ ዮናታን በአፍሪካ የ65 ዓመታት የምርጫ ዴሞክራሲ ጉዞ ከሚጠቀሱ ጥቂቶች መካከል አንዱ ሆነው ሰንብተዋል፡፡ ይህም ተግባራቸው በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ታላቅ ሥፍራ የሚሰጣቸው የፖለቲካ ሰው አድርጓቸዋል፡፡ በአፍሪካ በተካሄዱ በርካታ ምርጫዎች የሕዝብን ድምጽ በማክበር ሥልጣናቸውን ለተቀናቃኛቸው በማስረከብ የሕዝባቸውን ድምጽ ያከበሩ መሪዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ […]

Read More...

የመሪዎች እምባ

ከስም ልጀምር፣ የዛሬ ወጣቶች በተለይ ዘፋኞች ስማቸው በመጠኑ ተቆርጦ ወይም አንሶ ሲጠሩ እየሰማን ነው፤ ቴዎድሮስ – ቴዲ ብዙ ባያስከፋም ተያይዘው የቀጠሉት ዘፋኞች ግን እስከ አባታቸው ስለሚያሳንሱት ኢትጵያዊ ስም መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ የሆነብኝ ጊዜ አለ። እስቲ አሁን ጃህ ሉድ አጥሮ ነው ወይስ ተቆርጦ ቻቺ፣ ጃኪ፣ ጂጂ፣ አቢ፣ ኢሚ፣ ዮሲ፣ ጃኪ-ጎሲ፣ ሚሊ፣ ሚኪ፣ ዮኒ፣ … ልተዋቸው። እንደውነቱ […]

Read More...

“ለመተማመን እንነጋገር”

በጀርመን የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ

በጀርመን የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ ሜይ 2 ቀን 2015 ዓመተ-ምህረት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በአካሄደ እለት እውቁ የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት አቀንቃኝና ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መስራችና መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና እውቁ የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝና አሰባሳቢ ማንነት በአንድነት መጽሀፍ ደራሲ አቶ የሱፍ ሃሰን በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። ስብሰባው በቅርብ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ባሰቃቂ ሁኔታ ለተሰዉት […]

Read More...

“ጸርሁ በዓቢይ ቃል”

የታረዱት ነፍሳት ጩኸት

“ርኢኩ ታህተ ምስዋዕ ነፍሶሙ ለእለ ተቀትሉ በእንተ ቃለ እግዚአብሔር ወበእንተ ዘአቀቡ ህጎ። ወጸርሁ በቃል ዓቢይ ወይቤሉ እስከ ማእዜኑ እግዚኦ ቅድስ ወጻድቅ፤ ኢትትቤቀሎሙኑ ወኢትኴንኖሙኑ በእንተ ደምነ እምእለ ይነብሩ ዲበ ምድር” “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” እያሉ ከመሰዊያ በታች ሆነው የታረዱት ነፍሳት በታላቅ ድምጽ ሲጮኹ አየኌቸው (ራዕ 6፡9-10)። […]

Read More...

በየመን የሚታየው ምስቅልቅል እየሰፋ ስለመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጥረት ምን ያስተምረናል?

(አክሊሉ ወንድአፈረው)

በተለያዩ ሀገሮች የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ያለፉባቸውን ጥምዝምዞች፣ የገጠማቸውን ደጋፊና አደናቃፊ ሂደቶች መመርመር ባንድ ሀገር ውስጥ ለሚካሄደው ትግል ታላቅ ጠቀሜታ አለው። በዚህ አንጻር በ2011 የአረብ ስፕሪንግ ካምባገነናዊ ስርአት ወደ ዴሞክርሲ ልትሸጋገር ነው ተብላ ተስፋ የተጣለባት የመን፣ እነሆ ዛሬ በእርስ በርስ ጦርነት ተናውጣ እንኳንስ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ልትሸጋገር ከራሷም አልፋ አካባቢውን ለማመስ የቻለ ሁኔታ ውስጥ ገብታለች። ይህ እንዴት […]

Read More...

እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭

(ወለላዬ)

ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አራት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ የወልደጊዮርጊስ ቢታይ ምስላቸው ሁሉም ሰው አወቀ እስከታሪካቸው እንደዚህ በሥራው ያገኘ ሰው ሞገስ ምንግዜም ይኖራል በጥሩ […]

Read More...

የመጨረሻው ደወል !

(አሥራደው ከፈረንሳይ)

ኳ! ኳ! ኳ! ይላል፤ በማርያም ደጃፍ – በገብርኤል፤ በጎርጊስ ደጅ – በሩፋኤል፤ በጨርቆስ ደጃፍ – በአማኑኤል፤ በተክልዬ – በሚካኤል፤ ኳ! ኳ! ኳ! እያለ፤ የመጨረሻው ደወል ተደወለ፤ አትንበርከክ በቃ ! ቆመህ የጴጥሮስን ሞት ሙት አለ:: (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Read More...

እረኛ የሌለው ከብት እና መሪ የሌለው ሕዝብ አንድ ናቸው

ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ የደረሱባቸው ከፍተኛ ሰቆቃዎች አሉ። አምና በሣዑዲ ዓረቢያ፣ ባለፉት ሁለት ወራት ደግሞ በየመን በሚኖሩ የዕለት እንጀራ ፈላጊ በሆኑ በመቶ-ሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተጸፈመባቸው ግፍ የተሞላበት ግድያ እና ስቃይ፣ መንስዔው ኢትዮጵያ መሪ አልባ አገር በመሆኗ ነው። የደረሰው ሳይበቃ፣ በዚህ ምክንያትም ኢትዮጵያውያን ከደረሰብን መከራ ሳናገግም፣ ስቃዩ እና […]

Read More...

በመጨረሻም በግብጽ ነጻ ወጡ . . .

እኛ ግን መንግስት አለን እንዴ?

* ሕንጻና መንገድንማ ቅኝ ገዥዎችም ሰርተዋል የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊብያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን።  እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በእንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት። መቼም ሼም የሚባል ነገር ከነሱ […]

Read More...

ምርጫው አዲስ “ጠቅላይ ሚ/ር” አግኝቷል

“የተለቀቁት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እናጣራለን?” ኢህአዴግ

በሊቢያ ታፍነው የነበሩ ወደ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል ነጻ አውጪነት መለቀቃቸውን የግብጽ መንግሥት አስታወቀ፡፡ የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲ የተለቀቁትን ኢትዮጵያውያን አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመገኘት አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ ኢህአዴግ እንደተለመደው “የተለቀቁት ኢትዮጵውያን መሆናቸውን አጣራለሁ” እንደማይል ተገምቷል፡፡ “ተይዘን የነበረው በሊቢያ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ነበር” ከተለቀቁት አንዱ ኢትዮጵያዊ፡፡ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን ሐሙስ በተሰራጨው የዜና መረጃ መሠረት በሊቢያ ደርና […]

Read More...