ጸሃይ አዘቅዝቃ ስትገባ ከቤቷ ጨለማ ሲተካ ደሞ በሷ ቦታ አካባቢው ሁሉ ፀጥ ረጭ ብሎ ከሁከት ጫጫታ ዝምታው አይሎ የነገሰ እለት ያኔ ነው ማዳምጥ የዉስጠትን ጩኸት ፈልጎ ለማግኘት የጠፋን ማንነት፡፡ **** ዉብአለም ታደሰ ፤ 14-02-2007 … [Read more...] about ራስን ፍለጋ
Archives for January 2015
“ሕዝብን ለማውደም ውጤታማው መንገድ ታሪካቸውን የሚረዱበትን መንገድ ማስካድና ጨርሶውኑ መደምሰስ ነው”
“ሕዝብን ለማውደም ውጤታማው መንገድ ሰዎች ታሪካቸውን የሚረዱበትን መንገድ ማስካድና ጨርሶውኑ በመደምሰስ ነው” የሚለው የእንስሶች እርሻ ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ብሒል ሰሞኑን ከፍተኛ መነጋሪያ ሆኗል፡፡ ለዚሁም መነሻው በየተራ እንዲወድሙ ከተደረጉት የሕዝብ የማንነት መገለጫዎች መካከል አንደኛ ቅርስ የሆነው የጣይቱ ሆቴል መውደምን ተከትሎ ነው፡፡ የእንስሶች እርሻ መጽሐፍ ህወሃት በተሰነጠቀበት ወቅት የእነ መለስ መገለጫ ነው ተብሎ በስፋት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲነበብ የነበረ መጽሐፍ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የውኅዳኑ ደጋፊ ሪፖርተርም በየሳምንቱ እየተረጎመ ያቀርበው እንደነበር ጋዜጣው ምስክር ነው፡፡ ጋሼ ጳውሎስ ኞኞ በጻፈው “አጤ ምኒልክ” መፅሐፍ ገጽ 328-330 የሆቴሉ ታሪክ እንዲህ ይነበባል፡፡ በአዲስ አበባ የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ተሠርታ በምትመረቅበት ጊዜ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ … [Read more...] about “ሕዝብን ለማውደም ውጤታማው መንገድ ታሪካቸውን የሚረዱበትን መንገድ ማስካድና ጨርሶውኑ መደምሰስ ነው”
ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸውን ታስረው ጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተገለጸ
የቀድሞው የጋንቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸው ታስሮ ጨለማ ክፍል መታሰራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አቶ ኦኬሎ ቂሊንጦ በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚታወስ ሲሆን ከሰሞኑ የርሃብ አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ በእስር በሚገኙበት እስር ቤት እጅና እግራቸውን ታስረው ብቻቸውን ጨለማ ክፍል እንዲገቡ እንደተደረጉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ቂሊጦ ማረሚያ ቤት እስረኞችን ሊጠይቁ ሄደው እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ እዚያው በእስር ላይ ካሉ ሰዎች አቶ ኦኬሎ ያሉበትን ሁኔታ መረዳታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል የ18 አመት እስር ፍርደኛው ታዋቂው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ ውጭ ሌላ ሰው መጠየቅ እንደተከለከለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ) … [Read more...] about ኦኬሎ አኳይ እጅና እግራቸውን ታስረው ጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተገለጸ
South Africa’s Democratic Transition and Transformation from 1994-2014
Title: South Africa’s Democratic Transition and Transformation from 1994-2014: What Difference Has It Made to date?[1] By Mammo Muchie[2] December 31, 2014 Inspiration “Africa without South Africa can be like a ship without a captain; South Africa without the rest of Africa can be like a ship without a compass.” Mammo Muchie I. South Africa 20 years after Apartheid? As 2014 passes and 2015 comes, the twenty years of South African democracy is also entering the next twenty years and … [Read more...] about South Africa’s Democratic Transition and Transformation from 1994-2014
“ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም” – ኢህአዴግ
በተለይ ምርጫ ሲደርስ ቀለማዊ ነክ ነገሮችን በጣም የሚያስፈራው ህወሃት/ኢህአዴግ በመጪው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ሰማያዊ ቀለም እንዳይታይ መከልከል መጀመሩ ተዘግቧል፡፡ የደኅንነትና የፖሊስ አባላቱን በማሰማራት በግልጽ ማስጠንቀቂያ እየሰጠ ያለው ኢህአዴግ ለዘመናት በቆየው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የጨመረው ባለ ሰማያዊ መደብ ኮከብ በበዓሉ ላይ እንዳይታይ አብሮ ካልከለከለ በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማነት የሰየመውን የኢህአዴግ ዓርማ መቀየር አለበት በማለት አንዳንዶች ተሳልቀዋል፡፡ በሰማያዊ መደብ ቢጫ ኮከብ ያለውን የኢህአዴግ ዓርማ በቲሸርት በማሰራት “ለኢህአዴግዬ ያልሆነ … ይበጣጠስ” በማለት “አምረውና ደምቀው” በበዓሉ ለመታየት ያሰቡ ካድሬዎቹና አፈቀላጤዎቹም በዚህ ጉዳይ ላይ አመራር ካልተሰጣቸው “ከኑግ የተገኘ …” የመሆን ዕጣ እንዳይደርሳቸው “ያስፈራል” ተብሏል፡፡ ጉዳዩ … [Read more...] about “ጥምቅት በዓል ላይ ሰማያዊ ቲሸርት መልበስ አይቻልም” – ኢህአዴግ
የምርጫ 2007 10ቱ ቃላት
የዚህ ጽሑፍ ግብ በምርጫ 2007 ቁም ነገር መስራት የሚፈልግ የምርጫ ፓርቲ ማድረግ ከሚገቡት ሌሎች እጅግ በርካታ ዝግጅቶች በተጨማሪ ከግንዛቤ ሊያስገባቸው የሚገቡ 10 ነጥቦች መዘርዘር ነው። ምርጫው ነፃ እና ፍትሃዊ ካልሆነ ከምርጫ መወጣት (ቦይኮት ማድረግ) ጠቃሚ ነው ለሚሉ ወገኖችም መልስ ይሰጣል ይኽ ጽሑፍ። መልካም ንባብ። (1) መንግስት በስልጣን መኖር የሚችለው፥ (ሀ) ህጋዊነት የሚለግሰው ህዝብ ሲኖር፣ (ለ) ህዝብ የሙያ ትብብር ሲለግስ፣ (ሐ) ህዝብ የግብር ክፍያ ትብብር ሲያደርግ፣ (መ) የመንግስትን የአገር ተፈጥሮ ሃብት እና አገራዊ ኢኮኖሚ ባለቤትነት ህዝብ እሺ ሲል ብቻ ነው። እነዚህን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ህዝብ አሳልፎ ለገዢው ቡድን አሳልፎ የሰጠው በፍራቻ ወይንም በፈቃደኛነት ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ የእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤት ህዝብ … [Read more...] about የምርጫ 2007 10ቱ ቃላት
“ከኢህአዴግ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እፈልጋለሁ” መድረክ
የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች እንዳሉት የገለፀው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ በጉዳዩ ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡ መድረኩ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች አመራረጥና በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ከመንግስት በሚሰጠው የድጐማ ገንዘብ ክፍፍል ላይ ቅሬታ እንዳለው ጠቁሟል፡፡ ምርጫውን ለማስፈፀምና ለመታዘብ ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ገለልተኛ የሆኑ ሠዎች መመረጥ ያለባቸው ቢሆንም በቅርቡ የተመረጡት አስፈፃሚዎች አብዛኞቹ የገዥው ፓርቲ አባላት መሆናቸው እየታወቀ “የማንም ፓርቲ አባላት አይደለንም” እያሉ ፈርመው ወደ አስፈፃሚነቱ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ሲል ፓርቲው ቅሬታውን ገልጿል፡፡ መንግስት ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጐማ በተመለከተም ገንዘቡ ለሚመለከታቸው ፓርቲዎች ብቻ … [Read more...] about “ከኢህአዴግ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እፈልጋለሁ” መድረክ
ትንሽ ምስክርነት ስለ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)
ከመሰንበቻዉ መረራ ጉዲና ከ25 ዓመታት በላይ ካስተማረበት ዩኒቨርሲቲ ተባረረ የሚለዉ አስገራሚና አስደንጋጭ ወሬ ከተዛመተ በኋላ አነጋጋሪነቱ ሞቅ ብሏል፡፡ (በጨዋታችን ላይ የማከብረዉ መምህሬ ስለሆነ አንተ እያልኩ ነዉ የምጠራዉ … እሱም ቢሆን አንቱታዉን ብዙም የሚፈለገዉ አይደለም … አዉቃለሁ)፡፡ በይፋ ከዩኒቨርሲቲዉ መሰናበቱን የሚያስረዳ ደብዳቤ እንደረሰዉ ባይገልጥም ነገሩ እሳት ካየዉ … ነዉ እና የምናዝን እናዝናለን፡፡ ዶ/ር መረራን ሳዉቀዉ ለመጀመሪያ ጊዜ መረራ የሚባል ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ … በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ጎልቶ መዉጣት የጀመረዉ ይመስለኛል በ1992 ብሔራዊ ምርጫ ወቅት ነዉ፡፡ በዚያን ጊዜ የደመቀ ባይሆንም ጥቂት ፖለቲከኞች ገዢዉን ፓርቲ ሲሞገቱ የሚያሳይ የቅድመ ምርጫ ክርክር በቴሌቪዥን ይለቀለቅ ነበር፡፡ ያኔ ታድያ የብዙዎችን ቀልብ የሳበዉ በእኩልነት … [Read more...] about ትንሽ ምስክርነት ስለ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)
ከሸአቢያ መልካም ነገርን ከኩርንችት የወይን ፍሬን ማግኘት ይቻል ይሆን?
ኢትዮጵያ ሆይ! አሁንስ ተስፋሽ ማን ነው እግዚአብሔር አይደለምን? መቸስ በጣም ይገርማል! ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ መከራችን ሊያልቅ ነው ስንል ገና መጀመሩ ነው እንዴ ጃል? ጉድ እኮ ነው! የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ለመሆኑ ከዚህ በላይ ሌላ የመከራ ዘመናት መሸከም የሚችል ትከሻ አለህን? የአርበኞች ግንባር ግንቦት 7 ሌሎችም በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ኃይሎች ውሕደት ሊፈጽሙ እንደሆነ ካስታወቁ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ደርሶ በይፋ ለሕዝብ ከማስታወቃቸው በፊትም ከዚህ መግባባት ላይ ለመድረስ አጭር የማይባል ጊዜ እንደወሰደ መገመት ይቻላል፡፡ ይሄም ሆኖ “ታጋይ ኃይሎቹ ሊዋሐዱ እንደሆነ ካስታወቁ በኋላ ግን ዓላማቸው ያን ያህል ግልጽና ተጣጣሚ የሚፈልጉትም ከሆነ ምን አንጓተተው?” የሚለው ጥያቄ ከብዙዎች የሚነሣ ጥያቄ ነበረ፡፡ አሁን ግን የዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልጽ እየሆነ … [Read more...] about ከሸአቢያ መልካም ነገርን ከኩርንችት የወይን ፍሬን ማግኘት ይቻል ይሆን?
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ ነው ወይስ የኋሊት ጉዞ እያሳየ ነው?
ዶ/ር ዳንኤል ተፈራና ዶ/ር ፀሀይ ለኢሳት ጋዜጠኛ ለአቶ ፋሲል የኔ ዓለም ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሰጧቸው መልሶች የቀረበ አስተያየት ከፈቃዱ በቀለ መግቢያ በቅርቡ ሁለት በአሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚስቶችን የኢሳት የቴሊቪዝን ጋዜጠኛ የሆነው አቶ ፋሲል የኔ ዓለም ኢትዮጵያ ከውጭ የምትበደረው ብድር መጠን እያደገ ስለመምጣቱና ስለኢኮኖሚው አጠቃላይ ሁኔታ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በመጋበዝ በመሰላቸውና በሚታያቸው፣ እንዲሁም ከተማሩት የኢኮኖሚ ትምህርት አንፃርና ከዕምነታቸው በመነሳት ለተደረገላቸው ጥያቄ አስተያየት ለመስጠት ሞክረዋል። ፕሮፊሰር ዳንኤል ዕዳንንም ሆነ፣ የሚሰሩትን ፕሮጅክቶች ወደ ፊት ሊገኝ ከሚችለው ውጤትና አትኩሮ ቅድሚያ መስጠት የሚገባውን፣ ነገር ግን የሚታለፈው አንገብጋቤ ጥያቄ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ውጤት በንጽጽር … [Read more...] about የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ ነው ወይስ የኋሊት ጉዞ እያሳየ ነው?