ከአዘጋጆቹ፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው “ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?” በሚል ርዕስ ለጻፉት ሥርዓት ጠብቆ ምላሽ የሚሰጡ ተቀብለን እናትማለን ባልነው መሠረት ኢብኑ ሙነወር “መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው” በሚል ርዕስ ጨዋነት በተሞላበት አጻጻፍ የላኩልንን ምላሽ ከዚህ በታች አትመናል፤ ምስጋናችንንም እናቀርብላቸዋለን፡፡ ሌላ አዲስ አጀንዳ እስካልመጣ ድረስ በዚሁ ይህንን ውይይት የቋጨን በመሆኑ ምላሽ ጽሁፎችን የማንቀበል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ ጉዳዩን መቀጠል የሚፈልጉ ከጸሐፊዎቹ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋውና ኢብኑ ሙነወር ጋር በኢሜይል ወይም በፌስቡክ ወይም በሌላ በሚያመቻቸው መንገድ በመገናኘት ሃሳባቸውን መላክ ይችላሉ፡፡ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መንግስት ለአመራሮቹ በሰጠው ስልጠና ላይ … [Read more...] about መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
Archives for October 2014
“አሸባሪ ብዕሮች”
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር "ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።" ነበር ያለው። አንባገነኖች ፕሬስን ይፈራሉ። ይጠላሉም። የህዝብ መሰረት የሌላቸው፤ በራሳቸው የማይተማመኑ ሁሉ ነጻ ሃሳብን ይጠላሉ። ነፍጥን ብቻ ተማምነው በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሚቀመጡ፤ እንደምን ነጻ አመለካከትን ሊቀበሉ ይችላሉ? ፍጹም አንባገነናዊነት በሰፈነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፤ ህግ አውጭው ህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ የለም። ይህንን ቁጥጥር በጥቂቱም ቢሆን ተክቶ ይሰራ የነበረው ነጻው ፕሬስ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝቡ መብቱን እንዲያውቅና መብቱንም እንዲያስከብር ብዙ ሰርቷል-ፕሬሱ። ሙስናን አጋልጧል፣ እንደ እንባ … [Read more...] about “አሸባሪ ብዕሮች”
ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?
ከአዘጋጆቹ ማሳሰቢያ፤ በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈረው ሃሳብ በከፊል ወይም በሙሉ የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣን አቋም የሚገልጽ አይደለም፡፡ እንደ ሚዲያ የማንንም ሃይማኖት በመንቀፍም ሆነ በመደገፍ አቋም አንይዝም፡፡ በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈረው ሃሳብ በሙሉ የጸሃፊው ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ነው፡፡ ጽሁፉን አስመልክቶ በጨዋነት ማስረጃዎችን በመጥቀስ ለመመለስ ለሚፈልጉ ሁሉ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል፡፡ አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኘው አገዛዝ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ከነሐሴ 18 እስከ መስከረም 16 ድረስ 800 ለሚሆኑ የመካከለኛ አመራሮቹ የፖሊሲና ስትራቴጂ ሥልጠና በሚሰጥበት ወቅት የእስላም ሴቶች በትምህርት ተቋማትና መንግሥታዊ በሥሪያ ቤቶች ሂጃብና ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ ሲጠየቁ “እኛ እንድናወልቅ የምንገደድ ከሆነ ክርስቲያኑም ማተቡን … [Read more...] about ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?
የእርቅና የመግባባት ሂደት መመዘኛዎች
በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ምእራፍ እንዲኖር መፍትኤው ምንድነው? ያልተሞከረው ብቸኛ መፍትኤ እርቅና መግባባት ነው። ለመሆኑ እርቅና መግባባትን እምቢ ባዩ ማን ይሆን? መንግስት ወይስ ተቃዋሚ? ወይስ ዝምተኛው አብዛኛው ሕዝብ? ወይስ ሁላችንም? ሁሉም ክሱን ትቶ ራሱን ይመርምር። ራሳችንን እንድንመረምርበት የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የእርቅና የመግባባት ሂደት መመዘኛዎች እንደ መንደርደሪያ አሳብ አድርገን እንውሰድ። ታዲያ በነዚህ ሚዛን ተመዝነን ቀለን እንዳንገኝ አምላክ የእሽታን መንፈስ ለሁላችንም ይስጠን። መንግስትን በተመለከተ 1ኛ/ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት ኢዮቤሊዩ (“Jubilee”) ማብሰር 2ኛ/ በፊታችን ያለውን ምርጫ ፍታዊ ማድረግ(በራስ መተማመንን ያሳያል) 3ኛ/ ተቃዋሚ የሚያቀርበውን መጥፎ አሳብ እያጋለጡ መልካም የሆነውን ግን በስራ ላይ ማዋል ተቃዋሚን … [Read more...] about የእርቅና የመግባባት ሂደት መመዘኛዎች
ኦባንግ ስለ ሁለተኛው የአፍሪካ መሬት ነጠቃ
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በሥራ ጉዳይ እንግሊዝ አገር ተገኝተው የነበሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሎንዶን የሚገኘው Minority Rights Group International ጽ/ቤት ባደረገላቸው ግብዣ ቃለምልልስ አድርገው ነበር፡፡ በቃለምልልሱ ወቅት ሁለተኛው የአፍሪካ የመሬት ነጠቃ እየተካሄደ እንደሆነ እና እንዲህ ዓይነቱ አስከፊ ተግባር እየተፈጸመ ያለው በእንግሊዝና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት ዕርዳታና ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ የአናሳ ቡድኖች መብት አይከበርም የሚባልበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ያለው እነዚህ ወገኖች መብት የሚባል ነገር እንደሌላቸው አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ እንደ ማስረጃም በጋምቤላ አካባቢ መሬታቸውን በግፍ እየተነጠቁ ለስደት፣ ለግዳጅ ሰፈራ፣ ይህንንም … [Read more...] about ኦባንግ ስለ ሁለተኛው የአፍሪካ መሬት ነጠቃ
ከወያኔ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሾልኮ የወጣ
ይህ ባለ 16 ገጽ ዘገባና ሰነድ ሲሆን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ከወያኔ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሾልኮ የወጣ
“በዓሉ ይመጣል ብዬ አሁንም በር በሩን አያለሁ”
በኢትዮጵያ ሥነ ፅሐፍ ውስጥ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠሩት ደራስያን መካከል አንዱ የሆነው ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ "ኦሮማይ" በሚል ርዕስ ባሳተመው መፅሐፉ ሳቢያ መስዋዕትነትን የከፈለ ደራሲ ነው፡፡ በአፃፃፍ ቴክኒኩ፤ በአጫጭር አርፍተ ነገሮቹና በድርሰት መዋቅሩ አዲስ የአፃፃፍ ብልሃትን አምጠቷል ተብሎ የሚታመነው ደራሲ በዓሉ ግርማ የካቲት 24 ቀን 1976 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ከቤቱ እንደወጣ የደረሰበት ያልታወቀ ደራሲ ነው፡፡ የበዓሉ መጨረሻ ከዓመት ዓመት ሲያነጋግርና የቆየና ያውቃሉ የሚባሉ ሰዎችን ምስክርነት እንደሻተ እነሆ 30 ዓመት ሞላው፡፡ ይህኑ መሰረት በማድረግ የሙያ አጋሩ ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ባለፉት ሁለት ተከታታይ እትሞች "የማይጮሁት በዓሉን የበሉ ጅቦች" የሚል መጣጥፉን በቁም ነገር መፅሔት ላይ አስነብቦናል፡፡ ይህንኑ መነሻ በማድረግ የበዓሉ ግርማን ባለቤት … [Read more...] about “በዓሉ ይመጣል ብዬ አሁንም በር በሩን አያለሁ”
ትግል ለምንና ለማን! ዓላማውስ ምንድነው? ትግል ሲባል ሳይንሳዊ ሊሆን ይችላል?
መግቢያ እንደምናየውና እንደምንከታተለው የዓለም ሁኔታ እጅግ እየተወሳሰበ መጥቷል። በተለይም የጥቢው አብዮት በመባል ከሶስትና ከአራት ዐመታት በፊት በሰሜን አፍሪካ በአንዳንድ አገሮች የተካሂዱት እንቅስቃሴዎችና የለውጥ ፍላጎቶች የመጨረሻ መጨረሻ የተጠበቀውን ውጤት አላመጡም። ከዛሬ ሶስት ዐመት ጀምሮ የፕሬዚደንት አሳድን መንግስት ለመጣል የተካሄደውና የሚካሄደው እልክ አስጨራሽ ትግል ለብዙ መቶ ሺህ ሰዎች መገደል፣ መሰደድና መንገላታት፣ እንዲሁም ለጥንታዊ የታሪክ ቦታዎች መውደም ምክንያት ሆኗል። የፕሬዚደንት ሳዳም መንግስት ከተደመሰሰና ፕሬዚደንቱም ከተገደሉ በኋላ ኢራክ የሱኒቶችና የሺኢቶች መፋለሚያ በመሆን እስካሁን ድረስ ወደ ስድስት መቶ ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ሞቷል። ያን የመሰለ ጥንታዊ የታሪክ አገርና በዘይት ሀብት የተገነባ አገር አሁን ህዝቡ በድህነት የሚማቅቅበት፣ በበሽታ … [Read more...] about ትግል ለምንና ለማን! ዓላማውስ ምንድነው? ትግል ሲባል ሳይንሳዊ ሊሆን ይችላል?
“ትግሬ ትጠላለህ”
. . . ነፍሱን አይማርና! ያ! ቀጣፊ ከንቱ - የሂትለሩ ጉብልስ፣ አሳልፎ ሄደ፤ መሰሪ ትምህርቱን - ለበረከትና...ለነ አቶ ሽመልስ፤ እነሱም በተራ፣ ለታችኛው አሽከር ነጭ ውሸቱን ዘርተው፣ አጨዱት. . .፣ ከመሩት. . .፣ ማተብ-አልባ አድርገው፤ ከወያኔ ካድሬ፣ የውሸት ፋብሪካ፣ ተመርታ የወጣች፣ የዘረኞች ቋንቋ፣ “ትግሬ ትጠላለህ” የሚሏት ቃል አለች፤ ያገር ወዳዶችን ተቃውሞ ማስቆሚያ፣ በይሉኝታ ገመድ ሸብቦ ማሰሪያ. . .፣ ሆና ታገለግል ዘንዳ የተቃኘች፣ የጥላቻ ዜማ፣ ለጆሮ እምትቀፍ፣ ጩኸት የቁራዎች። . . . እዩትማ እንግዲህ፣ ወደ ውስጥ ሲሰምጥ፣ መብሰሉን ሲያቅተው፣ ሲላወስ እንደ ሊጥ፣ ራሱ በፈጠረው፣ ራሱን አስጨንቆ፣ ጭቃ ሲንከባለል፣ እኩዮቹን ክዶ፣ ራሱን አሳንሶ፣ ሚጢጢዋን ሲያክል፤ ስልጣኑ አስክሮት፣ የግፍ ሃብት ቆዝሮት፣ ንቀት አሳውሮት፣ … [Read more...] about “ትግሬ ትጠላለህ”
ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?
ሰሞኑን ኢህአዴግ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ታጅቦ የ"ባንዲራ ቀን" በሚል የመለስን ፈረጀ ብዙ ዝክር ሊደግስ ከወዲያ ወዲህ እያለ ነው። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ሲያነሱና ሲጥሉት የነበረውን ያገር መለያ ለፈጠራና ከጀርባው ተንኮል ያዘለ ዓላማቸው ሲሉ ቀኑ እንዲዘከር አድርገዋል፤ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደመሆናቸውም የታዘዙትን በሠንደቅ ዓላማው ላይ ጨምረዋል። በዚሁ የ"ባንዲራ ክብር" ሳይሆን በሌላ አህጉራዊ ክስተት ራሳቸው ያሰፉትን ጨርቅ ገልብጠው ባደባባይ ሰቅለውት ነበር። በወቅቱ ራሳቸው ያሰሩትን ባንዲራ አናትና ግርጌ መለየት ባለመቻላቸው ተወግዘውበታል፤ የትግራይን ቢሆን እንዲህ ያደርጉት ነበር ተብሎም ተጠይቋል። ባድመ ስትወረር "ደርግ ኢሰፓ" ተብለው ጎዳና ላይ የተጣሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ለዳግም ዘመቻ "እናት አገር ጥሪ" ሲተም በገጸ በረከትነት የተሰጠው ያደራ ቃል … [Read more...] about ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?