ከዚህ በፊት ስናደርግ የነበረውን የግጥም ጫወታ በበርካታ ምክንያቶችና ለመቀጠል ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለn:: በተቻለን ሁሉ እንደገና ለመጀር እየሞከርን በመሆኑ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በአጫጭር ግጥሞች ታላላቅ መልክቶችን የምታስተላልፈውን የብሌን ከበደን ግጥም ለዛሬው አቅርበናል - ግጥሙን ያገኘነው ከብሌን ፌስቡክ ገጽ ላይ ነው:: እስቲ እናንተም የፌስቡክ ውሎዋችሁን ስንኝ ቁዋጥሩበት:: ምን ይባላል! ውሎና አዳሬን እዚህ ተወዝቼ ሰፈሬን መንደሬን ቀዬዬን ዘንግቼ ከጠለቀው ባህር `ከፌስ ቡክ `ገብቼ ጥቂት ሞጫጭሬ ብዙ እውቀት አጊኝቼ ሀሳብን ደግፌ ካልመሰለኝ ትቼ አሁንም እዛው ነኝ መስኮቴን ከፍቼ ። አንድ ጊዜ በላኘ ቶኘ አንድ ጊዜ በስልኬ አይኖቼን ተክዬ እዛው ተላክኬ ቀንና ሌት ሳልመርጥ ስገባ ስወጣ ያ ደሞ ምን አለ ይሄ ምን አመጣ ያቺ ምን … [Read more...] about ምን ይባላል!
Archives for April 2014
ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ብትሆንም ቅሉ በተከታታይ ስልጣኑን የጨበጡት ጭፍን አንባገነኖች በሚያራምዱት አግላይ ምሁር ፖሊሲ ምክንያት እውቀታችሁን እና … [Read more...] about ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!
አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ
የሰው ልጅ ግላዊና ማህበራዊ ህይወቱን ለማሻሻል እንዲሁም የለት ተለት ህይወቱን የተሻለ ለማድረግ በአካባቢው ወይም በሚኖርበት ሃገር ያለውን አካባቢያዊና መንግስታዊ ስርዓት ጤናማ መሆኑ ግድ ነው። የማህበረሰቡም የለት ተለት ህይወት ከግዜ ወደ ግዜ አስቸጋሪ እየሆነ ሲሄድ የዛ ማህበረሰብ መንግስት ወይም አገዛዝ መቀየሩ አንደኛው መፍትሄ ነው። እንደሁለተኛ አማራጭ መፍትሄ የሚወሰደው ደግሞ የነበረውን አገዛዝ ለአነስተኛና ከፍተኛ ለውጦች ካለው ምቹነት አንፃር ተመዝኖ አስፈላጊ የሚባሉ የፖሊሲና የመንግስታዊ አወቃቀር ለውጦችን መተግበር ሲሆን ይህም በሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ጥሩ ሊባል የሚችል ለውጥ ሲያስገኝ ተስተውሏል። ነገር ግን ወደ ሃገራችን መንግስት ስንመጣ ከበድ ያሉ የማስተካከያ መፍትሄዎችን ቀርቶ እጅግ አነስተኛ የሚባሉ የማህበረሰብ የመብት ጥያቄዎችን እንኳን በሃይል በመጨፍለቅ … [Read more...] about አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ
ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም
"የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።..." የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ "የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።" የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነቁ። ሰው ሁሉ የጨከነባቸው መሰላቸው። እንዲህም አሉ። "የሃገሬ ሰው እንኳን የስልክ ጥሪ፤ የእናት ሃገር ጥሪስ መች ተቀበለ።" ለአመታት በተከታታይ በሁለት ድጅት እያደገች ያለች ሃገር የስልክ መስመር ችግር ይገጥማታል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ችግሩን በደንብ ላልተረዳው፣ ሰው የሞባይል ስልክ የሚገዛው እንዲሁ ይዞ ለመታየት ነው ያስብል … [Read more...] about ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም
ነጋ ደግሞ !
ላስታምም የሆዴን ጩርር ..... ርታ፤ ላዳምጥ የወስፋቶቼን ጩኸት ጫጫታ፤ የማያቋርጥ የረሃብ ሳል ልስል፤ እሹሩሩ እያልኩ ረሃብን ላባብል፤ ልደማ ልቆስሌ ልገዘገዝ በችጋር፤ በቁም ሞቼ - ላልኖር ስኖር፤ በብርሃኗ ላላጌጥ - ጮራዋ ለኔ ላይፈነጥቅ፤ ነጋ ደሞ ! ...... ሌላ ቀን - ፀሐይ ወ'ታ ልትጠልቅ :: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ነጋ ደግሞ !
አይ አዜብ!
አዜብ ሲባል ማን በአዕምሮህ ሊመጣ እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ በውስጥህ ያሰብከው ‹የባለራዕዩን መሪ› ባለቤት አዜብ መስፍንን ከሆነ ለጊዜው ግምትህ አልሰራም፡፡ አሁን አዜብ የምልህ ሌላ ሴት ናቸው፡፡ አዜብ አስናቀን ነው፡፡ (አስናቀ ስልህም እንዳትደነግጥ...የሰው ለሰው ድራማው አስናቀ አይደለም፡፡) ለማነኛውም አዜብ አስናቀ የግልገል ጊቤ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩትን ሴት ነው እየጠቀስኩልህ ያለሁት፡፡ እና አዜብን እንዴት አነሳኋቸው ካልክ ጉዳዩ ወዲህ ነው፡፡ ሴትዮዋ ከግቤ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነታቸው ተነስተው ወደ ሌላ ‹ከፍ› ወዳለ ሹመት መጥተዋል፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚነት አድገዋል፡ ፡ ሹመታቸው በቀድሞው ስራ አስፈጻሚ አቶ ምህረት ደበበ ቦታ መሆኑ ነው፡፡ እኒህ ሴት ታዲያ ‹አይ› የሚያስብል ነገር … [Read more...] about አይ አዜብ!
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ‘ሮሮና ስጋት
የትምህርት ሚኒስትር በ2006 ዓ.ም በአገሪቱ በተፈጠረው የመምህራን እጥረት ምክንያት በተለ ያዩ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ኢትዮጵያውያንን ለአንድ አመት ሙሉ ወጫቸውን ችሎ የማስተማር ስነ ዘዴ (ፔዳጎጅ) በማስተማር ወደ መምህርነት እንዲገቡ ማስታ ወቂያ ያወጣል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረ ትም ለማጣሪያነት የቀረበውን ፈተና በመፈተን መልምሎ ለስልጠና እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሰረት በ10 ዩኒቨርሲቲዎች (መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ወሎ፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ሀሮማያ፣ ሀዋሳና አዲስ አበባ) እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡ ይህ ስልጠና እየተካሄደ ባለበት ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ሙሉ ወጫቸ ውን መንግስት እንደሚችል ተነግሯቸው ነበር የመጡት፡፡ በዩኒቨርሲቲው መጀመሪያ የተደለ ደሉት 330 ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ተማሪዎቹ ቃል በተገባላቸው መሰረት … [Read more...] about የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ‘ሮሮና ስጋት
የከሸፉት የህወሓት የተስፋ ቃላት
የደርግ መንግስት ከወደቀ በኋላ በእግሩ የተተካው ህወሓት ይኸው ሥልጣን ላይ ከወጣ 23 ዓመት ሊሆነው ነው። ህወሓት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ዲሞክራሲን አሰፍናለው፣ ሰብአዊ መብት አክብሬ አስከብራለው፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብትና እኩልነት ይከበራል፣ ልማት ይመጣል የኢትዮዽያ ሕዝብ ስደት ያበቃል፣ በቀንም ሦስት ጊዜ ይበላል የሚሉት ዋንኞቹ ነበሩ። እስኪ አንድ በአንድ እንያቸው። 1. ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በተመለከተ ህወሓት ከበረሃ ወጥቶ ከተማ እንደገባ ዋንኛ ጩኸቱ ይሄ ነበር። በመጀመሪያ አካባቢ ነፃ ጋዜጦችን ማሳተም፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በፖለቲካ ፓርቲ መደራጀት የመሳሰሉት ነገሮች ጥሩ ጅማሮ ያሳዩ ቢሞስሉም ብዙም ሳይቆይ ግን የህወሓት ትክክለኛ ባሕሪ መገለጥ ጀመረ። ጋዜጠኞችን ማሰርና ማንገላታት፣ ነጻ የሙያ ማኅበራትን ማፍረስ፣ ተቃዋሚዎችን ማሰር ብሎም በስውር ማስገደል፣ … [Read more...] about የከሸፉት የህወሓት የተስፋ ቃላት
ፋሲካን በመንገድ ዳር
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ፋሲካን በመንገድ ዳር
ሕወኃት/ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን?
ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ጨካኝ አምባገንን መንግስትና የመንግስት ስርአቶች አስተናግዳለች::እነዚህም ስርአቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሉል አሁንም እየተክፈለ ይገኛል:: አሁን ኢትዮጵያን አስተዳድራለው የሚለው የወያኔ ቡድን ከሁሉም የባሰውንና በታሪኩ አይቶ የማያውቀውን ከፍተኛ ግፍ በደል ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሠበት ይገኛል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን ላለፉት 22 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጅግ በጣም አስከፊና ሁዋላ ቀር የህዝብን ጥቅም የማያስጠብቅ ጭከናና ኢሰብኣዊ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም አገርን ማፈራረስና የኢትዮጵያዊነትን ታሪክና ባህልን የማጥፋት ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብን የሀገር ሀብት መዝረፍ በስፋት እየፈጸመ ይገኛል::(ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሕወኃት/ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን?