ወንድ ልጅ ሲወለድ አባት ለተወለደው ልጁ ጠብ - መንጃ (ጠመንጃ) ለመግዛት ደፋ ቀና ከሚባልበት አካባቢ ነው ተወልጄ ያደኩት፡፡ ይህ የሚደረገው ደግሞ በቂ ሃብት ስላለ ሳይሆን “ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ እንዝርት አቅርቡለት ይፍተል እንደ እናቱ” የሚለው የንቀት አባባል በልጁ ላይ ሲያድግ እንዳይደርስበት ከወዲሁ ለማዘጋጀት ነው፡፡ እንዲያውም ልጅ በልጅ ተሸንፎና ተመትቶ እያለቀሰ ወደ ወላጆቹ ለእርዳታ ሲቀርብ አልቃሻ ልጅ አልወድም/የለኝም ተብሎ በጥፊ ወይም በአለንጋ ይደገማል፡፡ በለው! ትሸነፍና ወዮለህ! እንዳታሳፍረኝ! የሴት ልጅ! (ከወንድ ብቻ የተወለደ ያለ ይመስል)፣ ሊጥ አትሁን!፣ አስለቅስ እንጂ አታልቅስ!፤ አትበለጥ! ኩራት እራቱ! ከአረባባ ግልድም ሙልጭ ያለ ቂ . . . ይሻላል! ከማን አንሼ!. . . ወዘተ እየተባልንና እያልን ነው እኛ ኢትዮጵያውያን … [Read more...] about በክርስትና ላይ ጥናታዊ ምርምር ሲያደርግ የነበረው ሰው በራሱ ሕይወት ላይ ምርመራ ተደርጎበት እጁን ሰጠ!!!
Archives for March 2014
የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ
የመጨረሻውን በማያውቁት ያዘቀዘቀ ጨለማ መንገድ እየተውዘረዘጉ፤ መሪዉን በማስተካከል ከማያውቁት መጨረሻ ለመድረስ የሚጣድፉ መሪዎች፤ የድንቁርና ኒሻን ይገባቸዋል። በፈጠሩት የራሳቸው የመኖሪያ የገዢነት መኮፈሻ “ሀቅ” ተጀንነው በመቀመጥ፤ ፈንጠር ብሎ ርቆ ሌላውን ማየት ባለመቻላቸው፤ የተከተላቸውን ሳይውቁት እጃቸውን ሠጥተዋል። የተለዬ የመሰለ የራስ “ሀቅ” የብዥታ ጭጋግ፤ ሩቅ ማየትን ነፈጋቸው። ማስተዋልን ከአእምሮ መዝገባቸው ሰወረው። መደናበርን አነገሠባቸው። ካይናቸው ፊት በተገተረው የእብሪታቸው መነፅር፤ ዓለምን ግቢ ውጪ እያሉ በማስገደድ፤ ያለው የሌለ ሆኖ፣ ከተጨባጩ ይልቅ በምኞታቸው ዓለም ሲዳክሩ፤ የቆሙበት መሬት ከዳቸው። ከሕዝቡ መሆናቸው ቀርቶ ሕዝቡ የነሱ አገልጋይ ሎሌ ሆነና፤ የነሱ መኖሪያና የሕዝቡ መኖሪያ በአጥር ተለያዬ። መኖሪያቸው ዓለማቸው ሆነና ከሕዝቡ ዓለም ወጡ። ረጋ … [Read more...] about የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ
የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ አሳሳች መረጃዎችና የተምታታ አስተያየት
በመሠረቱ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ስለ አብዮቱ “ እኛና አብዮቱ “ የሚል መጸሐፍ ጻፉ የሚል ዜና ስሰማ ፣ መጸሐፋቸው እንደ ሌ/ኮ መንግሥቱ ኃይለማርያም መጸሐፍ በቅጥፈት የተሞላ አይሆንም ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ፡፡ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡ በነገራችን ላይ የሻምበሉን መጸሐፍ ገና አላገኘሁትም፣ ነገር ግን አንድ ወዳጄ ከምዕራፍ 13–16 ያሉትን ገጾች ፎቶ ኮፒ አድርጎ ስለሠጠኝ አየተገረምኩኝ አነበብኳቸው፡፡ ሻምበሉን ምን ነካቸው ብዬም እራሴን ጠየኩኝ፡፡ ደራሲው በትምህርታቸው እንዳልገፉ ይገባኛል ፡፡ ሆኖም ግን በትምህርት ያለመግፋት ትንታኔ ላይ ችግር ይፈጥር እንደሆን እንጂ ፤ “ በእጅ የገባን መረጃ ” አሳስቶ ማቅረብ ከምን ሊመነጭ እንደሚችል ፈጽሞ ሊገባኝ አይችልም፡፡ ፍቅረሥላሴ መረጃው በእጃቸው ከሌላቸው አርፈው መቀመጥ አለባቸው እንጂ ባልሆነ ማስረጃ አንባቢን ማሳሳት … [Read more...] about የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ አሳሳች መረጃዎችና የተምታታ አስተያየት
እኔና አንቺ… ፫
በሕዝብ ተጋርደን ባ’ገር ተከልለን ለካስ እኔና አንቺ ብዙም ዕውቀት የለን። እኔን ስመረምር አንቺን እዚህ ሳይሽ እኔም ያን አይደለሁ አንቺም ያቺ አይደለሽ። እንዲህ ካደረገን ስደት አሸንፎ ጭራሽ ከሚለየን ኑሮአችንን ገፎ ሠርግ ባንደግስም ባይረጭ አበባ በአዲስ ትውውቅ ድጋሚ እንጋባ። ****************** እኔና አንቺ … ፩ - ፖለቲካና ስደት እኔና አንቺ…፪ - ሀገርና ክህደት … [Read more...] about እኔና አንቺ… ፫
በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ
Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል። በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ … [Read more...] about በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ
አድዋ ለኔ
እኔ የምኖረው በአሜሪካ ነው። በአሜሪካ ሆኜ የአድዋን በዓል አከበርኩ። የኢትዮጵያዊያን ድረገፆችን እየተመላለስኩ ቃኘኋቸው። ሬዲዮኖችን አዳመጥኳቸው። የስልከ ልውውጦችንና የእንግዶችን ሃሳቦች ተከታተልኩ። ስደሰት፣ ሳዝን፣ በጣም ስደሰትና በጣም ሳዝን ዋልኩ። ሲመሽና የምኝታ ሰዓቴ ቀርቦ ባልጋዬ ላይ ስጋደም፤ እንቅልፍ ቶሎ አልወስድህ አለኝ። መገለባበጡ ለውጥ አላመጣ ሲል በሃሳብ መዋተቱን ተያያዝኩት። አድዋ ለኔ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ከዕለቱ ወደላይና ወደታች መዋዠቅ ጋር ተዛምዶ አፋጠጠኝ። እውነት አድዋ ለኔ ምንድን ነው? አድዋ ከመቶ ዓመት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ነው። በዚያ ጊዜ የተካፈሉትና የነበሩት አሁን የሉም። አድዋ በአንድ የሀገራችን አካባቢ የተፈፀመ ጉዳይ ነው። ታዲያ ለኔ ከአንድ መቶ ዓመት በኋላ ላለሁት ምኔ ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ ስመላለስበት እኩለ ሌሊት ሆነ። ለካስ … [Read more...] about አድዋ ለኔ
የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ
በእርግጠኝነት ኢትዮጵያዊ ልብ ላለው ሰው ሁሉ ስለ አድዋ ድል ሲሰማና ሲያወራ ልቡ በኩራት ይሞላል መንፈሱ ይነቃቃል፡፡ ኢትዮጵያዊ ብቻም አይደለም በየትኛውም ዓለም ያለ በቅኝ ግዛት ቀንበር ፍዳ ያየ የትኛውም የሰው ዘር ጭምርም እንጅ፡፡ ይህን አንጸባራቂ ድል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሰልፎ ካስመዘገበ እነሆ ነገ የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም 118 ዓመቱን ይይዛል፡፡ ይህንን ድል ለመቀዳጀት ፈተና የነበሩት ነገሮች ምን ምን ናቸው? ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ተገኘ ? የዚህ ታላቅ ድል ትሩፋቶችስ ምን ምን ናቸው? የዚህ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? ይህ ድል እንዴት ይጠበቃል? ብዙ ቢባልለት ከማይበቃው ከአድዋ ድል እነዚህን ነጥቦች ብቻ ነጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡ ዐፄ ምኒልክ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ፋሽስት ጣሊያን በዘመነ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከነበረበት አልፎ … [Read more...] about የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ
ህዝብን በመጨቆን ሀገርን መምራት አይቻልም!
የፖለቲካ ስርአትና የአንድ ሀገር እድገት ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸዉ። አንድ አገር ትክክለኛ ባልሆነ የፖለቲካ አገዛዝ ይበለፅጋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያም የወያኔ መንግስት ባነገሰው የተዛባ አገዛዝ ሳቢያ ህዝባችን ለከፋ ችግር መዳረጉ በገሃድ የሚታይ ሃቅ ነው። ታዲያ በዚህ ወያኔያዊ የተዛባ አገዛዝ እንዴት ከችግር ልንወጣ እንችላለን? አገራችን ኢትዮጵያ ምንም እንኳ የጥንት ስልጣኔ ባለቤት ብትሆንም በአየር ንብረትም ሆነ በተፈጥሮ ሀብት ጥሩ ከሚባሉት ሀገሮች አንዷ ብትሆንም እንደ እድል ሆኖ መሪዎች ግን አልተሳኩላትም። ለምን ኢትዮጵያ የረሃብ አገር ተባለች ለምን ዜጎቿ ተደስተው በነጻነት መኖርን እንደተመኙ ህልማችዉ ከንቱ ሆነ? ብዙዎች የሞቱላት አገር አንገታቸዉ ለሰይፍ ደረታቸዉ ለጥይት የሰጡላት አገር ኢትዮጵያ በህዝቦቿ ታታሪነት አለም ያደነቃት ለምን … [Read more...] about ህዝብን በመጨቆን ሀገርን መምራት አይቻልም!
ዝምታው በዛ
አገር ሲቆረስ ድንበሩ ሲፈርስ ማንነት ታሪክ ሲሻር መሬት ሲገመስ አገር ያለ ባህር በር ስትቀር ዜጋ ማንነት በጎሳ ሲቀየር ድንበር ተቆርሶ ለባድ ሲለገስ ወገን ሲጨቆን መኖሪያ ቤቱ ሲፈርስ ሀብት ንብረቱ ተዘርፎ ከቀየው ቦታው ሲሰደድ ዜግነት ክብሩ ሲጣስ ሰብአናው ሲዋረድ በአረብ ምድር ሲገደል አንደ አንስሳ ሲታረድ ህይወት ሲቀጠፍ ሲታነቅ በገመድ ዜግነት ክብሩ ሲዋረድ ሰአብዊ መብቱ ሲናድ የመኖር ህልሙ ባዶ ሲሆን ፊቱ በአንባ ሲታጠብ ሲዋጥ በሀዘን ለስቃይ ችግር ሲዳረግ በረሀብ አለንጋ ሲገረፍ ጠኔ ሲመታው በከባድ ህመም ሕይወት ሲቀጠፍ ሀገር ወገን ሲጣራ ሰሚ ሲያጣ ሲያለቅስ መንግስት ጆሮ ሲደፈን አልሰማ ሲል ሲሆን ደንታቢስ አስከመቼ ነው ዝምታው ላገር ለወገን መድረሻው የብሶት የችግር ማብቂያው ተነሳ ወገን ህብረት አንድነት አጠንክር ጨካኝ ወያኔን … [Read more...] about ዝምታው በዛ
“ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!
“ … ወታደር ባለመሆኔ የጦርነቱን ውሎ ማተት አያምርብኝም፡፡ ያም ሆኖ የአድዋ ድል ዛሬ ብርቅ በሆኑብን ሁለት እሴቶች ረድኤት የተገኘ ይመስለኛል፡፡ እኒህ ሁለት እሴቶች መተባበርና መደማመጥ ናቸው፡፡ ጣልያኖቹ በጊዜው ወደ ጦርነት ሲገቡ ተስፋቸውን የጣሉት በመድፍና በጠመንጃቸው ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዝነኛ በነበሩበት የውስጥ መቆራቆስ ላይ ነው፡፡ የትግራይ ቅልጥም ሲመታ ሸዋ ያነክሳል ብለው አላሰቡም፡፡ በርግጥም በክፍለ ሀገሮች ውስጥ የተለያዩ ሽኩቻዎች ነበሩ፡፡ እኒህን ሽኩቻዎች አስረስቶ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ለአንድ አላማ ማሠለፍ ምኒልክነትን ይጠይቃል፡፡ “መደማመጥ ያልሁትን ላሳይ፡፡ አባ ዳኘው ከዛሬው የይስሙላ ፓርላማችን በተሻለ ሁኔታ ለልዩነቶች ቦታ የሚሰጥ ተንቀሳቃሽ ምክር ቤት በጦርነቱ ወቅት መፍጠር ችለዋል፡፡ ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ በውጊያው ዋዜማ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ … [Read more...] about “ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!