መዝሙረ ኢህአዴግ! (በላይ ማናዬ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በተደረገላቸው ግብዣ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በጉዞው ዓላማና በተለያዩ የአገራችን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያና የዩክሬኑ ግጥምጥሞሽ * ባለ ቀለሙን አብዮት ማን ይመራዋል? (በጌታቸው ሺፈራው) አዲስ ጠብመንጃ በምንሽር፤ አገዳደሉ ሆድ የሚያሽር፡፡ (በዝክረ ታሪክ አምድ፡- አቶ ታዲዎስ ታንቱ) “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ” (ግርማ ሞገስ) ኑሮ ሆነብን እሮሮ (ጋሻው መርሻ) የኢትዮጵያ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ (ኤልሳቤት ወሰኔ) ሰላማዊ ትግሉ መሪዎቹን ይሻል (ታምራት ታረቀኝ) ኢትዮጵያዊነት ለእኔ! (አፈወርቅ … [Read more...] about ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር
Archives for March 2014
የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፈኑ
የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ። በመለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ከማምራታቸው በፊት ኬንያ እንደነበሩ፣ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን ለምን እንደተጓዙ የዜናው ምንጮች በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲደበቅላቸው የጠየቁ የጋምቤላ አስተዳደር ባልደረባ ለጎልጉል የአካባቢው ዘጋቢ እንደተናገሩት አቶ ኦኬሎ ደቡብ ሱዳን ሆቴል በተቀመጡበት መታፈናቸውን አረጋግጠዋል። “ወያኔ እጅ ገብቷል” ሲሉ ያከሉት እኚሁ ሰው “አቶ ኦኬሎ ብረት … [Read more...] about የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፈኑ
Some policy considerations regarding the Ethiopian outmigration
In our December 19, 2013 article entitled “Explaining the Ethiopian outmigration: incentives or constrains” we alerted readers and policy makers in Ethiopia about the push, pull and mediating factors of outmigration in general and outlined the factors as they relate to Ethiopia. In this short article we aim to discuss further the incompatibility between macroeconomic growth and outmigration and close the piece by outlining potential mitigation strategies. By the end of 2013 and early 2014 the … [Read more...] about Some policy considerations regarding the Ethiopian outmigration
የግብጽ ፍርድቤት 530 በሚሆኑ የሙስሊም ወንድማማች አባላት ላይ ሞት ፈረደ
* ውሳኔው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አስደንግጧል በሕዝብ ከተመረጡ በኋላ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተወገዱትን የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲን በመደገፍ በፖሊስ ጣቢያ ላይ አደጋ አድርሰው የነበሩ 529 ተጠርጣሪዎች ትላንት ሰኞ ዕለት የሞት ቅጣት ተበየነባቸው፡፡ የብይኑ ፍጥነትና የተፈረደባቸው ተከሳሾች ብዛት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አስደንግጧል፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ከሆነ ውሳኔው ለይግባኝ የሚቀርብ ሲሆን በሙስሊም ወንድማማች ላይ ሆን ተብሎ የተነጣጠረ ጥቃት እንደሆነ ዘግቧል፡፡ በዓለማችን በቅርብ ጊዜያት ከተካሄዱ የሞት ፍርድ ብያኔዎች በብዛትም ሆነ በፍጥነት ለየት ያለ እንደሆነ የተጠቀሰለት ይህ የፍርድ ሂደት በግብጽ የሕግ የበላይነት እየከሰመ የሄደ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ በርካታ የሕግ ምሁራን … [Read more...] about የግብጽ ፍርድቤት 530 በሚሆኑ የሙስሊም ወንድማማች አባላት ላይ ሞት ፈረደ
የእነ ሠዓሊ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን የቅስቀሳ ዘመቻ የታሪክ ነጠቃ ኣካል ነው፣
አንድ ነገር ለማለት ያነሳሰኝ ጉዳይ ይህ ግላሰብ ያለ ዕውቀቱና ምንም በማያገባው ነገር ውስጥ ገብቶ ሲያምስ ስላገኘሁት ነው። ይህም “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን?” በሚለው ርዕስ ሥር የወሬ ወሬ ጽሁፍ ደራርቶ ራሱንና መሰሎቹን ለማስደሰት ስለ ፈጸመው ጉዳይ ትንሽ ለማለት ፈለግሁ። … [Read more...] about የእነ ሠዓሊ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን የቅስቀሳ ዘመቻ የታሪክ ነጠቃ ኣካል ነው፣
የጎሣ ግጭቶችና የአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ሚና
የተባበሩት መንግሥታት በ1948 ዓ.ም. ባወጣው የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ መግለጫ አንቀጽ 2 ላይ እያንዳንዱ ሰው በዘር፣ በቀለም፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አስተያየት፣ በኅብረተሰብ ምንጭ፣ በሃብት፣ በትውልድ፣ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ምንም ዓይንነት ልዩነት ሳይደረግበት በመግለጫው ላይ በተጠቀሱት መብቶችና ነፃነቶች በእኩል የመጠቀም መብት እንዳለው የደነግጋል። ይህንን ድንጋጌም መነሻ በማድረግ ዘረኝነትንና ሌሎች ከሰብአዊ መብቶችና ነፃነቶች ጋር የሚቃረኑ የአድልዎ ተግባራትን ለማስቀረት በሚል በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ስምምነቶችና መግለዋዎች በተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ጸድቀው ወጥተዋል። ከእነዚህም መካከል በተባበሩት መንግስታት ጸድቆ የወጣውና ከጃንዋሪ 04 ቀን 1969 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለው “ማንኛውንም ዓይነት የዘር አድልዎ ለማስወገድ … [Read more...] about የጎሣ ግጭቶችና የአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ሚና
ኢህአዴግ ባደባባይ የወደቀውን ፈተና “በጓሮ” አለፈ
ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ብሎም ለህዝቦች ጥቅም ቅድሚያ እንደሚሰጥ ህግ ደንግጎ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ኢህአዴግ ያቀረበውን የይግባኝ ማመልከቻ ተቀብሎ ማጽደቁ አነጋጋሪ ሆኗል። በ2009 ኢህአዴግን "ያወጣሁትን መስፈርት አታሟላም" በማለት እውቅና የከለከለው ይህ ተቋም፣ ኢህአዴግ በሚከሰስባቸው ዋና ጉዳዮች ለውጥ ሳያደርግ የራሱን ውሳኔ የገለበጠበት አካሄድ እየተመረመረ እንደሆነ የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል። የኢህአዴግን የእውቅና ይግባኝ ጥያቄ ተቀብሎ ያጸደቀው የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የሚባለው ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ነው። ተቋሙ ኢህአዴግ በ2009 አቅርቦት የነበረውን የእውቅና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ የሰጠው ምክንያት … [Read more...] about ኢህአዴግ ባደባባይ የወደቀውን ፈተና “በጓሮ” አለፈ
የታሪክ ጥናት አብነት – የታሪክ ትምህርት ተግዳሮት
ታሪክ ማጥናት አያሌ ጠቀሜታዎች አሉት። ታሪክን የምናጠናው በተለያዩ ምክንያቶች ነው። ለታሪክ ማጥናት የመጀመሪያው አስባብ የአእምሮን እድገት ለመለኮስ ግልጋሎት መዋሉ ነው። ታሪክ ማዕምራዊ ብስለትን ያነቃል። ሁለተኛው ምክንያት ደሞ፣ ለመልካም ዜግነት መሰረት መጣል ነው። ሶስትም፣ ምግባራዊ ግዴታዎችን ለመፈፀም በብርቱ ያግዛል። በአራተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የታሪክ ጥናት ዞግ ታሪክ ባህልን ለመገንዘብ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ነው። በመጨረሻም፣ ታሪክ ለዉጥን ለማገናዘብ አስፈላጊነቱ መጉላቱ። አሜሪካዊው የታሪክ ምሁር ዋልተር ማክዱጋል ታሪክን መረዳት ለምን እንደሚጠቅም ባስተነተነበት የምርምር ወረቀት ላይ፣ ሶስት አበይት ምክንያቶችን እንደመደምደሚያ አቅርቧል፣ እንዲህም ይነበባል ። "የታሪክ ትምህርት የአንድን ሀገር ህዝብ አእምሮአዊ እድገት የሚያነቃቃ፣ አስፈላጊ የሆነዉን … [Read more...] about የታሪክ ጥናት አብነት – የታሪክ ትምህርት ተግዳሮት
ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አፈናና እሰራት ምላሽ አይሆንም
የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት መጋቢት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ዓመት አራተኛ መደበኛ ስብሰባው የካቲት 30 ቀን 2006 ዓም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ በተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት ላይ ፖሊስና ፍርድ ቤት በመተባበር የፈጸሙትን ሕገ መንግስት የጣሰ ተግባር፣ እንዲሁም ከአሜሪካ መንግስት በደረሳቸው ግብዣ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓም ምሽት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፈያ በተገኙት የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ላይ ራሳቸውን ከህግ በላይ ያደረጉ የደህንነት ኋይሎች የፈጸሙትን አሳፋሪና ሕገ ወጥ ተግባር በመመርመር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ የተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በሩጫው ከተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የሚለዩት … [Read more...] about ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አፈናና እሰራት ምላሽ አይሆንም
ሲቪል ድርጅቶች
ዴሞክራሲ ስርዓት በመገምባት ላይ በሚገኙ ወይንም የዴሞክራሲ በዳበረባቸው አገሮች ውስጥ እጅግ ብዙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ተቋሞች ከመንግስት ነጻ ሆነው ይመሰረታሉ። በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ። የጋዜጠኞች ማህበሮች፣ የጋዜጠኞች መድረኮች፣ የሰራተኛ ማህበሮች፣ የተማሪ ማህበሮች፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ የስነጽሑፍ ማህበሮች፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ አሳብ አቀንቃኝ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ አሳብ አቀንቃኝ ቡድኖች፣ የህዝብ ጤንነት እና ኑሮ ሁኔታ መሻሻል ተቆርቋሪ ድርጅቶች፣ የመንግስት ግልጽነት ታዛቢ እና አጋላጭ ድርጅቶች እና የመሳሰሉትን ድርጅቶች ማለታችን ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሲቪል ድርጅቶች