‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡ መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡ በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም … [Read more...] about የመረጃ ነፃነት?
Archives for January 2014
ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል
በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ … [Read more...] about ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል
ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?
ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው። ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው አገራቸውን ለመርዳት ወደ አገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?
The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW)
In appreciation of Ethiopian Sports Federation in North America (ESFNA) for the Support Given to The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) in 2013 The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) sends its well wishes for a happy and peaceful new year to all members of our community. We are grateful to individuals and organizations that have supported us in 2013. We would like to extend our special thanks to the Ethiopian Sports Federation in North America (ESFNA ) for the support … [Read more...] about The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW)
የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃትማጥፊያ መዳኒት
ካለመታደል ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ … [Read more...] about የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃትማጥፊያ መዳኒት
የቦይ ስካውት ትዝታዬ
"አስካውት!..." "ምን ጊዜም ዝግጁ!!!" ዱሮ ዱሮና በኛም ዘመን የቦይ እስካውት ክለብ (Boy Scout) እንቅስቃሴ ሞቅና ደመቅ ያለ ነበር፡፡ ሰላሌ ፍቼ፣ የአበራና አስፋው ወሰን የ1ኛ ደረጃና ወሊሶ የደጃዘማች ገረሱ ዱኪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ እያለሁ (ከ1953-1960 ዓ.ም.) የቦይ እስካውት ክለብ አባል ነበርኩ፡፡ ፍቼ እያለን፣ የእስካውት ክለባችን ኃላፊ መምህር ወልዴ ይባሉ ነበር፡፡ በእግራችን ወደ ገጠር እየተጓዝን ድንኳንም ተክለን፣ ምግባችንን አብስለን፣ ሻይ አፍልተን እየተደሰትን አድረን እንመለስ ነበር፡፡ ማታ ማታም ደመራ ደምረን (Camp fire) ዙሪያውን ከበን እየጨፈርን፣ ግጥም የመግጠም ተሰጥኦ ያለን እየገጠምን ለጓደቾቻችን እያሰማን፣ አጫጭር የወዲያው ፈጠር ድራማም እያሳየን እንደሰት ነበር፡፡ ቀልዳ ቀልድም የሚያሰሙ ብዙዎች ነበሩ፡፡ በተለይም … [Read more...] about የቦይ ስካውት ትዝታዬ
ሰማቹህ ወይ መርዶ
ሰማቹህ ወይ መርዶ ? ሀገር ተገምድሎ ሰማቹህ ? ወይ ነዶ!! ፤ ካገርህ ተከፍሎ ሀገርህ ተቆርጦ ፤ ለሱዳን ተሰጠ መንግሥት ነኝ ባለው ፤ ራሱን ባስቀመጠ ብለው ሲያወሩልኝ ፤ መንፈሴ ተናጠ አንጎሌ ተናጋ ፤ አቅሌ ተናወጠ ብርድ ብርድ አለኝና ፤ እያቅለሸለሸ ወይ ወደላይ አይል ፤ እንዲሁ እያሸ ባዕድ የሆነ ስሜት ፤ ሲያውከኝ አመሸ አሳድሮ አዋለኝ ፤ ሰንብቶም አልሸሸ ይሄን የሀገር ክህደት ፤ ይሄን የሞት ዜና ሙሾ ልጻፍለት ፤ ብየ ተነሣሁና ወረቀት ብዕሩን ፤ ካለበት አንሥቸ ለታሪክ ለትውልድ ፤ ከትቤ ላልፍ ትቸ ከዚህች ቀን በፊት ፤ በሀገሩ ታሪክ እንደዚህ ያለ ጉድ ፤ እንዲህ ያለ መታወክ በገዛ መንግሥቱ ፤ ለባዕድ ሲበረከት ሽንጥ ገትሮ በሐሰት ፤ ለባዕድ ሲሟገት ገጥሞት አያውቅምና ፤ ብዕሩ … [Read more...] about ሰማቹህ ወይ መርዶ
ዋናውን “ሌባ” ማን ይከሰዋል?
ኢህአዴግ ልዩ ምክንያት ከሌለው በስተቀር የውጪ ጠላት አያፈራም የሚሉ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። ምክንያት ካለው ግን ቅንድቧን አንደተላጨችው ነገረኛ ሴት ለመጋጨት ይፈጥናል። ከፊትለፊቱ ገንዘብ ካየ ደግሞ ኢህአዴግ ገደል ሜዳው ነው የሚሉም አሉ። ገንዘብ በሌለበት ቦታ ኢህአዴግ አይታይም በማለት ከበረሃው ኑሮ ጀምሮ የሚከሱት ጥቂቶች አይደሉም። በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ምድር በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚሰቃዩትን ወገኖች አስመልክቶ የያዘው አቋምም ከዚሁ መርሁ የተቀዳ እንደሆነ የሚከራከሩ በርካታ ናቸው። "ምን ያድርግ የኖረው የአገሪቱ ችግሮች ሁሉ ተቆልለው እሱ ላይ ወደቁ" በማለት ኢህአዴግን ለኢትዮጵያ የተቀመጠ "የተቀባ" መፍትሔ አድርገው የሚያወድሱ አሉ። ኳስ ሜዳ ያደገችው ኑሪያ መሐመድ አሁን የምትኖረው ኳታር ነው። ኑሮ እንዳሰበችው የተመቻቸ ባይሆንላትም ወደ አገርዋ ለመመለስ … [Read more...] about ዋናውን “ሌባ” ማን ይከሰዋል?
Who is Seyyid Mohamed Abdillahi Hassan? An Ethiopian hero or a Somalia nationalist who championed for the goal “Greater Somalia”
Recently the Somali Regional government installed a statue in the middle of Jijiga town (the regional capital). This statue is for the 19th century “Somali patriot” who fought with all forces within the Horn of Africa. Historical books and literatures are full of the ideal he had waged battles and wars. In this short article I would like to consider whether he was an Ethiopian and deserve a multi-million dollar statue in the centre of the regional capital. And examine the legacy this man will … [Read more...] about Who is Seyyid Mohamed Abdillahi Hassan? An Ethiopian hero or a Somalia nationalist who championed for the goal “Greater Somalia”
የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ
መግቢያ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ውድ አቶ ካሳሁን ነገዎ ታዋቂ ሰዎችን ወይም ምሁሮችን ለቃለ-መጠይቅ እያቀረበ አስተያየታቸውንና አመለካከታቸውን እንድናዳምጥና ትምህርት እንድንቀምስ የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። በዚህም መሰረት በአ.አ በ23.12.2013 ዓ.ም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በቅርቡ ለዕትመትና ለንባብ ባበቃው፣ ‘‘ዲሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት‘‘ በተባለው መጽሀፉ ዙሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ለቃለ-መጠይቅ ጋብዞት አንዳንዶቻችን ለማዳመጥ ችለናል። የቃለ-መጠይቁን ምልልስ በጥሞና ላዳመጠ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ መልስ ግልጽና ብዙም የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም። እንደ ዕውነቱ ከሆነ አዲሱን የዶክተር ብርሃኑ ነጋን መጽሀፍ ለማግኘት ስላልቻልኩና ስላላነበብኩት ስለመጽሀፉ ጥሩና መስተካከል ይገባቸዋል ብዬ በማምነው ላይ ገንቢ ትችት መስጠት አልቻልኩም። መጽሀፉን አግኝቼ ከአነበብኩት … [Read more...] about የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ