የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አራት ኪሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጆሊ ባር፣ ኮጆሊ ባር ወደ አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገርያ የሚያገለግል የብረት መሰላል መሥራቱ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣኑ ይህንን መሸጋገሪያ መሰላል የሠራው፣ በአካባቢው የሚተላለፈው የሕዝብ ብዛት ከሌሎች አካባቢዎች የበዛ ስለሆነ፣ የትራፊክ መጨናነቅና በየቀኑ በተሽከርካሪ አደጋ እየተቀጠፈ ያለውን የሰው ሕይወት (ምንም በተባሉት ቦታዎች እስካሁን የከፋ አደጋ ባይደርስም) ለመታደግ በሚል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ሦስተኛ መሸጋገሪያ ድልድይ የሠራው ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ወደ ራስ መኰንን፣ ወደ አዲሱ ገበያና ወደ አፍንጮ በር (ውቤ በረሃ) በሚወስደው አደባባይ ላይ ነው፡፡ ይህ መሰላል አቀማመጡ ወይም የተሠራበት አቅጣጫ ለተጠቃሚው አመች ባለመሆኑ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሲጠቀሙበት የሚስተዋሉት … [Read more...] about ‹‹ጥቅም›› ላይ ሳይውል የፈረሰው መሸጋገሪያ
Archives for December 2013
የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ
1. መግቢያ ከደርግ የ17 አመታት የአገዛዝ ውደቀት በኋላ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች በስፋት ሲንጸባረቁ ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ዋነኛው ነው:: በዚህ ወቅት ውስጥ ለብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ በፖለቲካ ኃይሎች የቀረቡት የመፍትሔ ሃሳቦች የተለያዩ ቢሆንም የመፍትሔ ሃሳቦቹ የሚመነጩት ግን በዋናነት ከሁለት ተገዳዳሪ አስተሳሰቦች ነው:: አንደኛው አስተሳሰብ የሚያጠነጥነው የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄው የሚካትተው ከኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ ጋር ተያይዞ የተፈፀሙ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትንና በደሎችን እንዲሁም በያ ትውልድ ውስጥ የተፈፀሙ መጠፋፋትን አካቶ ሁሉን-አካታች መድረክ በማዘጋጀት ያለፈውን በደሎች ዕውቅና በመስጠት በፖለቲካ ሊህቃን መካከል መግባባትን ማስፈንን ነው:: ሁለተኛው አስተሳሰብ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን የሚመለከተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በአዲስ መሰረት … [Read more...] about የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ
Saudi Arabia: Labor Crackdown Violence
(Beirut) – Ethiopian migrant workers have been the victims of physical assaults, some of them fatal, in Saudi Arabia following a government crackdown on foreign workers. Many workers seeking to return home are being held in makeshift detention centers without adequate food or shelter. Human Rights Watch spoke to five Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia. Four Ethiopians in Riyadh told Human Rights Watch that the attacks began after November 4, 2013, when authorities resumed a … [Read more...] about Saudi Arabia: Labor Crackdown Violence
መንግስት – ስደት – ውርደት
ጀርመን አገር የምትታተመው ጥላ መጽሔት 8ኛ እትም ለንባብ በቅታለች። ለወቅታዊው ሁኔታም ልዩ ትኩረት ሰጥታለች። የሽፋን ስዕሉም ሙሉ ገፁን ለዚሁ ጉዳይ አውሎታል። (ሙሉውን መጽሔት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about መንግስት – ስደት – ውርደት
የጅዳ ሸረፍያ እስከ ሽሜሲ የተሰማው የወገን ዋይታና እዚህ ያደረሰን መንገድ!
ፈታኙን ወቅት ለማለፍ ... የሳውዲ የምህረት አዋጅ አልቆ በሪያድ መንፉሃ ላይ አለምን ያሳዘነ ሰቆቃ ተፈጸመ ...ስጋት ነግሶ ፣ ኑሮ ከብዶን ጨንቆን ጠቦን ከርመናል! በዚህ ክፉ ቀን ወገን ወገኑን ለመርዳት ደፋ ቀና በማለቱ ረገድ የሃገሬ ልጅ ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጭት ስሜት ሲንቀሳቀስ የፖለቲካው ትኩሳት ወላፈን እያጓተተን አልሰነበትንም አይባልም። ግልጥልጥ አድርግን እናውራ ካልን የኑሮ ውድነት እና ድህነቱ እየደቆሰን ቢያስቸግረን ከወገን ቤተሰቦቻችን ተለይተን ፣ የእማማ ኢትዮጵያውያን ምድር ለቀን በስደት ስንባዝን በደረሰብን የከፋ አደጋ ለመቋቋም ከምናደርገው ትግል ባልተናነሰ ልዩነትን የሚያገዝፉ መሰናክሎችን ማለፉ የከበደ አበሳ ሆኖብን ሰነባብቷል! በዚህ ፈታኝ ወቅት መፈተን ግድ ሆነና የዜጎች እንግልት ከሪያድ አልፎ ወደ ጅዳና አካባቢው ሲሸጋገር በርካታ ወገኖች በግልና … [Read more...] about የጅዳ ሸረፍያ እስከ ሽሜሲ የተሰማው የወገን ዋይታና እዚህ ያደረሰን መንገድ!