ጀግናው አሸለበ፣ ደከመው ተረታ ሞት አይቀርምና፣ የማታ የማታ፤ ምን ብርቱ ቢሆኑ፣ ሺ መካች ቢሆኑ ሰው አያልፍ አይገደፍ፣ ተዛቹ ተቀኑ፤ አፍሪካ ሆይ መጥኔ፣ አንድ ወልደሽ ላጣሽው ተንግዴ መሸበሽ፣ በማን ትዘከሪው? በማንስ ትጠሪው? ማንዴላ ብረቱ፣ የሮቢን ደሴቱ የዘረኞች ዋግምት፣ የጥቁር ኩራቱ- ተንግዲህ የለህም፣ ታሪክ ነበርክና ታሪክ ነህ ተንግዴ፣ ላትመጣ እንደገና፤ ዓለም አሸርግጂ፣ ቱቢት አስመቺና ደረት እየመታሽ፣ ”ወይ ልጄን...” በዪና፤ አንበሳሽ ቀን ጣለው፣ ይውጣልሽ ሀዘንሽ ሙሾሽን ደርድሪ፣ ማቅ ልበሽ እባክሽ ማንዴ እኮ ነው ሃጁ፣ ሌላው እንዳይመስልሽ፤ ባፍሪካ ሰማይ ላይ፣ የበራው ኮከብ ተወርዋሪ ነበር፣ ዐይንን የሚስብ፤ ባፍሪካ ሰማይ ላይ፣ የነጋው ጀምበር ለወገኑ ነበር፣ ብርሃንና አድባር ለጠላቱ ነበር፣ መራር እንደ ኮሶ ገፍናኝ … [Read more...] about አፍሪካዊው ኮከብ
Archives for December 2013
የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ
የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡ ስለቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣ የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንፀባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመሆኑ ዓለም አቀፍ … [Read more...] about የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ
ላምበሎቼ
በሕይወት እያላችሁ... ላለመዋደድ ተፋቅዳችሁ የኋላ ኋላ ኋላ... ባንዲት ጉድጓድ ታድማችሁ የኋላ ኋላ ኋላ... ምስጥና አፈር ላስማማችሁ የኋላ ኋላ ኋላ... ማንም ምንም ላይለያችሁ የኋላ ኋላ ኋላ... ተቃቅፋችሁ የኋላ ኋላ ኋላ... ላሸለባችሁ... ለናንተ... ላምበሎቼ ለጋሼ ኃይሌ ፊዳ ለጋሼ ብርሃነ መስቀል ረዳ እነሆኝ እላለሁ... ይህን ያገር እዳ፡፡ (በአበራ ለማ) “ጥሎ ማለፍ” ለተባለው የታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፌ መታሰቢያ ቋጥሬው የነበረ - 2003 ዓ.ም. … [Read more...] about ላምበሎቼ
ኢትዮጵያን በሙስና ከሚታወቁ የዓለም አገሮች ተርታ ያሰለፈው ሪፖርት ይፋ ሆነ
ትናንት ኅዳር 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በመላው ዓለም ይፋ የሆነው የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ተቋም የሙስና አመላካች ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ከሙስና ጽዱነት ተርታ ውጭ ከሆኑና በሙስና ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈረጁ አገሮች አንዷ ሆና መገኘቷን ይፋ አደረገ፡፡ ሪፖርቱ በሚከተለው የሙስና መለኪያ ሚዛን መሠረት፣ ከሙስና ጽዱ የሚባሉ አገሮች ከዘጠና እስከ መቶ ነጠብ የሚያገኙት ናቸው፡፡ በአንፃሩ ከፍተኛ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል፣ የሙስና ጎሬ ሆነዋል ተብለው የሚታሰቡ አገሮች ደግሞ ከመለኪያው ከ50 በመቶ በታች የሚያስመዘግቡት ናቸው፡፡ በመንግሥት ተቋሞች ውስጥ ከፍተኛ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል ተብለው ከተለዩት ውስጥ ኢትዮጵያ 33 ከመቶ የመለኪያውን ነጥብ በማስመዝገብ ከከፍተኛ ሙስኞች ተርታ እንደምትሰለፍ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ከ177 አገሮች ውስጥ … [Read more...] about ኢትዮጵያን በሙስና ከሚታወቁ የዓለም አገሮች ተርታ ያሰለፈው ሪፖርት ይፋ ሆነ
አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ ሁለት
አበሻ ድግስ ይወዳል፤ ድግስ የሚወደው መብላትና ማብላት ስለሚወድ ነው፤ ለመብላት የአበሻ ምክንያቱ ብዙ ነው፤ ልጅ ተወለደ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ክርስትና ተነሣ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ አገባ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ሞተ ብሎ መብላት ነው፤ አበሻ ሰው ቀብሮ ሲመለስ በንፍሮ ይጀምርና ቀስ በቀስ ወደሌላው ይተላለፋል። ሃይማኖትም ቢሆን ለመብላት ካልሆነ የነፍሱ ጉዳይማ በጣም ሩቅ ነው፤ ሕያዋን ለነገሥታት፣ ሙታን ለካህናት ይገብራሉ፤ በሚለው መመሪያ መሠረት ግብር መቀበል ያለ ነው፤ ክርስቶስ ተወለደ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተጠመቀ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ሞተና ተቀበረ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተነሣ መብላት ነው፤ ማርያም አረገች መብላት ነው። ማኅበርም የሚጠጣው (የሚበላው ለማለት ነው፤) ለመብላት ነው፤ አምላክ በተለያዩ ስሞቹ፣ ቅድስት ማርያም በተለያዩ ስሞችዋ፣ መላእክት፣ ቅዱሳን፣ … [Read more...] about አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ ሁለት
ከሰማይ የራቀችው ምድር ከምድሪቱ የራቀው ሰማይ
ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ‹‹መንግሥት›› ስደትን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ባልነበረው ትኩረት ያስቆጨውና ያሳሰበው መስሎ በመታየት በሕዝብ የብዙኃን መገናኛዎች የተለያዩ ዲስኩሮችን እያደረገ ይገኛል ፡፡ ሲጀመር ገዥው ፓርቲ (ቡድን) የዜጎችን ስደት በተመለከተ ማንነቱን አሳምሮ ለሚያውቀው ሕዝብ ምንም የማለት የሞራል (የግብረ-ገብ) ብቃት ጨርሶ አልነበረውም፡፡ ራቅ ካለው ታሪኩ እስከ ቀረብ ካለው ከዚያም እስከአሁን ካለው ታሪኩ አሁን ባለበት ሁኔታም ተስፋ የሚሰጥ ምንም ነገር ባለመኖሩ ነገም ከሚኖረው ታሪኩ ስንመለከት ይሄንን ክስ የሚያስተባብል ሆኖ አናገኘውም ፡፡ ከዚህ አንጻር ትኩረቱን በጣም አጥቦ በአራቱም አቅጣጫዎች በእግር እግራቸው ወደ አመራቸው በሚሰደዱ ታዳጊ ሕፃናትና ወጣቶች ላይ ማድረጉ በቦሌ በኩል በተለያየ ጫና ፣እንግልትና ውክቢያ ሳይወዱ ሀገራቸውን ጥለው በሚሰደዱት፤ ሕዝቡ … [Read more...] about ከሰማይ የራቀችው ምድር ከምድሪቱ የራቀው ሰማይ
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ኅዳር 23፣ 2006 ዓም ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው! ግልጽ ደብዳቤ ለሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/የሱስ ____________________________________________________________ ለዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም፤ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ኢትዮጵያውያንን በቀለም፣ በዘር፣ በጎሣ፣ በቋንቋ፣ በጾታ፣ በክልል፣ ወዘተ ሳይከፋፍል በየትኛውም የዓለም ክፍል (ኢትዮጵያንም) ጨምሮ የሚደርስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ማኅበራዊ ኢፍትሃዊነት ለመከላከል፣ ለማስቆም፣ ለማጋለጥ፣ ወዘተ እና ባሉበትም ቦታ ሁሉ ከፈጣሪ የተሰጣቸውን መብት ለማስጠበቅ የቆመ ድርጅት ነው፡፡ ሆኖም … [Read more...] about ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ለነ ድንጋይ ልቡ
ካላየህ ከልነበርክ ሕሊና ከሌለህ፣ ግድ የለም ይመችህ፤ ወሬህን አሳምር አፊዝ እሞቀህ ቤት፣ ቁስሉ የሰው ነው እንጨት ስደድበት፤ አንድ ቀን ጀንበርህ የጠለቀች ዕለት፣ እስቲገለጽልህ ያለህበት ሌሊት፤ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለነ ድንጋይ ልቡ
ETHIOPIANS IN LONDON ECHO THE PLIGHT OF THEIR COMPATRIOTS IN SAUDI ARABIA
London residents of Ethiopia came out again on 2 December 2013 to protest in front of the Saudi Arabian Embassy for the 2nd time in less than 10 days. Although we are aware that some Ethiopians have been transported to Addis Ababa, there are still tens of thousands of Ethiopian immigrants in captivity in that Kingdom, held in subhuman conditions, without food, and sanitary for women. Horrendous news trickling out to the rest of the world through various sources tells gross violation of human … [Read more...] about ETHIOPIANS IN LONDON ECHO THE PLIGHT OF THEIR COMPATRIOTS IN SAUDI ARABIA
አቶ ታምራት ላይኔ እንዳደመጥኳቸው
የቀድሞው የኢትዮጵያ የሽግግር ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ኋላ ላይ ደግሞ የኢፊድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ ከአውስትራሊያዊው የኤስ.ቢ.ኤስ የአማርኛ ራዲዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ጋር ያደረጉትን በሶስት የተከፈለ ሰፊ ቃለመጠይቅ በአንክሮ ተከታተልኩት:: አቶ ታምራት ብዙ ነገሩን፤ ብዙ ደበቁንም:: ከምንም በላይ አቶ ታምራት በረጋ አንደበት ከቁጣ እና ከብስጭት የጸዳ ቃለምልልሳቸውን በዚህ አጋጣሚ ሳላደንቅ አላልፍም:: እርግጥ ነው ቃለመጠይቁ ሰፊ ቢሆንም በደምሳሳው አቶ ታምራት በመለስ ዜናዊ ተታለልኩ የሚል ቃና ያለው መልዕክት እንዳስተላለፉ ነው የተረዳሁት:: ከምንም ነገር በላይ አሁን ከሚከተሉት ሃይማኖት ጋር አያይዘው ቢሆንም ኮሚኒዝም አንደርዮት አለም በፍጹም የስሕተት እና የጥፋት መንገድ አንደነበር በአደባባይ መናገራቸው ለኔ ታላቅ ቁም ነገር ሁኖ … [Read more...] about አቶ ታምራት ላይኔ እንዳደመጥኳቸው