ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው። በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው። ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው። ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ … [Read more...] about የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ?
Archives for October 2013
Ethiopia: The 65 Percent and Political Consensus
Ethiopia’s population is predominantly young. This is according to the United States Central Intelligence Agency July 2013 estimate of Ethiopia’s population: 0-14 years olds are 44.4% of population, while the 15-24 age group is 19.9% of the population. The sum of the under 24 year old demographics is 65% of Ethiopia’s population, which amounts to more than 60 million people. (The 44.4% is more than 41 million, the 19.9% a little under 20 million). Our country’s young population is coming of … [Read more...] about Ethiopia: The 65 Percent and Political Consensus
እባብ ለእባብ፣ ይተያያል በካብ
የለንደኑ ጸረ-ሕዝብ አመጸኛ፣ አንድ እርምጃ ሲወስዱ፣ ሕዝቡ ሁለት እርምጃ ቀድሞአቸው ይጠብቃቸዋል። ሲበዛ ተንኰለኛ በመሆናቸው፣ አንድ ቀን ተሳስተውም ደግ ነገር ሠርተው ቢገኙ፣ የሚያምናቸው ሰው አይኖርም። በዓይነ ቁራኛ ነው እንቅስቃሴአቸውን የምንቆጣጠረው። በዕውነት ተጸጽተው እንኳን ቢያለቅሱ፣ የአዞ ዕምባ ብሎ ነው ሰው የሚሸሻቸው። አሁንም ተነቃቅተናል። አባ ተባዩ አስመሳይ መነኵሴ፣ የሚጠቅማቸው መስሎአቸው፣ ለወየኔ የመሽሎኪያ ቀዳዳ አበጀተውለት አስጠቁን። “የአስተዳደር መዋቅሩ አይሻሻልም፣ እኔም ከሥልጣኔ አልወርድም” - እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ሁኖባቸው ለወያኔ ወደው ገብተው እኛን በሶልዲ ሸጡን። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) (Click here to read the report and video by the local Guardian) … [Read more...] about እባብ ለእባብ፣ ይተያያል በካብ
ስንቱን አጣን!
እንደኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደአሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት … [Read more...] about ስንቱን አጣን!
የአዘርባዣኑ ኢህአዴግ
ትላንት ረቡዕ በአዘርባዣን የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ነጻና ፍትሓዊ እንደማይሆን የብዙዎች ግምት ነበር፡፡ ከ10ዓመት በፊት ከአባታቸው ሥልጣን በውርስ የተረከቡት ፕሬዚዳንት ዒልሃም አሊዬቭ የጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በመገደባቸው የምርጫው ውጤት ምን እንደሚሆን ለመገመት ያዳገተ አልነበረም፡፡ እንደ ኢቲቪና ሬዲዮ በአገሪቷ መንግሥት የሚቆጣጠረውና ለገዢው ፖለቲካ መሣሪያነት የዋለ ሚዲያ በመኖሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የነጻ ንግግር ገደብ እንዳሳሰባቸው ሲጠቁሙ ቆይተዋል፡፡ ቢቢሲም የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የተወሰነ መሆኑን ዘግቦ ነበር፡፡ ምርጫ ተካሂዶ ቆጠራው ከመፈጸሙ በፊት የአዘርባዣን ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚሽን ለብልህስልኮች (smartphones) አዘጋጅቶ የለቀቀው ግብረታ (app) ፕሬዚዳንቱ በ72.76 በመቶ ማሸነፋቸውን የሚያሳይ ነበር፡፡ እኤአ በ2003 … [Read more...] about የአዘርባዣኑ ኢህአዴግ
“የይሉኝታ ፖለቲካ ይገድላል”
“ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ትላለች። የተወለደችው ዱከም ነው። በቀድሞው አጠራር በኢትዮጵያ የተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች ኖራለች። ሐረር፣ ባህርዳር፣ አስመራ፣ አዲስ አበባን በመጥቀስ ልዩ ትዝታዎች እንዳሏት ትናገራለች። ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት አሜሪካ ከትማለች። “ፖለቲከኛ አይደለሁም፣ እኔ አገር ወዳድ ነኝ። አገሬ የማንኛውም ጉዳዮቼና የውሳኔዎቼ በሙሉ መለኪያ ሚዛኔ ናት" ትላለች። ለአገሯ ማድረግ የሚገባትን እንዳላደረገች ይሰማታል። የይሉንታ ፖለቲካ ችግርና መዘዝ ያሳስባታል። በመናገርና ሃሳብን በነጻነት ስለመግለጽ ያላት አቋም የጸና መሆኑን አትደብቅም። በማህበራዊ ገጾች ንቁ ተሳታፊና መረጃ በማስተላለፍ በርካታ ተከታታዮች አሏት። በኢትዮጵያውያን የወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ አስተባባሪ ከሆኑት አንዷ ኃላፊ (አድሚን) ናት። ቤተሰቦቿ ካወጡላት መጠሪያዋ ይልቅ ራስዋ ለራስዋ ስም ተክላለች። … [Read more...] about “የይሉኝታ ፖለቲካ ይገድላል”
ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል
በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት "ባለሃብት" በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል። የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር። ሳዑዲ ስታር የስራ አቅሙ ተገምግሞ መሬት እንደሚጨመርለት ቃል ቢገባለትም … [Read more...] about ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል
The Secret (ሚስጢሩ…)
ሚስጢሩ አሁን በሀይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤የተግባር ሀይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው።ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ? ያሁኑ ማንነታችን ያለፈው አመለካከታችን ውጤት ነው። ቡድሃ የየቀኑ ምስጋናህ ፀጋ ወደ አንተ የሚመጣበት ማስተላለፊያ ቀዳዳ ነው ዋላስ ዋትልስ መተንበይ ሁሉንም ነገር ነው።የህይወት መጻኢ መስህቦች ቅድመ እይታ ነው። አልበርት አንስታይን ሀይለኛው ሂደት የምትፈልገውን አጥብቀህ መጠበቅ ሊረዳህ ይችላል ፍላጎት እንዳይርቅ ስትተኛም ሆነ ጠዋት ስትነሳ በያንዳንዱ ነገር ማመስገን አትርሳ በጅህ ባለ ነገር ማመስገን ስትጀምር መንገድ ትፈጥራለህ ሌላ ለመጨመር የምትፈልገውን በዓይነ ህሊና አስቀድመህ አይተህ አስተካክለውና ማግኘትህን … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
ፓለቲካዊ መግባባት እና 18 የፓልቶክ ታዳሚዎች
ይህ ጥያቄ እና መልስ ከ18 የፓልቶክ ታዳሚዎች ጋር ስለ ፓለቲካዊ መግባባት ("ብሄራዊ መግባባት") የተደረገ ነው። ጥያቄ እና መልስ የተደረገበት ጊዜ ከSeptember 16-20, 2013 ሲሆን ፡ ጠያቂ አቶ ያዬ አበበ ነው (Paltalk nick name: Beruhan)። የዚህ ጥያቄ እና መልስ አላማ የፓልቶክ ታዳሚዎች ስለ ፓለቲካዊ መግባበት ያለቸውን ግንዛቤ ለማሰስ ሲሆን ፡ በተጨማሪ የአሰሳውን ውጤት በመጠቀም ስለ ፓለቲካዊ መግባባት በዲያስፓራ መወያያ መድረኮችና ሚዲያዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥና ጥልቀት ያለው የፓለቲካ ውይይት የሚፈጥር ጥንስስ ለመጀመር ነው። ((ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)) … [Read more...] about ፓለቲካዊ መግባባት እና 18 የፓልቶክ ታዳሚዎች
አባ አጋግዮስ
ባለፈው ሳምንት የዘንድሮውን የደመራ በዓል አከባበር በዜና ማሰራጫዎች የተመለከቱ ግሪካዊ ቄስ ባነሱት ጥያቄ የተቀሰቀሰብኝን ስሜት፤ ለዚህች ክታብ መግቢያ ላደርገው ፈለኩ። “ባገርህ የተደረገውን የመስቀሉን በዓል በመገናኛ ዘዴወች አይቼው በጣም ደስ ይላል። ሄደህ ነበር? ብለው ጠየቁኝ። “አልሄድኩም” አልኳቸው። “ለምን አልሄድክም? ብለው መልሰው ጠየቁኝ። ያሰለቼኝ ጥያቄ ስለሆነ የጥያቄቸውን መስመር በመቀየር “እርስዎን ምኑ ነው ያስደሰተዎ? ብየ ጠየኴቸው። “አከባበሩ ደስ ይላል” አሉኝ። “የእርሰዎ መንፈስ የተማረከው ባከባበሩ መብልጭልጭ ነው። የኔን መንፈስ የሚማርከው ደግሞ በበዓሉ የሚወሱት እነ ቆስጠንጢኖስ፤ ዲዮቅልጥያኖስ፤ እነ ቅድስት እሌኒና የአባ አጋግዮስ አስከፊ ባህርይ ነው። ከዚህም ጋር ደመራ የሚለው የበዓሉ መጠሪያ እንደሚያመለክተው፤ ከልጅነት ጀምሮ ለበዓሉ የክብር መርገፎች … [Read more...] about አባ አጋግዮስ