በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለፍትህ ሚኒስቴር በይቅርታ እንዲፈታ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከፍትህ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደተገለፀላቸው ባለቤቱ አስታወቁ። የጋዜጠኛ ውብሸት ባለቤት ወይዘሮ ብርሃኔ ተስፋዬ ለሰንደቅ እንደገለጹት፤ “ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ከፍትህ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ፈርሞ ተረክቧል። በደብዳቤው የጠየቀው ይቅርታ እንዳልተፈቀደለት በሁለት መስመር ከመግለፁ ባለፈ ይቅርታው ለምን ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚገልፅ ኀሳብ አልያዘም” ብለዋል። አያይዘውም፣ “ከዚህ በፊት የአቶ ኤልያስ ክፍሌ እህት የሆኑት ወ/ሮ ሂሩት ይቅርታ ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር ምክንያቱ ተገልፆ ነበር። ለውብሸት ግን ምክንያቱ አልተገለጸም። ጉዳዩን ለማወቅ ለፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቤ ነበር። የውብሸት ደብዳቤ ወጪ ተደርጓል። … [Read more...] about የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ የይቅርታ ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ
Archives for September 2013
የሐምሌ ጨረቃ
በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ፡፡ ይህ ኩነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እንደ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ከኋላቀሩ የፖለቲካ ባህላ የተላቀቁ አለመሆናቸው ነው፡፡ እናም አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስጀመር ከመስራት ይልቅ ሳያውቁት ከዘመነ-መሳፍንት የተቀዳውን የፖለቲካ ባህል በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ዛሬም ይታያሉ፡፡ የእስከ ዛሬውን የከሸፈ ሂደት የገመገመና የኢትዮጵያን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ከተጫነበት የጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ … [Read more...] about የሐምሌ ጨረቃ
የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!
ያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡ በዕለቱ እንደሆነው የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከመውረራቸው በፊት ኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠዋል፡፡ በቀጣዩም ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረጉ የነበሩትን አመራሮችና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ዘግናኝ በሆነ … [Read more...] about የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!
ሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፉን ቀን ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም አስተላለፈ!!
ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!! ሰማያዊ ፓርቲ ለነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጠርቶት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂ ኋይሎች ሕገ-አራዊት እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ፓርቲያችን ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጳጉሜ 2 ቀን 2005ዓ.ም ሠልፉ በድጋሚ እንደሚካሔድ አስታውቋል፡፡ ሠልፉ የተሳካና ሰላማዊ እንዲሆን በፓርቲ በኩል ልዩ ልዩ ተግባራት ከመከናወናቸው ጎን ለጎን አስፈላጊው የጸጥታ ጥበቃና የአስተዳደር ድጋፍ እንዲሰጠን በህጉ መሰረትም ሠልፉ እውቅና እንዲያገኝ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሰወቂያ ክፍል ነሐሴ 27 ቀን 2005ዓ.ም ደብዳቤ ለማስገባት በአካል ተገኝተን ጠይቀናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ክፍል ደብዳቢያችንን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ በፓርቲው በኩል በሁኔታው ተስፋ ባለመቁረጥ በኢትዮጵያ ፖስታ … [Read more...] about ሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፉን ቀን ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም አስተላለፈ!!
አጭር ማስታወሻ በሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሠልፍ
ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደሰፈር ጉልበታኛ ዱንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በሃይማኖት ስበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በህግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተቃውሞ ሠልፍ በማድረግ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሠልፈኞች እንዲሁም የአገር ውስጥና የውጪ የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት መንግስት ሊመልሳቸው የሚገባ ጥያቄዎችን የጠየቀ ሲሆን ለጥያቄዎቹም ምላሽ የሰጠው የጊዜ ገደብ ሦስት ወር መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት በተሰጠው ጊዜ የተጠየቀውን ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ፓርቲውን በመወንጀል እና ስም የማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ … [Read more...] about አጭር ማስታወሻ በሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሠልፍ
የአክሰስ ሪል ስቴት ደንበኞች አቶ ኤርሚያስን በጋራ ለመፋረድ ተስማሙ
በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ከ2,500 በላይ ደንበኞች የአክሰስ ሪል ስቴት መሥራች፣ ሥራ አስኪያጅና የቦርድ ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን፣ በጋራና በአንድ አቋም ሆነው ለመፋረድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባደረጉት ስብሰባ ተስማሙ፡፡ ቤት ገንብተው ሊያስረክቧቸው ባደረጉት ስምምነት ሩብ፣ ግማሽና ሙሉ ክፍያ መፈጸማቸውን የሚናገሩት ደንበኞች፣ አቶ ኤርሚያስን በጋራ ለመፋረድ የተስማሙት፣ ገንዘባቸውን ለማስመለስ በተናጠል ወደ ፍርድ ቤት መሄዳቸውንና የሪል ስቴቱ ንብረት ነው በሚል ንብረት ለማሳገድ ወይም የኪሳራ ውሳኔ ለማስወሰን መንቀሳቀሳቸውን በመተው፣ አቋማቸውን አንድ በማድረግና በመስማማት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተወሰኑት በተወካዮቻቸው፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ራሳቸው በስብሰባው ላይ በመገኘት በቅርቡ … [Read more...] about የአክሰስ ሪል ስቴት ደንበኞች አቶ ኤርሚያስን በጋራ ለመፋረድ ተስማሙ
ደቡብ ክልል ሪፖርተርን በህግ እጠይቃለሁ አለ
የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የደቡብ ክልል የመንግስት ጉዳዮችን ጠቅሶ እንደዘገበው "ሪፖርተር ጋዜጣ 3ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ በማለት ያወጣው ዘገባ መሰረተ ቢስ" ብሎታል። ይሁን እንጂ ሪፖርተር ከሃላፊነታቸው ተነሱ ያላቸው ሶስት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች በስልጣን ላይ ስለመኖራቸው ያለው ነገር የለም። ዜናውን አስተባበለ፣ ጉዳዩንም ወደ ህግ ሊወስድ ዛተ የተባለው የክልሉ የመንግስት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተጠቀሰበት ዜና ከዚህ የሚከተለው ሲሆን፣ ዜናው ከሪፖርተር በኩል ስላለው የዜናው መረጃ እውነተኛነት አላካተተም። ሪፖርተር ለሰራው ዜና ምንጮቹ የተሳሳቱ ከሆነ ዜናውን ቀደም ሲል በሰራበት መጠንና ቦታ ይቅርታ ለመጠየቅና ራሱን በራሱ ማስተባበል ይጠበቅበታል። ዜናው እንደሚከተለው ይነበባል:- ሪፖርተር ጋዜጣ 3ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች … [Read more...] about ደቡብ ክልል ሪፖርተርን በህግ እጠይቃለሁ አለ
የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ
የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡ የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው … [Read more...] about የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ
የሙስናው ጉዳይ
በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች "ጸዳ" ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ። በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው። አቶ ነጋም ለጥሪው እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው … [Read more...] about የሙስናው ጉዳይ
የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ተከሰሱ!!
ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አዲስ አበባ አመልካች፡- ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው ጉዳዩ፡- በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ (በአየር ሞገድ በሚሰራጩ የብዙኃን መገናኛዎች) በፖለቲካዊና በሕገወጥ መመሪያዎች የመደመጥ ወይም የመስተናገድ ዕድል ስለመነፈግ በአየር ሞገድ የሚደመጡ የብዙኃን መገናኛ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚለቀቁ ዘፈኖች በአንድ ነጠላ ርእሰ ጉዳይ ላይ ማለትም በጾታዊ ፍቅር ላይ ብቻ ማተኮር እና ከያኔያኑም ቀድሞ ከነበረን የኪነት አትኩሮት በተቃራኒው ሀገርን ወደፊት ሊያራምዱ የሚችሉ፣ ትውልድን የሚቀርጹ ማለትም ሥነ-ምግባሩን ሥነ-ልቦናውንና ሰብእናውን የሚያንጹ ስንት ቁምነገሮች እያሉ ይህንን ርእሰ ጉዳይ ብቻ ያውም አንጋዶ ማለትም ከግብረ-ገባዊ አመለካከት አንጻር ትክክል ባልሆነ አቅጣጫ ሙጥኝ ብሎ መቅረት አገራችን ድሀ እና ልማት የጠማት ሀገር ከመሆኗ አንጻር … [Read more...] about የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ተከሰሱ!!