የመጽሐፉ ርእስ.................. ትውልድ ያናወጠ ጦርነት ደራሲ.................................. ንጋቱ ቦጋለ (ሻለቃ) አሳታሚ............................... በግል አታሚ.................................. ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ የሕትመት ሥራ የገጽ ብዛት............................ 341 ዋጋ........................................ 55 ብር ቅኝት..................................... በአበራ ለማ ". . . የሽሬ ውጊያ ብሎም በትግራይ ውስጥ የነበረው የመንግሥት ጦር አመራር በነመጋቢ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋው ችሎታ ማነስ ምክንያት፣ ምን ያህል ተፍገምግሞ እንደወደቀ ደህና አድርገህ ገልጸህዋል፡፡ መጋቢ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋው ጀምለው በያዙት … [Read more...] about ትውልድ ያናወጠ ጦርነት
Archives for June 2013
የአባይ ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት ወይንስ የነፃነት ትግላችን!
አምባገነኖች ስልጣናቸውን ለማጠባበቅ አጋጣሚውን ሁሉ ይጠቀማሉ። ሰሞኑን የአባይን ግድብ አስታከው አምባገነኖቹ ህውሃት/ኢህአዴግ እና የግብጽ መንግስት መምታት የጀመሩት የጦርነት ከበሮም ከዚህ የተለየ አይደለም። የህዝባቸውን ብሄራዊ ክብር ስሜት ተቆጣጥረው የዲሞክራሲ ኃይሎችን ለማዳከም እና ስልጣናቸውን ለመጠጋገን የሚያደርጉት ድራማ ነው። ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት አይቀሬ አይደለም። የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች ወደ ጦርነት አይሄዱም። የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ወታደር አይኑን ከነፃነት ትግሉ መንቀል የለበትም። የአባይ ወንዝ የሚጓዝበትን ሽምጥ ሸለቋማ ክፍል የአዲሱ ግድብ አካል ቢደረግ ግድቡ ሰፊ ቦታ እንዳይዝ፣ ውሃው ለጸሐይ ብዙ ተጋልጦ እንዳይተን እና መጠኑ እንዳይቀንስ ይረዳል። የግድብ ግንባታ ወጪም ይቀንሳል። ይኽን ተፈጻሚ ለማድረግ ደግሞ የአባይን ወንዝ ለጊዜው አቅጣጫውን ማስቀየር … [Read more...] about የአባይ ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት ወይንስ የነፃነት ትግላችን!
አባይ የኢህአዴግ ኤአርቲ!
Nile River, Arabic Baḥr Al-Nīl or Nahr Al-Nīl river, the father of African rivers and the longest river in the world. It rises south of the Equator and flows northward through northeastern Africa to drain into the Mediterranean Sea. Encyclopedia Britannica. በዓለማችን በግዙፍነታቸው ከሚወደሱትና አንቱ ከተባለላቸው ወንዞች መሃል የአባይ ወንዝ /Blue Nile/ግንባር ቀደሙ ነው።ከ6ሺ ኪሎሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው የኣለማችን ግዙፉ ወንዝ በርካታ አገሮችን እያቋረጠ የሜዲትሪያንያን ባህርን ይቀላቀላል። አባይ የሚያቋርጥባቸው አገሮች ደም ስር ሆኖ በማገልገልም ላይ ይገኛል።ምንም እንኳን የአባይ ወንዝ ምንጭና የ80 በመቶ ባለድርሻ … [Read more...] about አባይ የኢህአዴግ ኤአርቲ!
ታላቅ ሕዝባዊ የስብሰባ ጥሪ
ኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል በአገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር ቅዳሜ ጁን 22 ቀን 2013 ሕዝባዊ ስብሰባ አዘጋጅቷል። በዕለቱም የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በክብር እንግድነት ይገኛሉ። ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን ከምሽቱ 8:00 ጀምሮ በኢየሩሳሌም ከተማ በያፎ 97 ብንያን ክላል ሕንጻ እንዲገኙና የበኩልዎን ተሳትፎ እንዲያደርጉ አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪውን ያቀርባል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 054-2950990 ወይም 052-4062853 ይደውሉልን አስፈላጊውን መረጃ ልንሰጥዎ ዝግጁ ነን። አስተባባሪ ኮሚቴው … [Read more...] about ታላቅ ሕዝባዊ የስብሰባ ጥሪ
ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?
በግብጽ ረዳትነት፣ በሱዳን መሪነት መንግስት ለመሆን የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ግዙፉን የጣና በለስ ፕሮጀክትና ንብረቱ እንዲዘረፍ ያደረገበትን ምክንያት በማንሳት መከራከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ እንዳደረጉት በአገር ጉዳይ ሁሉንም ያሳተፈ ግልጽ አቋም እንዲያዝና አጋጣሚውን በመጠቀም ብሔራዊ ህብረት እንዲፈጠር ኢህአዴግ በሩን ሊከፍት እንደሚገባ ተገለጸ። በተለያዩ ጉዳዮች ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ በማሳሰብ ለጎልጉል አስተያየት የሚሰጡት የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት በርካታ ጉዶች ያሉበትን የአባይን ግድብ ተከትሎ ከግብጽ ጋር የተነሳው ውዝግብ አስቀድሞ የሚታወቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ስልትና ውጤት ነው። አሁን ድረስ አገር እየመራ በነጻ አውጪ ስም የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ "ዲሞክራሲ አመጣሁ" በማለት ኢትዮጵያን መምራት እንደጀመረ የሚያወሱት … [Read more...] about ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?
ምርጫ፦ ህወሃት ወይስ ግብጽ?
አቶ መለስ ዜናዊ የአባይ ግድብን ለመገንባት መስተዳደራቸው መቼ እንደወሰነ ሲጠየቁ ውሳኔው ከ2002 ዓ.ም. በኋላ እንደሆነ ተናግረው ነበር። አቶ መለስ በአንጎላቸው ውስጥ የነቀርሳ ዕጢ እንዳለባቸው ያወቁት ከ2002 ዓ.ም. በፊት ነው። እንግዲህ የቀድሞው ጠሚራችን (ጠቅላይ ሚኒስትራችን) አባይን ለመገንባት ለምን እንደተመኙ ስጠራጠር ምናልባት የሳቸው መስተዳደር የፈጠረውን አገራዊ መከፋፈል እና የራሳቸውን ታሪካዊ ትሩፋት (legacy) ለማግነንና ለመቤዤት ጭምር ሳይሆን አይቀርም። የቀድሞው ጠሚራችን ህመማቸው እንደሚገላቸው ያዉቁ ነበር ቢባል ማጋነን አይመስለኝም። አቶ መለስ ታሪክ በበጎ አይን እንዲያያቸው አባይን መገደቡን ጥሩ አማራጭ አርገው አግኝተውታል። አባይ የሚገደበው በአማራ ክልል ውስጥ አይደለም ፤ በቤንሻንጉል እንጂ። አባይ የኢትዮጵያውያን መንፈስን በቁጪት ጠፍሮ ያሰረ … [Read more...] about ምርጫ፦ ህወሃት ወይስ ግብጽ?
አገዛዙ ለሰላማዊ ሰልፉ ዕውቅና የሰጠው ፈጽሞ አማራጭ ስላልነበረው ነው – በእኔ አመለካከት!
ሕወሓት/ኢህአዴግ በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት የተካሄደውን ሰላማዊ ዕውቅና የሰጠው ወድዶና ፈቅዶ ወይም ሕገ-መንግሥቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከትቶት አልነበረም። ይልቅስ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ሁለት ነገሮች ናቸው ፡- 1ኛ - ወቅታዊነት! በወቅቱ የሚካሄደውን ርዕሰ-ሃገራትና ከፍተኛ የዓለም ባለሥልጣናት (እንደ ጆን ኬሪ እና ባንኪ ሙን) በተገኙበት እንዲሁም በዓለም መገናኛ ብዙሃን እየተዘገበ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት ጉባዔ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና መጠየቁ፣ 2ኛ - መደራጀት፣ ብስለት እና ቁርጠኝነት!!! የሰማያዊ ፓርቲና አመራሩ መደራጀት፣ ብስለት እና ቁርጠኝነት፤ ሕወሓት/ኢህአዴግ ከለመዳቸው የከሸፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግደርደሮች (ከይቅርታ ጋር በርካታ የከሸፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮች እንዳሉም ጭምር እምነት አለኝ) የተለየ መሆኑን … [Read more...] about አገዛዙ ለሰላማዊ ሰልፉ ዕውቅና የሰጠው ፈጽሞ አማራጭ ስላልነበረው ነው – በእኔ አመለካከት!
ግንቦት 25 /2005/
የ ኢትዮጵያ 21ኛው ክፍለ፥ዘመን የተጀመረበት ቀን ሊሆን ይችላል! ትግሉ እንዲቀጥል፣ አንዳንድ ቁም ነገሮች… አንደኛ - በተለይም የግብጽ ወጣቶች በምን ዘይቤና ብልሃት ወደ ህዝቡ ልቦናና መንፈስ ወስጥ ሰርጸው በመግባት፣ በሰላማዊ አመጽ፣ በአልገዛም ባይነት፣ ያን እስተአፍጢሙ ድረስ የታጠቀን የሙባረክ መንግሥትን እንዴት እንዳምበረከኩ፤ (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ግንቦት 25 /2005/
ኦባንግ ለኃይለማርያም ግልጽ ደብዳቤ ላኩ
ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውንና በሰላም የተጠናቀቀውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ ኢህአዴግ ሰልፈኞቹንም ሆነ የፓርቲውን አመራሮች ለማሠር የሚያደርገውን ሃሳብ ከመፈጸም እንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡ አቶ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ላይ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን በቅድሚያ ግን ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ሠልፉን በመፍቀዳቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ ከቀድሞው መሪ መለስ እንደሚለዩና ምናልባትም ህዝብን ለማዳመጥ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቋሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ መለስ በእንደዚህ ዓይነቱ ሠልፈኞች ላይ የህወሓት አልሞ ተኳሾች ተኩስ በመክፈት እንዲገደሉ ማድረገቸውና የፓርቲ አመራሮችን … [Read more...] about ኦባንግ ለኃይለማርያም ግልጽ ደብዳቤ ላኩ
“ይህ መንግሥት አይመጥነንም”
ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው። በወጣት አመራሮች የተገነባውና በርካታ ሴት አባላት እንዳሉት የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዋናነት የተገኘው ድል የፍርሃት ደመና መገፈፉ ነው። አቶ መለስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ በ1997 ዓ.ም ዜጎች አልመው በሚተኩሱ የአጋዚና ታማኝ የህወሃት አባሎች ደረትና አናታቸው እየተወጋ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ የማይታሰብ ሆኖ ላላፉት ስምንት ዓመታት ቆይቶ ነበር። ከዳር እስከዳር ድምጽ አልባ ሆኖ የተሸነፈው ኢህአዴግ በጠመንጃ ፣ በወቅቱ የነበሩት የቅንጅት አመራሮች ታሪካዊና ሊረሳ የማይችል ስህተት ተዳምረው የህዝቡን … [Read more...] about “ይህ መንግሥት አይመጥነንም”