ጀግንነቱን ዓለም መስክሮለታል፣ ስሙን ከፍ አድርጎ ጠርቶታል፣ ታሪክ በማይጠፋ ቀለም፣ በማያረጅ ብራና አስፍሮታል፡፡ ጠላት ሮጦለታል፣ በስሙ ተሸብሮለታል፣ ከእግሩ ሥር ወድቆ ይማሩኝ ንጉሥ ኾይ ብሎለታል፡፡ በጀግንነቱ በጠላቶቹ ልብ ላይ የነገሠ፣ በዝናው ዓለምን ያዳረሰ፣ የጠላቶቹን አንጀት የበጠሰ፣ የወዳጆቹን አንጀት ያራሰ ጀግና ነው እርሱ፡፡ የማይገመት ልብ ያለው፣ ጠላት የማይችለው፣ ጀግንነት፣ ብልሃት፣ አሸናፊነትና ጽናት የታደለው ኃያል ንጉሥ፡፡ ነጭ ባየለበት ዘመን በነጭ ላይ የገነነ፣ የነጭን ኃያልነት የበጣጠሰ፣ የነጭን አብዮት ያፈራረሰ፣ የጥቁርን ክብር የመለሰ፣ ያለቀሱትን እንባቸውን ያበሰ፣ በጨለማ ውስጥ ለነበሩት የደረሰ፣ በድል ብቻ የገሰገሰ፣ በጨለማው ምድር ብርሃን ያበራ፣ ከተራራ የገዘፈ፣ ዘመናትን በክብር ያለፈ ታሪክ የሠራ፣ የጥቁር አባት፣ የነጻነት መሪ፣ … [Read more...] about ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው
Opinions
የኔ ሃሳብ
“ነገርን ከሥሩ ውሃን ከጥሩ”
የአማራ ሕዝብ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት ባልነበረበት፣ የግንኙነት አውታሮች እጅግ ኋላ ቀር በሆኑበት ሁኔታ አንድነቱን አስጠብቆ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ገንብቷል። የባህል መስተጋብሩና ሌሎች ማህበራዊ እውነታዎቹ ከራሱ አልፎ ኢትዮጵያን ድርና ማግ ሆኖ አስተሳስሯል። የሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች (ክርስትና እና እስልምና) መንፈሳዊ መሪዎች መፍለቂያ መሆኑ አጥር የማይበጅለት አቃፊና ተጋሪ የማንነት ባለቤት አድርጎታል። ለዚህ በርካታ ማሳያዎችን ማቅረብ የሚቻል ቢሆንም የነገረ-ፍሬየ መዳረሻ አይደለምና እዘለዋለሁ። ሊሰመርበት የሚገባው የአማራ ሕዝብ አንድነት ግን የሰላሳ ዓመታት ሳይሆን በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን የተሻገረ ነው። የዳማት ዙፋን ወራሽ፣ የአክሱም ሥልጣኔ ባለቤት ነው!! ይህ የአማራ ያገጠጠ ሃቅ በትህነግ ዘመን ለመፍጠር ከታሰበው አማራ እና ፖለቲካዊ … [Read more...] about “ነገርን ከሥሩ ውሃን ከጥሩ”
አበበ በለው በአማራ ሚዲያ? እንዴት ሆኖ?!
እንደ አገርም፣ እንደ ሕዝብም የገባንበትን የችግር ማዕበል በቅጡ የመረዳት ችግር እንዳለ የሚያመላክቱ ጉዳዮች አሉ። እነዚህን ጉዳዮች ባስቸኳይ ካላቆምን ውርደት በግል፣ በቤተሰብ፣ በቀዬና በአገር ደረጃ በደጅ ቆሞ እየጠበቀን ነውና “ግባ በለው” የማለት ያህል ይሆንብናል። ይህ ከሆነ ደግሞ ዕድሜ ልክ ቀና ማለት አይቻልም። እንግሊዞች ተንበርክከው እንደ ከብት ሳር እንደጋጡት እንኳን ዕድል የሚሰጥ የለም። ኢትዮጵያ ከዳር እስከዳር ተነስታ፣ ልጆቿ አንድ ሆነው፣ የቻለ ህይወቱን፣ ያላቻለ በደጀን ተጋምዶ በከፈሉት ዋጋ ዛሬ የተገኘው ድል ተመዝግቧል። ከትግሬ ወራሪ ኃይል ነጻ በወጡ አካባቢዎች እንደታየው ዓላማው አገሪቱን መዘረፍ፣ ቀሪውን ማውደምና ወደ ዓመድነት መቀየር ነው። ይህ በዓይን ብረታችን ያየነው እውነት በመሆኑ ማስተባበያ አይቀርብበትም። ይልቁኑም ትምህርት ቤት፣ ክሊኒክና … [Read more...] about አበበ በለው በአማራ ሚዲያ? እንዴት ሆኖ?!
ቀጣይዋ ትግራይ = “ትግ-ሶቶ”
መውጫው እንደመግቢያው ቀላል አልሆነም። በትግሬ ልሂቃን እብደት፣ ማኅበራዊ መሠረታቸው ላይ የእሳት ቀለበት ሰርተዋል። በእያንዳንዱ የትግሬ ጎጆ የመከራ ዜና፣ የመርዶ መልዕክት ገብቷል። በጦርነቱ እና ከጦርነቱ ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች አራት መቶ ስድሳ ሺህ ትግሬዎች ረግፈዋል። ይህን እኔ ሳልሆን ያልኩት የሳልሳዊ ወያኔ (ሳወት) መሪ ተስፋ ኪሮስ ሳህለ ነው። ያለምንም ጥርጥር ጦርነቱ በሕዝባቸው ላይ የትውልድ ክፍተት ፈጥሯል። ምናልባትም አንድ ወንድ አምስት ሴቶችን እንዲያገባ በልዩ ሁኔታ የቤተሰብ ሕጉ ካልተሻሻለላቸው በስተቀር የትውልድ ክፍተቱን በቀላሉ አይሞሉትም። ወያኔ ራሱ በለኮሰው እሳት “እወክለዋለሁ” የሚለውን ሕዝብ የእሳት ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል። ከዚህ ጦርነት የሚተርፍ ቢኖር እንኳ በርካታ የትግራይ ከተሞችና መንደሮች የአዛውንት እና የሕጻናት ስብስብ … [Read more...] about ቀጣይዋ ትግራይ = “ትግ-ሶቶ”
“ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ
ከአሸባሪው ትህነግ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻ ፍልሚያ አስመልክቶ ጠቅላዩ ይህንን ብለው ወደ ግምባር እንደሚዘምቱ አስታውቀዋል፤ “ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ”። ይህ በዘመናዊ አገላለጽ የተጻፈ ብዙ ጊዜ ሲነገር ከነበረው የአጼ ምኒልክ የክተት ጥሪ ጋር የሚመሳሰል ነው። ጠቅላዩ ቃላቸውን ጠብቀዋል። “አንገቴን እሰጣለሁ እንጂ ተላላኪ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም” ብለው ነበር። ምቾታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ወደ ሌላ አገር አልሄዱም። ወይም ደንዝዘው አዲስ አበባ በመቀመጥ እንደነ ጋዳፊ ለመሆን አልፈጉም። በዘመናዊ ታሪክ አገሩን … [Read more...] about “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ
እነ ኤርሚያስ ለገሰን አማራ ምን ቢበድላቸው ነው በዚህ መጠን ሊበቀሉት ፈለጉ?
እነ ኤርሚያስ ለገሰ አርብ ምሽት አንድ ፕሮግራም ሰርተዋል። በዚህ ፕሮግራም ዋና ሀሳባቸው አማራ ክልል ላይ አዲስ መንግስት መመስረት የለበትም የሚል ነው። በፕሮግራሙ: 1) አማራ ክልል ላይ ጭካኔና ውድመት እየፈፀመ ያለውን የትግሬ ወራሪ ኃይል TDF እያለ የትግሬ ወራሪ ራሱን የሚጠራበትን ይፋዊ ስሙ አድርጎ፣ ይህ ቡድን ምርጥ ተሞክሮ እንደሆነ ይናገራል። የትግራይ ወራሪ ኃይልን ጥሩ ምሳሌ ሲያደርግ፣ የትግራይን ወራሪ ኃይል እውቅና ሰጥቶ ትክክለኛና ሌላውም ምሳሌ ሊያደርገው የሚገባ ነው ሲል ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው። አማራን ለማጥፋት እየሰራ ያለን ኃይል ነው ምርጥ ተሞክሮ እያለ የሚያስተዋውቀው፣ የሚያሞካሸው። አማራው ላይ ይህን ያህል ውድመት እየፈፀመ ያለውን ቡድን ጠቅሶ አማራውም ይህን የሚመስል ቡድን ነው መንግስት ሊይዝ የሚገባው ይላል። ይህ ማለት የትግራይ ወራሪ … [Read more...] about እነ ኤርሚያስ ለገሰን አማራ ምን ቢበድላቸው ነው በዚህ መጠን ሊበቀሉት ፈለጉ?
“ዳፍንታም” ነኝ – ያሬድ ጥበቡ
“ጆሊው” ጀቤሳውን በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊነቷና “ኦሮማዊነቷ” ተምታቶባት ከነበረችው ቤተልሔም ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ አዳመጠሁት። ስለ ቤተልሔም ለመናገር ባይሆንም ዋናው ሃሳቤ፤ ቤተልሔም ከለውጡ በፊት ኦሮሞነቷን በአቅራቢያዋ የነበሩ ሰዎች እንኳን አያውቁም ነበር። በኋላ ግን እነ ጃዋር አራት ኪሎን በቅርብ ርቀት ማየት ሲጀምሩ “አኝከህ አኝከህ ወደ ወገንህ ዋጥ” ተብሎ በአማርኛ የተነገረው ብሒል ትዝ አላትና “ልትውጥ” ወደ “ዘመዶቿ” ዞር አለች። “ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ ቢኖር ኦሮሞ እንደሚሆን እርገጠኛ ነኝ” ብላ አምላክን ኦሮሞ አድርጋውም እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ወደ ጉዳዬ ስመለስ … ቃለ ምልለሱ ሲጀመር የሚታየው አጅሬው ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) በዚያ አዛውትነቱ ነጭ ሸሚዙን ከደረቱ አጋማሽ ድረስ ከፈት አድርጎ ከውስጡ ካኔተራው እየታየ … [Read more...] about “ዳፍንታም” ነኝ – ያሬድ ጥበቡ
ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ህይወቱን አሀዱ ብሎ የጀመረው 1983ዓ.ም. ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ የከተማዋን ወጣቶች የማደራጀት ስራ ላይ ከተሰማሩ ወጣቶች አንዱ ሆኖ ነው። በዚያ ወቅት ወጣቱ ልደቱ ለወያኔ መንግስት የመወገን ጫና በነበረበት የወጣት ማህበር ምስረታ ሂደት ንቁ ተዋናይ ነበረ። በመሆኑም የማህበሩ ሊቀመንበር የመሆን ፍላጎት እንደነበረው በወቅቱ አብረውት የነበሩ የመሰከሩት ነገር ነው። ነገር ግን በ1990 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በይፋ ሲመሰረት ወጣቱን በማደራጀት ምንም ተሳትፎ ያልነበረው የዳዊት ዮሃንስ (አፈጉባዔ የነበረ) ሚስት ወንድም የሆነው ወጣት ታጠቅ ካሳ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ይሄኔ ነው እንግድህ የልደቱ የመጀመሪያው የፖለቲካ አቋም እጥፋት የተጀመረው። የታጠቅን በሊቀመንበርነት መመረጥ አሚን ብሎ መቀበል አልፈለገም። … [Read more...] about ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
ቁጭ ብዬ ናሽናል ጂኦግራፊክ ስመለከት ጅቦች አየሁ። አንድ ጎረምሳ አንበሳ ይተናኮላሉ። አንበሳው እየገላመጠ መንጋጋውን እያጓራ ያሳያቸዋል። ራሱን ለመከላከል ብዙም ያልተጨነቀው አንበሳ እየተቆጣና እየተገላመጠ ሲራመድ ጅቦቹ የልብ ልብ ተሰማቸው። ጅቦች አንበሳን ሊበሉ ቋመጡ። በመካከሉ አንዱ ጅብ ዘልቆ ሲገባ አንበሳው ተወናጭፎ መቀመጫው አካባቢ ነከሰው። ይህኔ የተነከሰው ጅብ ጩኸቱን አምባረቀ። አንበሳው በጣም ተናዶ ጉልበቱን ማሳየት ሲጀምር ጅቦች አፈገፈጉ። ይህን ጊዜ የተነከሰውን ጅብ መቀመጫ የማየት ዕድል የገጠማቸው ጅቦች አንበሳውን ትተው “ወንድማቸውን” ያሳድዱ ጀመር። አባረው ያዙት። አንበሳው በነከሰው በኩል የሚፈሰውን ደም ተከትለው በደቦ በሉት። ጅብ ሌላው ጅብ ላይ ደም ካየ አይምርም። ደም ሲደማ ሆዱ እንደሚሞላ ስለሚያውቅ ማድማት ወይም በደማው በኩል ገብቶ … [Read more...] about የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
ወንድማማቾቹ የኢትዮጵያ ዘማቾች
ወጣት አለኸኝ ይመኑ እና ወጣት ግርማ ብሩ ከአንድ ማህጸን የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ውልደትና እድገታቸው ደግሞ በአዳማ አቅራቢያ በሚገኘው ልዩ ስሙ ቆቃ በተባለው አካባቢ ነው። ምንም እንኳን የእናት አንጀት ለልጆቿ ምን ያህል እንደሚራራ ቢተወቅም አገር ጥሪ ባቀረበች ጊዜ ግን ከሰንደቅ ዓላማ የሚበልጥ የለምና ኢትዮጵያን ከጠላት እንዲታደጉ እናታቸው መርቀው በደስታ ለውትድርና እንደላኳቸው ይናገራሉ።ቤተሰብና የአካባቢው ሰዎችም ልጆቻቸው ለአገር መከታ ይሆኑ ዘንድ በምርቃትና በደስታ ሸኝተዋቸዋል። (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ወንድማማቾቹ የኢትዮጵያ ዘማቾች