ባለቤት ያጣ ሕገ መንግሥት?

የሕገ መንግሥት ትርጉምና የከበቡት ጥያቄዎች

የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታና በሌሎች ግለሰቦች ላይ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89፣ 368/95፣ 622/2001 እና የወንጀል ሕግን በመጥቀስ፣ በሥልጣን አለአግባብ በመገልገልና በጥቅም በመተሳሰር የቀረጥ ነፃ መብትን ያላግባብ በመገልገል፡ እንዲመረመር አለማድረግ ወይም እንዳይመረመር ማድረግ፣ ገደብና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ዕቃዎች (መድኃኒቶች) በማስገባት ወንጀል ክስ አቅርቦባቸው፣ ጉዳያቸው በፌዴራል […]

Read More...

“የክስ መቋረጥ” ወይስ የኦባማ ጉብኝት?

ክስ ከተቋረጠ ሊቀጥል ይችላል ማለት ነው?!

“ክሴን አቋርጫለሁ” ከማለት ባለፈ ምክንያቱን ከመናገር ተቆጥቧል ከአንድ ዓመት በፊት ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በድንገት ተይዘው ከታሰሩ በኋላ፣ በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸውና የሰነድና የሰው ማስረጃ ቀርቦባቸው፣ ለብይን የተቀጠሩበትን ቀን እየተጠባበቁ ከነበሩት አሥር ተከሳሾች መካከል አምስቱ በድንገት ሐምሌ 1 እና 2 ቀን 2007 ዓ.ም. መፈታታቸው እያነገጋገረ ነው፡፡ ለተከሳሾቹም ሆነ ወክለዋቸው ለሚከራከሩላቸው ጠበቆቻቸው […]

Read More...

አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ የቀረበባቸውን ክስ ክደው ተከራከሩ

"እንኳን 16 ቤት አንዲት ደሳሳ ጐጆ የለኝም" አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ

“ልንመሰገንበት በሚገባ ሥራ ወንጀለኛ መባላችን ያሳዝናል”  አቶ መላኩ ፈንታ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣ የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከር ድርጊቱን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛም እንዳልሆኑ ለፍርድ ቤት ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. አስረዱ፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና […]

Read More...

የሽብርተኝነት እንቆቅልሽ

የኢትዮጵያው አዋጅ ትርጓሜና ክፍተቶቹ

መንግስታት በተለያየ መልኩ ትርጉመው ያቀረቡትን ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ህግ ያወጣሉ፡፡ በእርግጥ በአዲስ መልክ በሽብር ላይ የታወጀው ዘመቻ በአሜሪካ ግፊት የመጣ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 አሜሪካ ከደረሰባት የሽብር ጥቃት በኋላ “war on terror” እንዲሁም “counter ter­rorism” የተሰኙ ዘመቻዎችን ነድፋ ተንቀሳቅሳለች፡፡ አሜሪካ ወዳጅም ሆነ የቀዩ ባላንጣዎቿን ሳይቀር ደልላም ሆነ ተማጽና የጀመረችው ይህ “ጸረ ሽብር ዘመቻ” መንግስታት በየ አገራቸው […]

Read More...

የፀረ ግብረ ሰዶማዊነት ሕጋችን ቢከለስስ?

(የሙሴቬኒ ዓይነት የፖለቲካ ቁርጠኝነት አስፈላጊ ነው)

የዛሬው ጽሑፌ መነሻውና መድረሻው በዚህ ሳምንት አነጋጋሪ ስለነበረው የኡጋንዳ የፀረ ግብረ ሰዶም ሕግና አገራችን በንፅፅር የምትወስደውን ልምድ መቃኘት ነው፡፡ ኡጋንዳ ይህንን ሕግ በማውጣቷ ዓለም ተደንቋል፡፡ አፍሪካን ግን የሚደንቅ አይደለም፡፡ አገራችንንማ ሕጓን እንድታጠነክር ካልሆነ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚታገስ ባህልም ሕግም ኖሯት አያውቅም፡፡ ዜናው እጅጉን የሳበው ምዕራባውያንን ነው፡፡ ኡጋንዳ እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ አገሮች በአንድ ወቅት ቅኝ ገዥ ስለነበራት […]

Read More...

ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት …

(ይድነቃቸው ከበደ)

ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ […]

Read More...

በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉት 24 ተከሳሾች ክስ መሰማት ጀመረ

በገብረዋህድ ቤት በርካታ መሣሪያዎች ተገኝተዋል

የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እና ግብረ አበር ባለሀብቶች ላይ የመሰረተውን ክስ በፍርድ ቤት ማሰማት ጀምሯል። የኮሚሽኑ ዐቃቤ ህግ በተለይም በአንደኛው ተከሳሽ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ መዝገብ ቁጥር 14356 ስር ባለው 11ኛ ክስ ውስጥ ተከሳሹ በትዳር ያለችን ሴት አስኮብልለዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል። ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት […]

Read More...

አደባበዬቻችን እና መንገዶቻችን መሉሱልን?!

(ይድነቃቸው ከበደ - የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ)

‹‹ ዲሞክራሲ የሚመሠረተው መንግስት ሕዝቡን ሊያገለግል የቆመ ነው በሚል መሠረት ሃሳብ ላይ ነው፡፡ ይህም ማለት ሕዝብ መንግሥትን ለማገልገል የተፈጠረ አይደለም፡፡ በሌላ አነጋገር ህዝብ የአንድ ዲሞክራሳዊ አገር ዜጋ እንጂ ተገዥ አይደለም፡፡ መንግስት የህዝብን መብት በሚያስጠብቅበት ወቅት ህዝብ ደግሞ በልዋጩ ለመንግስት ታማኝነቱን ይገልፃል፤በጨቋኝ ሥርዓት ግን መንግስት ራሱን ከህዝብ በማግለል ታማኝነትን ከህዝብ ይሻል ፤መንግስት ውሳኔ የሚወስነው ተገቢውን የህዝብ […]

Read More...

ጥያቄው ሃይማኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ…

(ይድነቃቸው ከበደ - የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ)

‹‹መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕስ አንቀፅ 3፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው የማሰብ፤ የሕሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው፡፡ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይመኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡›› ሕገ መንግስት አንቀጽ […]

Read More...

አጭር ማስታወሻ በሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሠልፍ

ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደሰፈር ጉልበታኛ ዱንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በሃይማኖት ስበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በህግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም […]

Read More...