“ቅባትና ደረቅ” በአማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ታካሚዎች እንደ ደረጃ መዳቢ የተሰጠ ስም ነው። ታሪኩ ዘግናኝ፣ ኅሊናን የሚፈትን፣ ወዴት እያመራን እንደሆነ ግራ የሚያጋባ፣ መፈጠርን የሚያስጠላ፣ ሲሰሙት ግራ የሆነ፣ ቃላት ሊገልጹት የማይችል የክሽፈታችን ሁሉ ከሽፈት ነው። አማኑኤል ሆስፒታል ተኝቶ ለመታከም አርባ ሺህ ብር እንደሚከፈል ከመስማት በላይ ዘግናኝ ጉዳይ የለም። ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ ሌሎችም ጉዳዮች አሉ። በአማኑኤል ሆስፒታል ሴት የአዕምሮ ህመምተኞች መደፈራቸውን፣ ሲያረግዙ ጽንስ የሚቋረጥበት ክሊኒክ በውስጥ በተደረገ ስምምነት ይሰጥ እንደነበር ይፋ በተሰማ ጊዜ ጫጫታ ተሰምቶ ነበር። ጉዳዩን በወቅቱ ይፋ ያደረጉት አንድ የሆስፒታሉ ነርስ ነበሩ። ዛሬ ያ ግፍ ተመርምሮ መልስ ሳያገኝ ተጨማሪ ጉድ እየሰማን ነው። የሟቹ መለስ ዜናዊ ባለቤት የበላይ ጠባቂ ሆና ስትመራው … [Read more...] about እንባ ካለ አሁን እናልቅስ!! ሊታመን ባይችልም አማኑኤል ሆስፒታል እንዲህ እየሆነ ነው!
News
ዜና
የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!
ረዥሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ከነፍጥ፤ ከሞፈርና ከመስቀል ጋር ተዛማጅነቱ ፍፁም ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህ ይመስላል አባ ዳኘው (ዳግማዊ አጤ ምኒልክ) የአድዋ ጦርነት ዘመቻ ዝግጅት ላይ “… ሀገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖት የሚለዉጥ ጠላት…” መጥቷልና ከርስትህና ከሚስትህ ሳትነቀል የሚል ይዘት ያለው አዋጅ በወቅቱ እንዲነገር ያደረጉት፡፡ በጊዜ ሂደት ሀገሪቱ ከታሪኳ መድረክ “መስቀል”ን ገለል ብታደርግም ነፍጥና ሞፈር (ርስት) የአገሪቱ ህያው አምሳያ የታሪክ አካል ሆነዉ ቀጥለዋል፡፡ ወራሪ ኃይል በመጣ ቁጥርም እነዚህ የአገሬው ማታገያ አብይ አጀንዳዎች ሆነው ሲነሱ ኖረዋል፡፡ የነጮቹ ቅርጫ የሆነችው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ክፉ ዕጣ ውልቅልቋ ሲወጣ፤ ኢትዮጵያ አድዋ ላይ በጀግኖች አባቶቻችን ተጋድሎ ሉአላዊነቷን ማስከበር ችላ ነበር፡፡ ፋሺስት ጣሊያንም ሽንፈቷን በእልህና በቁጭት ለመቀበል አርባ … [Read more...] about የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!
የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል!
ጎንደርና ባህርዳር ከተማ ውስጥ በሁለት ወር ብቻ 9 የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል! “ህወሃት የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን ክፍል የበቀል መወጫ እያደረገው ነው”፤ ነዋሪዎች ላይቆም የተቀጣጠለው የሰሜን ምዕራብ ብረት አከል ህዝባዊ አመፅ የትግል ስልቱን እየቀያየረ ባህርዳር ደርሷል፡፡ አስር ወራትን ያስቆጠረው የነፃነት ኃይሎች እንቅስቃሴ ከገጠር ሽምቅ ውጊያ ወደ ከተማ የደፈጣ ቦምብ ጥቃት ተሻግሯል፡፡ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ዘጠኝ የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል፡፡ ድርጊቱ ሰላም የነሳው ህወሃት “የአማራ ክልልን የበቀል መወጫ እያደረገው” መሆኑ ይነገራል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሙሉ የደህንነት አቅሙንና የበዛ የመከላከያ ኃይሉን አማራ ክልል ላይ ቢያደርግም የነፃነት ኃይሎች ተከታታይነት ያለው ጥቃት ከመፈፀም ያገዳቸው ኃይል የሌለ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ የመጀመሪያዉ ዙር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ … [Read more...] about የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል!
ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!
“ዳግም የመኖር እድል ተሰጠኝ፤ ተማርኩበት፤ እናንተም ተማሩ” “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጋቸው ሁሉ “አለሁ” የሚሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን አጥብቀው ይዋጋሉ። ይጸየፉታል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልማቸውና የመጨረሻ ግባቸው ነው። ሰብዓዊነት ለአፍታም ከአንደበታቸው የማይለይ፣ በሚያውቋቸው ሰዎች ሁሉ የሚወደዱ፣ ግልጽ ተናጋሪነታቸው ልዩ የሚያደርጋቸው ኦባንግ በዚሁ ባህሪያቸው “አባ ነቅንቅ” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። በስደት ለሚሰቃዩ የኢትዮጵያ ልጆች /እሳቸው ቤተሰቦቼ የሚሏቸው/ በጠሯቸው ቦታና ሁሉ በመገኘት ለሚያሳዩት ትጋት አቻ የላቸውም። ኢትዮጵያን በመወከል በከፍተኛ ቦታዎች የሚሟገቱ፣ ያዘነውን የሚጎበኙ፣ ለሴት እህቶቻችን ቀድመው የሚደርሱ እኚህ ውድ ሰው በድንገተኛ የመኪና አደጋ … [Read more...] about ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!
“ግድያው ተገቢና ሕጋዊ ነው” የህወሃት “ሰብዓዊ” ኮሚሽን
ህወሃት/ኢህአዴግ በንፁሐን ደም ላይ ማላገጡን ቀጥሏል!! በኢትዮጵያ ለሩብ ክፍለ ዘመን የተከማቸው የግፍ አገዛዝ በምሬት የታጀበ ህዝባዊ አመጽ አስነስቷል። ህዝባዊ አመጽ ደግሞ ለኢትዮጵያ አዲስ ክስተት ባይሆንም በአገሪቱ ዉስጥ በሁለንተናዊ ዘርፍ ተጽዕኖ መፍጠር ከሚችሉት ሁለቱ ክልሎች (የኦሮሞና የአማራ፤ የደቡብ ኮንሶንና ጌዴኦን ተቃውሞዎች ሳንዘነጋ) ተከታታይነት ባለው መልኩ የአገዛዙን ማህበራዊ መሰረት በሚንድ ሁኔታ አመጽ መቀስቀሱ ይህኛዉን ክስተት የተለየ ያድርገዋል። በዚህ ህዝባዊ አመፅ ህወሃት ከበረሃ የሽምቅ ባህሪው በተሻገረ የ“መንግስት” ባህሪ የሌለው መሆኑን ለወዳጅ ጠላቶቹ ያስመሰከረበትን መንግስታዊ ፍጅት በዜጎች ላይ ፈጽሟል። በገዛ ዜጎቹ ላይ የከፈተውን ጦርነትና ጅምላ እስር ዘግይቶም ቢሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም ህጋዊ ሽፋን ሲሰጠው ታይቷል። ድርጊቱንም … [Read more...] about “ግድያው ተገቢና ሕጋዊ ነው” የህወሃት “ሰብዓዊ” ኮሚሽን
ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል! (ክፍል ሁለት)
የማጠቃለያው መግቢያ እስኪ አንድ ጥያቄ እንመልስ፤ እንዴት መሽቶ ይነጋል? እነዚህ ወገኖች እንዴት ቻሉት? እንዲህ ያለው ስቃይ እንዴት ሌሎችን ያስደስታል? በህይወት ያለ ሰው በኤሌክትሪክ ማቃጠል ምን ማለት ነው? ሰውን ማኮላሸት ምን የሚሉት ጭካኔ ነው? ሰውን ሰቅሎ መርሳት፣ ገልብጦ ሲደበድቡ ማደርና ማቃጠል፣ ተነግሮ፣ ተወርቶ፣ የማያልቅ ጉድ! እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች የሚያስቡት? ሕዝብ ስሜት ያለው አይመስላቸውም? የወላድንና የህጻናትን እንባና የፈጣሪን ፍርድ ለጊዜው ወደ ጎን ቢሉትም፣ ነገሮች በዋይታ የሚዘልቁ ሆነው ስለመሰራታቸው እርግጠኞች ናቸው? የትግራይ ሕዝብስ ለምን ዝም ትላለህ? የትግራይ ምሁራን ይህ እርካታን ይሰጣችኋል? ከመጠርጠር እስከ መመርመር፣ እስከ ማሰር፣ መክሰስ፣ መፍረድና ይቅርታ ማስጠየቅ በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) እየተከናወነ፤ የአሳሪው … [Read more...] about ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል! (ክፍል ሁለት)
መዘጋቱ ታቅዶ የተከፈተው የአህያ ቄራ
በህወሃት ፈቃድ በቢሾፍቱ የተከፈተው አህያ ማረጃ (ቄራ) መዘጋቱ በእንግሊዝኛ የሚታተመው ፎርቹን ጋዜጣ ከሁለት ቀናት በፊት ዘግቧል፡፡ ቄራው የተከፈተ ሰሞን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ድጋፍ እንደነፈገው አብሮ ተዘግቧል፡፡ ቄራው የተከፈተው እንደሚዘጋ ታቅዶ ነበር፡፡ የዛሬ ሦስት ሳምንት አካባቢ በቻይናዊ ባለሃብት ከአዲስ አበባ 48ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ የአህያ ማረጃ መከፈቱ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በብዙዎች ዘንድ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከውይይቱም ባለፈ በርካታዎች ጉዳዩን ከህወሃት/ኢህአዴግ ባለሥልጣናት ጋር በማገናኘት የመሳለቂያ አጀንዳ አድርገውት ከርመዋል፡፡ መዘጋቱንም በተመለከተ “አንዳንድ ባለሥልጣኖችን ከሥጋት ለመታደግ ነው” በማለት የተሳለቁም አሉ፡፡ ቄራው በሥራ በቆየበት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ሦስት መቶ አህዮችን ማረዱ ፎርቹን መረጃ … [Read more...] about መዘጋቱ ታቅዶ የተከፈተው የአህያ ቄራ
በበዓል ዋጋ ንረት የምትታመሰው አዲስ አበባ!
ተባዕት ዶሮ ከ280 - 360 ብር እየተሸጠ ነው! በግ ከ2,200 - 3,800 ብር የሽያጭ ዋጋ ደርሷል! ድልብ በሬ ከ25,000- 37,000 እየተሸጠ ነው! በረዥም ጊዜ ሂደት እየተዋረሰ የመጣው ኃይማኖታዊ በዓል አከባበራችን ከምግብ እና መጠጥ ጋር በጽኑ የተቆራኘ ነው፡፡ የአጽዋማትን ፍች በተመለከተ ከተቀመጡ ኃይማኖታዊ መርሆች ይልቅ ተለምዷዊ ድርጊቶች ገዥ ሐሳብ ሆነው ቀርበዋል፡፡ በዓላትን የታከከ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ደግሞ የአገሪቱ ኢኮኖሚ መገለጫ ሆኗል፡፡ መንግስታዊ ኃላፊነቱን በዘነጋ አገዛዝ ውስጥ ላለችው ኢትዮጵያ የመሠረታዊ ሸቀጦችና የቁም እንስሳት ዋጋ ንረት መታየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የህዝቡ የድህነት ቁስል ላይ ለመቆም የማይሳቀቁ ስግብግብ ነጋዴዎች የዋጋ ንረቱን በማጐን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ቀጥሎ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ለመንግሥት ሠራተኞች … [Read more...] about በበዓል ዋጋ ንረት የምትታመሰው አዲስ አበባ!
“… ተድብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ ካሁን በኋላ በራሴ ፈቃድ ‘ወደ ችሎት’ አልመጣም” በቀለ ገርባ
"… ተድብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ ካሁን በኋላ በራሴ ፈቃድ አልመጣም” በፍርድ ሂደቱ ሲሉ መሰላቸታቸውን አቶ በቀለ ገርባ ተናገሩ። አቶ በቀለ ይህንን የተናገሩት ሃሙስ ባስቻለው ችሎት የመናገር እድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው ሲፈቀድላቸው ነው። ከሁለት ቀን በፊት አቃቤ ህግ በማስረጃነት አቀርበዋለሁ ሲለው የነበረውን የድምጽ ከምስል ማስረጃ አስተርጉሞ እንዲያቀርብና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ሃላፊ ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ በቀጠሮው በትዕዛዙ መሰረት ዓቃቤ ሕግ በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ ያቀረበውን የድምፅ ከምስል ማስረጃ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዛሬም እንዳላስተረጎመው አሳውቋል። የኤጀንሲው ሃላፊ ችሎት አለተገኙም። የክልሎች ቋንቋ ሃላፊ ጸጋ ልዑል ወልደኪዳን "ብቁ ጋዜጠኞች ስለሌሉ አልተተረጎመም” በማለት የሰጡትን ምክንያት ፍርድ … [Read more...] about “… ተድብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ ካሁን በኋላ በራሴ ፈቃድ ‘ወደ ችሎት’ አልመጣም” በቀለ ገርባ
ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል!
በማዕከላዊ ስቃይ ተፀንሶ ይወለዳል፤ ጡት ጠብቶ ዳዴ ብሎ ጐልምሶ ያረጅበታል!! እንደገና አዲስ የማሰቃያ ስልት ይወለዳል!! በማዕከላዊ በንጹሐን ዜጐች ደም የጨቀዩ ገራፊዎች ይርመሰመሱበታል!! ከዝግጅት ክፍሉ፡- ማዕከላዊ አገዛዙን በወታደራዊ የበላይነትና በደህንነቱ አቅም በቁጥጥር ስሩ ያዋለው ህወሓት፤ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ እያደረሰ ያለውን ቃላት የማይገልፁት የዜጐች ስቃይ በተመለከተ ጎልጉል ድረገጽ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን ዜጐችና ቤተሰቦቻቸውን በማነጋገር ይህን ዘገባ በሁለት ክፍል አጠናቅሯል። ዘገባው የጋዜጠኛነት ሙያ የሚጠይቀውን (“የሕዝብ አይንና ጆሮ በመሆን የተደበቀውን ፈልፍሎ ማውጣት!” የሚለውን) ቀዳሚ መርህ በማድረግ በዳሰሳ ጥናት ተደግፎ የተዘጋጀ መሆኑን እንገልፃለን። የኢትዮጵያዊያን የስቃይ ጎሬ በሆነው ማዕከላዊ እስርቤት በ“ምርመራ” ወቅት በዜጎች ላይ … [Read more...] about ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል!