ጉብኝቱ “ከHR 128 … ውጪ ሊሆን አይችልም” ኦባንግ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ በአዲስ አበባ ላይ ከኢህአዴግ ሹሞች ጋር መከሩ። አቶ ኦባንግ ሜቶ ጉብኝቱ “ከHR 128 የተያያዘ ነው፤ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም” ይላሉ። በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት (2017) መጀመሪያ አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የነበሩት ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ከከፍተኛ የሕወሓት/ኢህአዴግ ሹሞች ጋር መነጋገራቸው ህወሓት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዜና አገልግሎቱ ውይይቱ መቼ እንደተደረገ ባይዘግብም ዜናውን ግን ጥቅምት 2/2010 በማለት ነው ያተተው። በውይይቱ ላይ ሴናተሩ ሌሎች የአሜሪካ እንደራሴዎችንና የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አባላትን በመምራት እንደተገኙ ዜናው አስታውቋል። የውይይቱ ትኩረትም “በሠላምና ጸጥታ … [Read more...] about የሴናተር ኢንሆፍ ህወሓትን የመታደግ ዘመቻ ቀጥሏል!
News
ዜና
የአባዱላ መጨረሻ
አቶ አባዱላ ገመዳ ከሁለት ሳምንታት በፊት ለዓመታት ከተቀመጡበት የአፈ ጉባኤነት መንበር ላይ ለመልቀቅ መጠየቃቸው ከባለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ ዋነኛ ርዕስ ሆኖ ዘልቋል። ከፓርቲያቸው ኢህአዴግ/ኦህዴድ እንዲሁም ከእራሳቸው አንደበት ዜናውን ለማስተባበል የተሰማ ነገር ስለሌለ ሥልጣን ለመልቀቅ መጠየቃቸው ሃቅ ወደ መሆኑ ያመዘነ በነበረበት ጊዜ ጥያቄ የማቅረባቸውን እውነትነት እራሳቸው አረጋጥጠዋል። ወታደራዊው መንግሥት አባዱላ መስራችና አባል የሆኑበት ኦህዴድ በሚገኝበት ኢህአዴግ ተሸንፎ ከተወገደበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የወታደራዊና የሲቪል ሃላፊነቶች ላይ ቆይተዋል። አባዱላ ከትግል በኋላ ፓርቲውን የተቀላቀሉ በርካታ አመራሮች ባሉበት ኦህዴድ ውስጥ ተቀባይነት ካላቸው ቀደምት ጥቂት መስራች አባላት ውስጥ ቀዳሚው እንደሆኑ ይነገራል። ለዚህም ይመስላል በርካታ የኦህዴድ አባላትና … [Read more...] about የአባዱላ መጨረሻ
“እስከማውቀው አባዱላ በዚህ መልኩ አይዳፈሩም”፤ አባዱላ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነት
በኦህዴድ አባላት ዘንድ “ጃርሳው” የሚል መጠሪያ ያላቸው አባዱላ ገመዳ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሰለቻቸው ከፍተኛ አመራሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው። "ንፍሮ እየበላሁ ከተራው ህዝብ ጋር መኖር ናፈቀኝ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን በነጻነት የምሄድበት ቀን መቼ ነው?" በማለት ለሚቀርቧቸው ሲናገሩ መቆየታቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ምስክርነት ይሰጣሉ። የጦር ሰራዊት መለዮ አውልቀው መከላከያ ሚኒስትር፣ ከዛም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት አባዱላ፣ በኢህአዴግ አመራሮች የማይደፈሩ ቦታዎች ድረስ ዘልቀው በመግባት ከህዝብ ጋር በተደጋጋሚ የመከሩ፣ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ኦሮሚያ ላይየተሻለ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው። በአቶ ደራራ ሞት እጃቸው አለበት በሚል የሚከሷቸው ያሉትን ያህል፣ በባህሪያቸው ሩህሩህ እንደሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አርሲና ባሌን … [Read more...] about “እስከማውቀው አባዱላ በዚህ መልኩ አይዳፈሩም”፤ አባዱላ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነት
HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
ለኢትዮጵውያን ታላቅ ተስፋ ይዞ የተነሳው HR 128/SR 168 በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኘ ተነገረ። የህወሃት/ኢህአዴግን ህልውና በማያፈናፍን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከት ብዙ የተባለለት ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሕግ መወሰኛ ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ ከማግኘቱ በፊት ጊዜውን ጠብቆ እንዲሞት የማቀዛቀዝ ተግባር እየተፈጸመበት ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረው በመታገል ይህ ዕድል እንዳያመልጣቸው ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጠ። ሐምሌ 20፤ 2009ዓም (7/27/2017) የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳደርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት ማለፉ ይታወሳል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን … [Read more...] about HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
እምቢተኝነት በተግባር!
“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ ከተናገረው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ዛሬ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ የህወሓትን ማስፈራሪያና ዛቻ ከምንም ባለመቁጠር የውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደሴና ሌሎች አካባቢዎች ህዝብ “ባለኮከቡን ባንዲራ አይወክለኝም” በማለት ኮከብ አልባውን ሠንቀድ ዓላማ ይዞ በመውጣት እምቢተኝነቱን አድፍረት አሳይቷል። ሃይለኪሮስ ታፈረ (Hailekiros Tafere) በፌስቡክ ገጹ የዘገበውን አስመልክቶ አምዶን ገብረሥላሴ ይህንን ብሏል፤ “ፖሊስ "ኮከብ የሌለው ባንዴራ ዳሜራ ሸፍናቹሃል" በሚል ሰበብ ዛሬ መስቀል በዓል እያከበረ የነበረው የውቅሮ … [Read more...] about እምቢተኝነት በተግባር!
ሹፌሮችን ያስቆጣ መመሪያ ተሻሻለ ተባለ
የአማራ ክልል መንግስት የመንግስት ተሸከርካሪ አያያዝ፣ አጠቃቀምና የንብረት አስተዳደር መመሪያ ሰሞኑን ማሻሻሉን ይፋ ቢያደርግም የከፍተኛ አመራሮች ሹፌሮች በበኩላቸው የተሻሻለው መመሪያ የኛን ሕልውና የሚፈታተን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጡ። የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሰሞኑን ለክልሉ ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ ከመስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ወይም የሥራ ኃላፊዎች ለሥራ ጉዳይ ክልሉን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የሚመሩትን ተቋም ተሸከርካሪ ይዘው እንዳሄዱ እያሳሰበ በተማከለ መንገድ በከተማው በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ አብራርቷል። በተማከለ መንገድ በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም የሚችሉ የሥራ ኃላፊዎች ብሎ የተሻሻለው መመሪያ የጠቀሳቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ም/ርዕሰ መስተዳድርና በዚህ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች፣ የክልሉ … [Read more...] about ሹፌሮችን ያስቆጣ መመሪያ ተሻሻለ ተባለ
ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!
“ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተለቀቁ ፍትሕ ይበየናል” “ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ውሳኔውን በመቀበል ለአገራቸው አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል” ኦባንግ ሜቶ “ዛሬ በአፍሪካ ታላቅ ፍትኅ ተፈፀመ” ራይላ ኦዲንጋ በኬኒያ በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በርካታ ችግሮች የገጠሙትና በአገሪቱ ሕግጋት መሠረት ያልተካሄደ ነው ሲል የኬኒያ ጠቅላይ ፍርድቤት ውጤቱን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ከመጀመሩ በፊት የኬኒያን ፖለቲካ በቅርቡ የሚከታተሉት ኦባንግ ሜቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማድነቅ “ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተደረጉ በምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን አፍሪካም የሕግ የበላነይትና ፍትህ ይሰፍናል፤ ሁለቱም ተወዳዳሪዎች፤ ራይላ ኦዲንጋ ከአመጽ ይልቅ በሥርዓት ጥቄያቸውን ለፍትሕ አካል በማቅረባቸው፤ ኡሁሩ ኬኛታ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ እገዛለሁን ማለታቸው የሚደነቁ ናቸው፤ … [Read more...] about ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!
የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ
ህወሓት በትግራይ ላይ የራሱን አቋም እንዲወስድ ተመክሯል በኢትዮጵያ ያለማቋረጥ ሲካሄድ ከቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ አኳያ በህወሓት የደህንነት ክፍል የተሰበሰበው መረጃ፤ አሁን ካለው የተቃውሞ ንቅናቄ የተነሳ የኢህአዴግ የገጠር መዋቀር በኦሮሚያና በከፊል የአማራ ክልሎች ሊፈርስ እንደሚችል አስታወቀ። ከሁኔታው አሳሳቢነት የተነሳ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች ቢኖሩም ህወሓት ትግራይን አስመልክቶ የራሱን አቋም እንዲወስድ ሃሳብ ተሰጥቶታል። ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ተስኖት ይገኛል። በተለይ “ባለራዕዩ መሪውን” ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ካስፈነጠረው ወዲህ ግምባሩ በአንድ መጓዝ፣ በአንድ መስማማት፣ በአንድ ማሰብ አቅቶት በተቃዋሚው መዳከምና በአንጋሾቹ አለሁ ባይነት … [Read more...] about የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ
ሕዝብ “በጠብመንጃ መገዛት በቃን” አለ!! ትውልድ እንዳመጸ ነው!
ለፖለቲከኞች እስር እውቅና የሰጡ “ፓርቲዎች” እየተደራደሩ - ሕዝብ እያመጸ ወዴት? “እንወክለዋለን” በሚሉት ሕዝብ ዘንድ እውቅና ያላቸው ተቀናቃኝ ፓርቲዎች እጅግ አነስተኛ እንደሆኑ ይነገራል። አብዛኞቹ በምርጫ ቦርድ እውቅና ያገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች “ጥቂት” ከተሰኙት ውጪ ስለመኖራቸው እንኳን እንደማይታወቁ በተደጋጋሚ አስተያየት ይሰጣል። እነዚህን ፓርቲዎች ሰብሰቦ ድርድር መቀመጥ የአገሪቱን ችግር ማስተንፈስ እንደማይቻል የሚከራከሩ ወገኖች ድርድሩን አያከብሩትም። በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ እዚህ ደረጃ መምጣቱ በራሱ አንድ ርምጃ ነው የሚሉና ድጋፋቸውን የሚሰጡ ጥቂት አይደሉም። በውጤቱ ሲታይ ግን አመጹም፣ ቅሬታውም፣ ችግሩም መልኩን ሲቀያይር እንጂ ሲለዝብ ማስተዋል አልተቻለም። ለዚህም ይመስላል የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ “ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር … [Read more...] about ሕዝብ “በጠብመንጃ መገዛት በቃን” አለ!! ትውልድ እንዳመጸ ነው!
የህወሓት “መከላከያ ሰራዊት” በበቃኝ ጥያቄ ተወጥሯል፤ ጄኔራሎች አሉበት!
ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ህወሓት የሚመካበትን የታጠቀ ሰራዊት የሚመሩ ከፍተኛ መኮንኖችና ጄኔራሎች በጡረታ ለመሰናበት ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። የአስቸኳይ አዋጁ ሲነሳ መልስ እንደሚያገኙ ቃል የተገባላቸው እንዳሉም ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ለደህንነት ሲባል መረጃውን ያገኘበትን ሳይገለጽ እንደጠቆመው “መከላከያ ሰራዊት” የሚባለውን የህወሓት ሥልጣን አስጠባቂ የታጠቀ ኃይል ከሚመሩት ጄኔራሎች መካከል “በቃኝ” ያሉት ጄኔራሎች ከሰባት በላይ ሲሆኑ፣ በከፍተኛ መኮንን ደረጃ ያሉት ግን ቁጥራቸው በርከት ያለ ነው። ጄኔራሎቹ ሰራዊቱን ለመሰናበት ያቀረቡትን ዋና ምክንያት የመረጃ ሰዎቹ ቃል በቃል ይፋ ባያደርጉም፣ ከሰራዊቱ ጋር ላለመቀጠል ዕድሜ፣ ጤና፣ ጋብቻና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎችን እንደ ምክንያት አቅርበዋል። መልቀቂያ ያስገቡት ብቻ ሳይሆኑ በርካቶች ተመሳሳይ ፍላጎት … [Read more...] about የህወሓት “መከላከያ ሰራዊት” በበቃኝ ጥያቄ ተወጥሯል፤ ጄኔራሎች አሉበት!