ጋምቤላን በረሃ አድርጎ፤ ሕዝቧን ገድሎ፤ በተለይ የአንድ ክልል “ዜጎችን” ብቻ ጠቅሞ በጋምቤላ የተተገበረው “ኢንቨስትመንት” ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ያህል የማይከፈል ዕዳ ውስጥ መዘፈቁን ህወሓት/ኢህአዴግ አመነ። ልክ የዛሬ 14ዓመት ነበር መለስ በመራው ስብሰባ ላይ “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለው ትዕዛዝ የወጣው። በዚህም መሠረት 424 ንጹሃን በግፍ ተጨፈጨፉ፤ መሬታቸው ተነጠቀ፤ ለባለሃብቶች በሃያ ብር (በወቅቱ 1 ዶላር) ሒሳብ ተቸበቸበ። ህወሓት ደርግን ሲወነጅልበት የነበረውን ግዳጅ ሠፈራና መንደር ምሥረታ በአኙዋክ ወገኖች ላይ ተፈጸመባቸው። ይህ ሁሉ የሆነው ለ"ልማት" ነው ተባለ። ሪፖርተር (8 November 2017) ባወጣው ዘገባ ላይ እንዳሰፈረው “ለጋምቤላ እርሻዎች የተሰጠው ብድር የልማት ባንክን መመለስ ያልቻሉ ብድሮች ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር … [Read more...] about ከ424 ዜጎች ጭፍጨፋ፤ ከ14 ዓመት መሬት ነጠቃ በኋላ የጋምቤላ “ኢንቨስትመንት” 9ቢሊዮን ብር ያህል ከስሯል
News
ዜና
በኢትዮጵያ ስም ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር የመጨረሻውን የጠቅላይ ጨዋታ ጀመረ
አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት “የእምነት አባቶች” የክህደቱ ተዋንያን ናቸው “... ይህ ዜና በተገለበ መልኩ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። ዜናው በደባና በተቀነባበረ ሤራ የሚካሄድ ቢሆንም ዜናውን በገደምዳሜ የሚያሰራጩት ክፍሎች ስለ ጉዳዩ የተጨነቁ አይመስሉም። ቅርብ ሆኜ እንደምከታተለው ይህ ዜና አደገኛና ኢትዮጵያን ዳግም ክህደት የሚያከናንባት፤ እንደ አገር የመኖር ኅልውናዋን አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ይህንን የሚያውቁ የሃይማኖት አባት መስቀል ተሸክመው የዚህ ሸፍጥ ተዋንያንና አስፈጻሚ መሆናቸው ያሳፍራል። ጉዳዩ በአጭሩ ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር በኢትዮጵያ ስም ሊታረቅ ዓለምአቀፍ ዕውቅና የተሰጠው ድርድር መጀመሩ ነው...” ይህ አጭር ሃሳብ ለጎልጉል ከተላከ የውስጥ አዋቂ ደብዳቤ የተቀነጨበ ነው። ደብዳቤውን የላኩት ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ኃላፊነት … [Read more...] about በኢትዮጵያ ስም ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር የመጨረሻውን የጠቅላይ ጨዋታ ጀመረ
ፈትለወርቅን ማንገስ ያቃተው የስብሃት ቡድን የአዜብ ዕገዳ እንዲነሳ ሊቀበል ነው
መቀሌ ላይ ሲሰዳደቡ የቆዩት የበረሃ ወንበዴዎች ደብረጽዮንን መሪያቸው አድርገው በመምረጥ የፈትለወርቅን ዋና መሪነት ውድቅ አድርገዋል። ይህ ለስብሃት ነጋ ሽንፈት የሆነው ክስተት በአዜብ ላይ የተጣለው ዕገዳ እንዲነሳ ወደመቀበል ሊገደድ ይችላል እየተባለ ነው። የኤፈርት ጉዳይ አሁንም አከራካሪ ሆኗል። ከልክ ባለፈ ሁኔታ መቀሌ ላይ ሲወነጃጀሉና ሲሰዳደቡ የቆዩት የህወሓት የበረሃና የድህረ በረሃ ወንበዴዎች በመጨረሻ ላይ የስለላውን ማሽን ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ዋና መሪያቸው አድርገው መርጠዋል። “ሞንጆሪኖ” በማለት ሳሞራ ዩኑስ ጣሊያናዊ ስም የሰጣት ፈትለወርቅ በነስብሃት ቡድን የዋናውን ቦታ እንድትይዝ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግላትም “የመለስ ራዕይ” አስጠባቂ የሆነው ቡድን አልረታም በማለት ውድቅ አድርጓታል። በውጤቱም በዓለምአቀፍ የመረጃ ቋት በአሸባሪነት የተመዘገበው የህወሓት ቡድን … [Read more...] about ፈትለወርቅን ማንገስ ያቃተው የስብሃት ቡድን የአዜብ ዕገዳ እንዲነሳ ሊቀበል ነው
አዜብ መስፍን በቁም እስር ላይ ነች
የጉዞ ዕገዳ እንደ ተጣለባት ይነገራል ከሰሞኑ የህወሓት የሥልጣን ሽኩቻ ጋር በተያያዘ የነደብረጽዮን ቡድን አዜብ መስፍንን ከማንኛውም የፓርቲ ሥልጣን ካገዳት በኋላ በቁም እስር ላይ እንደምትገኝ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። የጉዞ ዕገዳም ተጥሎባታል። ከህወሓት በተሰጠው መግለጫ ለመረዳት እንደሚቻለው የአዜብ ጉዳይ በዕገዳ ቆይቶ በቀጣይ የሚታይ ቢሆንም ዕገዳው በራሱ የቁም እስር እንደሆነ መረጃው ይጠቁማል። አዜብ የኤፈርት ዋና ኃላፊ እንደመሆኗ በቀጣይ ከዚያ ሥልጣኗ ጋር በተያያዘ ውሳኔ ቢሰጥ የሚያመጣው ተቀጣጣይ ውጤት እየታሰበበት ያለ ጉዳይ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያስረዳል። ከዚህ የቁም እስር ጋር በተያያዘ አዜብ የጉዞ ዕገዳ እንደተጣለባት ተጠቁሟል። መለስ የሞተ ጊዜ የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ዋና “ወንበዴ” የሆነው ስብሃት ነጋ “የግለሰብ ሌጋሲ የሚባል የለም፤ ሌጋሲ … [Read more...] about አዜብ መስፍን በቁም እስር ላይ ነች
የመለስ “ሌጋሲ” በአዜብ መታገድ መቃብር ገባ
ህወሓትን ለመምራት ደብረጽዮን፣ ዓለም፣ ጌታቸውና ፈትለወርቅ ታጭተዋል እርስበርሱ ሲነታረክ የቆየው የህወሓት ግምገማ አባይ ወልዱን በማባረርና አዜብ መስፍንን በማገድ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። እነደብረጽዮን የሚመሩት የማጽዳት ዘመቻ በመለስ “ሌጋሲ” ላይ አብሮ እርምጃ ወስዷል። የመሪነቱን ቦታ ፈትለወርቅ፣ ደብረጽዮን፣ ጌታቸውና ዓለም እየተፎካከሩበት ነው ተብሏል። አፍቃሪ ህወሓትና የህወሓት ልሳን ከሆኑ የዜና ምንጮች በቀረበው መረጃ መሠረት ሰሞኑን በግምገማ እርስበርሱ ሊበላላ ደርሶ የነበረው የህወሓት ግምገማ “ቆራጥ” እርምጃዎችን ወስዷል። በዚህም መሠረት በመለስ ዜናዊ ምትክ የ“ወንበዴ” ድርጅቱ ኃላፊ ሆኖ ሲሠራ የነበረው አባይ ወልዱ ከሊቀመንበርና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊነቶች ተወግዶ በተራ አባልነት እንዲቀጥል ተወስኖበታል። ከአባይ መሰናበት በተጨማሪ “አዜብን መንካት የመለስ … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” በአዜብ መታገድ መቃብር ገባ
እነ አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብታቸውን በማስረከብ ለመፈታት እየተደራደሩ ነው
ንጉሥ ሳልማን በቅርቡ ከሥልጣናቸው ወርደው በአልጋ ወራሹ ይተካሉ እስራኤል ከሳዑዲ ጋር የመረጃ (የስለላ) ልውውጥ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለች በሙስና እና የመንግሥትን ሃብት አለአግባብ በመጠቀም በሚል በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የሳውዲ ልዑላንና ሌሎች ታላላቅ ባለሥልጣናት ከእስር ለመውጣት እስከ 70 በመቶ ሃብታቸውን ለመንግሥት ለማስረከብ እየተደራደሩ መሆናቸው ተሰማ። አል-አሙዲ በ30 በመቶ መቀጠል አሳሳቢ ሆኗል። ንጉሥ ሳልማን ሥልጣናቸውን ለአልጋ ወራሻቸው ሊያስረክቡ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሳዑዲ ጋር ለየት ያለ ግንኙነት የጀመረችው እስራኤል ከሳዑዲ ጋር በሚፈለገው መልኩ ለመተባበር ፈቃደኝነቷን አስታወቀች። በኢትዮጵያ ላለፉት 26ዓመታት ከግብር ነጻ ንግድ በማካሄድ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የነበረው የህወሓት የቅርብ ወዳጅ አል-አሙዲ በሳዑዲ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ጊዜ ጀምሮ … [Read more...] about እነ አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብታቸውን በማስረከብ ለመፈታት እየተደራደሩ ነው
እነ አላሙዲ በሳዑዲ “ቂሊንጦ”
ቅዳሜ ማታ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሳዑዲ ልዑላንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም አላሙዲ መሬት ላይ ተኝተው የሚያሳይ ፎቶ ዴይሊ ሜይል በድረገጹ ላይ ለቋል። “ቂሊንጦ” በሚሰኝ ሁኔታ “አገልግሎት” እየተሰጣቸው እንደሆነ ከዴይሊ ሜይል ዘገባ ለመረዳት ይቻላል። “ከሳዑዲ መንግሥት ምንጮች የተገኘ” በማለት ዴይሊ ሜይል የለቀቀው ይህ ፎቶ እንደሚያሳየው አይነኬዎቹ እነ ልዑል አልዋሊድ (የእኛን ጉድ አላሙዲንን ጨምሮ) በሥሥ ፍራሽ ላይ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል መሬት ላይ ተኝተው ይታያል። ጋዜጣው ሲያላግጥም “የሳዑዲ ልዑላን ባለ አምስት ኮከብ እስርቤት ውስጥ” በማለት ለዘገባው ርዕስ ሰጥቶታል። ጋዜጣው ሁኔታውን “የሚያሳፍር” በማለት የጠቀሰው ሲሆን በትንሽ ብርድልብስ ተጠቅልለው ለዚህ ውርደት መብቃታቸው ቢፈቱ እንኳን ውርደቱን ተቀብለው ለመኖር የሚያቅታቸው እንደሆነ አስተያየት … [Read more...] about እነ አላሙዲ በሳዑዲ “ቂሊንጦ”
ደላላው “ባለሃብት” አል-አሙዲ በቁጥጥር ሥር ውሏል!
“ማንንም አንፈራም!” ንጉሥ ሳልማን የሳዑዲ የዙፋን ተስፈኛ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን 11 ልዑላንን እና 38 የመንግሥት ባለሥልጣናትን (የቀድሞውን ጨምሮ) እንዲሁም የንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ። ደላላ (ተጠሪ ወይም front man) ባለሃብት እንደሆነ የሚነገርለት በግማሽ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሞሐመድ አላሙዲ (አል-አሙዲ) በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል መሆኑን ጎልጉል አረጋግጧል። ንጉሥ ሳልማን የሕዝብን ንብረት የመዘበረ ማንም ሰው ተጠያቂ ይሆናል፤ “ማንንም አንፈራም” ብለዋል። ዜናው የተወሳሰበ ትስስር ያላቸውን የአላሙዲ “ወዳጆች” ከፍተኛ ሥጋት ላይ ጥሏል። ዜናው በመንግሥታዊው የዜና ወኪል አል-አረቢያ ከተዘገበ በኋላ በተለያዩ ምዕራባዊ የሚዲያ ውጤቶች እንደተነገረው ድርጊቱ “ፈጽሞ ያልተጠበቀ” እና በርካታዎችን “ያስደነገጠ” ሆኗል። በሃብታቸው … [Read more...] about ደላላው “ባለሃብት” አል-አሙዲ በቁጥጥር ሥር ውሏል!
ህወሓት የኦህዴድን የበላይነት በመቀበል ኦሮሞ ጠ/ሚኒስትር ሊሾም ነው
ጉዳዩ በህወሓት ዘንድ መጠነኛ መከፋፈል ፈጥሯል “ኃይለማርያም ደሳለኝ የመስዋዕት በግ?” ሲሉ የመረጃው ሰዎች አዲሱን ዜና ይጀምራሉ። የጎልጉል ታማኝ መረጃ አቅራቢዎች በኦሮሚያ ከአሁን በኋላ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ኃይል - ህወሓት ዕድል ፈንታ እንደሌለው ማመኑን ይጠቁማሉ። የኦሮሞ ጥያቄ የወንበር መሆኑን ህወሃት እንዳመነና ይህንኑ እምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መነሳቱን ለ“ወዳጆቹ”፣ ጌቶቹና አሳዳሪዎቹ ማሳወቁንም ይጠቁማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ይኸው ሁኔታ በህወሓት ውስጥ መጠነኛ መከፋፈልን እንደፈጠረ ይነገራል። እንደዜናው ሰዎች ከሆነ ህወሓት “የወለደውን፣ ያሳደገውንና፣ የሾመውን” ካድሬ ኢትዮጵያን እንዲመራ አጭቶታል። መረጃው ጎልጉል ካነጋገራቸው የተለያዩ ወገኖች በአሉታዊና በአዎንታዊ መልኩ አስተያየት ቢሰጥበትም ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆንና የኦሮሞ … [Read more...] about ህወሓት የኦህዴድን የበላይነት በመቀበል ኦሮሞ ጠ/ሚኒስትር ሊሾም ነው
“ሁሉንም ፈንቅል HR 128ን አምክን” – በሶማሊያ ዕልቂት የህወሓት ሥውር እጅ?
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ የተነሳበትን ዓላማ ለማሳካት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም የሚለው አስተያየት አሁን አሁን አከራካሪ ሊሆን አይችልም። በብዥታ ውስጥ የነበሩት እንኳን አሁን “ምን እየሆነ ነው” በሚል ራሳቸውን እየጠየቁ ያለአስረጂ ምላሹን እያገኙ ህወሓትን በጥርጣሬ የሚያዩበትን መነጽር አውልቀዋል። ይህ እንግዲህ በውጪውም ዓለም ጭምር እየሆነ ነው። በአስገንጣይነትና በተገንጣይነት ሲርመጠመጥ የነበረው ህወሓት ባላሰበው መልኩ፣ በህልሙም አስቦት የማያውቀውን፤ የአገር መሪነት ያስረከቡት “ቀጣሪዎች” ሳይቀሩ አሁን አሁን ፊት ለፊት “አናምንህም” ባይሉትም፣ ዙሪያውን እየዞሩትና እያዞሩበት ይገኛል። ብዙ ምልክቶች አሉ። አንደበታቸውን የከፈቱና “ዋ” የሚሉም እየተነሱ ነው። ከየአቅጣጫው የሚነሳውን ይህ ከላይ ጨምቀን ያቀረብነውን ጉዳይ የሚያጠናክር መረጃ ጎልጉል … [Read more...] about “ሁሉንም ፈንቅል HR 128ን አምክን” – በሶማሊያ ዕልቂት የህወሓት ሥውር እጅ?