እነ ለማ የሚያራምዱት የጽንፍ ፖለቲካ ነው - ወርቅነህ ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ለአሜሪካኖች “እኔ እንድመረጥ ድጋፍና ጫና ብታደርጉ የናንተን ፍላጎት ለማሳካት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነኝ” በማለት አሜሪካኖችን ሲወተውት እንደነበር ታወቀ። እርሱን እንዲመርጡ ድጋፍ ለመጠየቅ መነሻ አድርጎ ያቀረበው ሃሳብ “እነ ለማ ‹ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ› ቢሉም የሚያራምዱት የጽንፍ ፖለቲካ ነው፤ ከአማራው ጠቅላይ ሚኒስትር ቢመደብ ወደ አማራ ማድላቱ አይቀርም፤ ከሁለቱም ያልሆነ እንደእኔ ያለ ሰው መመረጥ አለበት” የሚል ነው። በግልጽ በማይነገር የጄኔራልነት ማዕረግ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበረው ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ይህንን ያለው ሰሞኑን በአሜሪካ ቆይታው ከፖሊሲ አውጪዎችና የዓለምአቀፍ ግንኙነት ባለሙያዎች ጋር ተገኝቶ ስለወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታና መፍትሄ ማብራሪያ ሲሰጥ ነው። … [Read more...] about ወርቅነህ አሜሪካኖችን “ምረጡኝ፤ አስመርጡኝ” ያለበት የጠ/ሚ ምርጫ ተውኔት ይፋ ሆነ
News
ዜና
የከረረው የአሜሪካና የህወሓት “ወዳጅነት ተበጥሷል”
አጋራችን ብትሆኑ ኤምባሲችን ወደየሩሳሌም እንዲዛወር ድምፅ ትሰጡ ነበር - አሜሪካ ለህወሓት ህወሓት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳያውጅ በጌቶቹ ከተነገረው በኋላ በራሱ መንገድ መሄዱ የግንኙነት “ገመዱን እንደበጠሰው” ተነገረ። አሜሪካ ኤምባሲዋ ወደየሩሳሌም እንዳይሄድ የተቃወሙ አገራትን ዋጋ ትከፍላላችሁ ያለችውን በህወሓት ላይ ተግብራዋለች። አውሮጳውያን የጠነከረ ተቃውሟቸውን በህወሓት ላይ በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል። በባራክ ኦባማ አስተዳደር የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት ቶም ማሊኖውስኪ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የአገሪቱን ሁኔታ የገለጹበትን አስመልክቶ ጎልጉል ይህንን መዘገቡ ይታወሳል። “ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቸኛ ሃላፊነት ነው፤ … በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ … [Read more...] about የከረረው የአሜሪካና የህወሓት “ወዳጅነት ተበጥሷል”
ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የትኛው ኦህዴድ?
በደም ወይስ በድርጅት አባልነት? ወርቅነህ ገበየሁ ወዴት ወዴት? ወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ፍላጎት መኖሩን፣ እሱም ቦታውን እንደሚፈልገው የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች ጠቆሙ። ወርቅነህ ቀደም ሲል ከነበረው ሃላፊነት፣ ኦሮሞ አይደለም በሚል የሚቀርብበት ክስ፣ በ1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለተካሄደው ግድያ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው በሚል ስለሚወነጀል ኢህአዴግ ራሱ የበጠሰውን የሕዝብ እምነት ሊቀጥል አይችልም የሚል ስጋት መኖሩንም አመላክተዋል። ቀደም ሲል በጄኔራል ማዕረግ የፌደራል ፖሊስ አዛዥ የነበረው፣ ከዚያም በጁነዲን ሳዶ እግር ተተክቶ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር የሆነው በኦሮሚያ ማሊያ ለትግራይ የሚጫወተው ወርቅነህ፣ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነትም የታጨው የኦሮሞን ሕዝብ ለማባባበል ነበር። እንደታሰበው ሳይሆን ግን በተሾመ ማግስት … [Read more...] about ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የትኛው ኦህዴድ?
በኢትዮጵያ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው ወታደራዊ አገዛዝ ሊታወጅ ነው!
በኢትዮጵያ በተከታታይ የዘለቀውን ሕዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠር የተሳነው ህወሓት በኢትዮጵያ በአስቸኳይ አዋጅ ስም አገሪቷን በወታደራዊ አስተዳደር ስር ለማስተዳደር ኣዋጅ አንደሚያወጣ ተሰማ። የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው አዋጅ ምናልባትም ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ያለፈው የኢህአዴግ ስብሰባ ወቅት ስምምነት ተደርሶበት የነበረው ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ምስረታ ህወሓት ኣልቀበለውም ብሏል፥ ይህንን ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣኑ እንዲወርድ በህወሓት ግፊት ሲደረግበት ቆይቷል፤ የሃይለማርያም በፈቃዱ ከስልጣን መውረድ ለህወሓት የደኢህዴንን ስጋት እንዲቀንስለት ታስቦ የተደረገ ግፊት ነው፥ የኦህዴድ መክዳትና የብአዴን መከተል ላይ ደኢህዴን ከተጨመረ የህወሓትን ህልውና አደጋ ላይ መጣሉ ስላሰጋው ነው ህወሓት ሃይለማርያም በፈቃዱ ለቀቀ ማስባል … [Read more...] about በኢትዮጵያ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው ወታደራዊ አገዛዝ ሊታወጅ ነው!
“ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
“ስድስት ሚሊዮን ወጣት በጠላትነት ፈርጀህ ማንን ልታስተዳድር ነው?” ለማ መገርሳ ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በምሥራቅ ሐረርጌ “ቄሮ” በመባል የሚታወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እመረምራለሁ፤ ለፍርድ አቀርባለሁ ብሎ ዝቷል። “አመራሩ ብቃት የለውም” በማለት ራሱን የገመገመው ህወሓት/ኢህአዴግ ብቃት አልባነቱን ተገንዝቦ ራሱን ከሥልጣን ማግለል ሲገባው አሁንም የማሰርና የማሰቃየት ግፉን በስፋት ለመቀጠል በዕቅድ ለመቀንቀሳቀስ ማሰቡን ነው በዚህ ዜና የገለጸው። የኢትዮጵያ ወጣቶችን በሥራ በማሰማራት ለአገር እንዲጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ “አደገኛ ቦዘኔ” በማለት ሲፈርጅና ሲስር የነበረው ህወሓት አሁን ደግሞ በኦሮሞ ወጣቶች “ቄሮ” ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ለመሰንዘር ጎራዴውን እየሳለ ነው። ግፉ የበዛባቸው ወጣቶች ታላቁ ሩጫ በተካሄደበት ባንድ ወቅት ላይ “አደገኛ ቦዘኔ … [Read more...] about “ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
“አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ታዲያ ሁላችሁም ለምን ከሥልጣን አትወርዱም? "ለአመጽ የግብረ መልስ የሚሰጥ አመራር እንጂ ለችግሮች ቀድሞ መፍትሄ የሚሰጥ አመራር አይደለም"፤ "አመራሩ ህዝቡ ከሚጠብቀው በታች ነው"፤ "አመራሩ ከሽፏል"፤ የማሸማቀቅና የማስፈራራት ተግባር ነው በፓርቲው ውስጥ ያለው፤ ተመሳሳይ ዓይነት ነገር ወደ ሕዝቡ ሰርጾዋል፤ ወዘተ በማለት "በድፍረት" የተናገረው የኦህዴዱ ለማ መገርሳ እንደዚህ ብቃት የሌለውን አመራር ቢያንስ "ሥልጣኑን መልቀቅ ይገባዋል" ሳይል ወይም ራሱ ሁኔታው የማይስተካከል ከሆነ ሥልጣኑን እንደሚለቅ ምንም ፍንጭ ሳይሰጥ ንግግሩን አብቅቷል። ህወሓት/ኢህ አዴግ እንደ ድርጅት ከሽፏል! ይህ የተመሰከረው ደግሞ በራሱ በአመራሩ ነው። እስካሁን በሥልጣን ለምን እንደቆዩ እና ወደፊትም ለመቆየት ለምን እንዳሰቡ ግልጽ ቢያደርጉ የተሻለ ነው። መለስም "እስከ እንጥላችን ገምተናል" እያለ … [Read more...] about “አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እስረኞችን እፈታለሁ አለ
ላለፉት በርካታ ዓመታት በየአደባባዩ "በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም" ሲል የነበረው ህወሓት/ኢህአዴግ ዛሬ በኃይለማርያም አማካኝነት "እስረኞችን እፈታለሁ፥ ማዕከላዊን እዘጋለሁ" ብሏል። ባለፉት ዓመታት በግፍ የታሰሩት በሙሉ የተከሰሱት በአሸባሪነት መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይህ መግለጫ በራሱ ህወሓት/ኢህአዴግ ሲዋሽ እንደነበር የሚያሳይ ነው ወይም ይቺ ጊዜ መግዣ የህወሓት ጨዋታ ነች። ለሁሉም በመቆየት የሚታይ ነው። የእኛ አቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ አመለካከቱ መታሰር የለበትም፥ በግፍ የታሰሩት ሁሉም የፖለቲካ እና የኅሊና እሥረኞች ህወሓት/ኢህአዴግ ይቅርታ እየጠየቀ ካሣ ከፍሎ በነጻ ይልቀቃቸው ነው። ጎልጉል! … [Read more...] about ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እስረኞችን እፈታለሁ አለ
ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከሁለት ሳምንታት በላይ ስብሰባ አድርጎ “መግለጫ” ያለውን “ቀጭን ትዕዛዝ” በማውጣት ተጠናቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በለውጥ አራማጅነት ሲጠቀሱ የነበሩት እነለማ መገርሳ “መግለጫውን” አብረው አጽድቀው ወጥተዋል። “የጨለንቆን ፍጅት የፈጸመው ማነው?” የሚለውም ደፋር አጀንዳ አብሮ የሞተ ጉዳይ ሆኗል። “ምን ይዤ (ወደ ሕዝቤ) ልመለስ?” በማለት ወደስብሰባው የገቡት ኦህዴድና ብአዴን “የተቀናጁ ተጨማሪ እርምጃዎች” እወስዳለሁ (መግደሌን እቀጥላለሁ) ለሚለው የህወሓት “መግለጫ” ይሁንታቸውን ሰጥተው ወጥተዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከወር በላይ ስብሰባ በማድረግ የደቆሰውና የፈጨውን በተስፈኞቹ ብአዴንና ኦህዴድ ላይ በመድፋት በድንፋታ ኢህአዴግ የሚለውን የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁ ከራሱ ከአገዛዙ የሚዲያ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
አስመራ ላይ የሙዚቃ ድግስ ማቅረብ – የቴዲ ተስፋ!
ለዓመታት በአገር ውስጥ የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) እንዳያሳይ የታገደው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አስመራ ላይ የሙዚቃ ድግስ ለማቅረብ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናገረ። ችግሮቻችንን አራግፈን ወደፊት መጓዝ አለብን ብሏል። ዴይሊ ሜይል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስን ጠቅሶ እንደዘገበው በእርሱ ላይ እየደረሰ ያለው ነገር እንዳለ ሆኖ ቴዲ “በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ላይ” ትኩረት ማድረግ መቀጠሉን ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤቱ ዘና ባለ ሁኔታ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። የልጅነት ዘመኑን በማስታወስ ቴዲ ሲናገር፤ “ልጅ ሆኜ እንደ አንድ አገር ስንኖር አስታውሳለሁ፤ አንድ የምናውቃት አገር ኢትዮጵያ የምትባል ነበረች፤ አሁን በዚህ ዘመን ግን የምንታወቀው በዘራችን ነው፤ ይህ ደግሞ እጅግ አደገኛ እየሆነ መጥቷል” ብሏል። ህወሓት በቴዲ የጥበብ ሥራዎች ላይ ማዕቀብ በመጣሉ በተለይ … [Read more...] about አስመራ ላይ የሙዚቃ ድግስ ማቅረብ – የቴዲ ተስፋ!
የአባዱላ አጣብቂኝ
ከሁለት ወራት በፊት “ … አሁን በደረስኩበት ደረጃ በዚህ ኃላፊነት ለመቀጠል የማያስችሉኝ ሁኔታዎች ስላሉና ፍላጉቱም ስለሌለኝ ለመልቀቅ ድርጅቴንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቄያለሁ” ያለው አባዱላ ገመዳ ዛሬ ኦህዴድን ለህወሓት ሲያግባባ በገሃድ ታይቷል። “የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ህገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ህዝባዊ ውይይት ለማካሄድ” በሚል ህወሓት የሚዘውረው “ፓርላማ” ዛሬ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። የኦህዴድ ተወካዮች በኦሮሚያ ችግር እያለ፤ የኦሮሞ ሕዝብ በረቂቅ አዋጁ ላይ በአግባቡ ሳይወያይ እንዲሁም የሁሉም አካባቢ ተወካዮች ሳይገኙና በአገሪቱ በአጠቃላይ ያለው ችግር ሳይፈታ ውይይት ማድረግ ተገቢ አይደለም ብለው ተቃውሞ አሰምተዋል። ከወራት በፊት “አሁን በደረስኩበት ደረጃ በዚህ ኃላፊነት ለመቀጠል የማያስችሉኝ … [Read more...] about የአባዱላ አጣብቂኝ