አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል!

ስለ ዓድዋ ጦርነት አንዳንድ እውነታዎች❗️

ቀን: የካቲት 23, 1888
ቦታ: አድዋ፤ ኢትዮጵያ
አሸናፊው ሀይል: ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች
አጤ ምኒልክ
እቴጌ ጣይቱ
ተክለ ሀይማኖት
ራስ መኮንን
ራስ ሚካኤል
ራስ መንገሻ
ፊታውራሪ ገበየሁ
ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ
ፊታውራሪ ዳምጠው
ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ
ኒኮላ ሊዮንቴቭ

በጣልያን በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች
ኦሬስቴ ባራቴሪ
ቪቶሪዮ ዳቦርሚዳ
ጁሴፔ አሪሞንዲ
ማቲዎ አልቤርቶኒ
ጁሴፔ ኤሊና

በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት
80,0000 መሳርያ የታጠቅ
20,000 ጦርና ጎራዴ የታጠቀ
8,600 ፈረሰኛ

በጣልያን በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት
24,804 ዘመናዊ መሳርያ የታጠቅ ወታደር
56 ረጅም ርቀት ተወርዋሪ መሳርያዎች

በኢትዮጵያ በኩል የተሰዉ ጦረኞች ቁጥር
3867 የሞቱ
ከ8000 በላይ የቆሰሉ

በጣልያን በኩል የተሰዉ ጦረኞች ቁጥር
6394 የሞቱ
1428 የቆሰሉ
ከ3000 በላይ የተማረኩ

© መልካም 74 Radio

Comments

 1. የዛሬን አያርገውና የአድዋ ድል ለመላው ጥቁር ህዝብ የድል ጮራ እንደሆነ በየትምህርት ቤቱ እንማር ነበር። አስታውሳለሁ አንድ ጊዜ በአንድ ትምህርት ቤት ግርማ ፍስሃ የተባለ የጀርመን ኗሪ አባቱን ሊጠይቅ ብቅ ይላል። ጊዜው ክረምት ነበረ። እኛም ተማሪዎች የክረትም ትምህርት እንድንማር (ሃገርህን እወቅ) አይነት ነገር ደ/ች መንገሻ ይልማ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተኮልኩለናል። ሰብሰብ ብለን በኦሮምኛ እየዘፈንን ስንቀላለድ ደወል ተደወለና ገባን። በቀኑ ግርማ ፍስሃ ተጋባዥ አስተማሪ ነበር። ሰላም ልጆች በማለት ራሱ ካስተዋወቀ በህዋላ ለዛሬ የማስተምራችሁ “አርሙኝ” ከተሰኘ መጽሃፍ ውስጥ ” አልሞትም ብዬ አልዋሽም የተሰኘውን ታሪክ በማንበብ እጀምራለሁ በማለት የአቶ ተማቹንና የወ/ሮ ጽጌረዳን በጣሊያን ወረራ ጀግንነት ማንበብ ጀመረ። በማህሉ ሲቃ ያዘውና ማልቀስ ጀመረ። ክፍሉም ሁሉ አብሮት አለቀሰ። ያ ጊዜ እንደ አሁኑ በዘር ዙሪያ ሰው ያልተሰፈረበት ሁሉም በሰላምና በህብረት የሚኖርበት የመልክዓ ምድር የመማሪያ መጽሃፋችን አርዕስት “አብሮ መኖር በዓለም ዙሪይ” የሚል እንደነበር ትውስ ይለኛል።
  ወደ ዛሬው የዘር ፓለቲካ ስንመለስ ደግሞ ሌቦች ጀግና የሚባሉበት፤ ወንድም እና እህቱን ገድሎ ሰው የሚፎክርበት፤ ለዘሬ፤ ለጎሳዬ፤ ለክልሌ በማለት ሰው ሁሉ በየጎራው የሚፎልልባት፤ በብሄር ነጻነት ስም ባርነት ውስጥ የምንኖርበት በጥቅሉ የደንበር ገተር ጊዜ ላይ እንገኛለን። አድዋ ከሃገሪቱ አራት ማዕዘናት ሃበሾች ተጠራርተው ጠላትን ያሳፈሩበት የድል ጎራ ናት። የአድዋው ድል የጋራ ድል ነበር ነውም። ሼሁ ከመስጊድ፤ ቄሲ ከመንበሩ፤ ገበሬው ከእርሻው፤ ነጋዴውና ሌላውም ተጠራርተው የነጭ መንጋን ያሳፈሩበት የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ጮራ! ታሪክን ሰርተው በታሪክ ውስጥ ያለፉ ጀግኖች ደምና አጥንት ዛሬም በአድዋ ሸለቆና ተራራዎች ይጣራል፤ ይናገራል። የሚሰማ ግን የለም። የክልል ፓለቲካ ያሰከረው የእብድ ክምችት ያፈራች ሃገር። ሲያሳዝን! በአዲስ አበባ ለሰላም ገቡ የተባሉ ጠበንጃ አንጋችና አፋዊ ፓለቲከኞች በለመድት የፓለቲካ የሾኬ ጠለፋ ሰውን ያተራምሳሉ። መማር ማለት እንዲህ ነው። ነጻ እናወጣሃለን የሚባለውን ሰው እሳት ውስጥ እየገፉ መክተት። ዶ/ር አብይም እየቆ መንግሥቱንና አቶ መለስን ለመምሰል ጥቂት ጊዜ የቀረው ይመስላል። በቅርቡ ከብዙ ውጣ ውረድ በህዋላ አንድ የደረስኩበትን መረጃ አልባ የሆነ የራሴን አስተያየት ልስጥ። ሁልጊዜ ኢንጂኒየር ስመኘውን ማን ገደለው በማለት እጠይቅ ነበር። መልሱ ጠ/ሚሩ ናቸው። እንዴት ለሚል። ባፋቸው። ግድቡን በጊዜው ሄደው ከጎበኙ በህዋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እጠቅሳለሁ ” ግድቡ በአስር ዓመት ጊዜም አያልቅ” ይህ ይፋዊና ፌዚያዊ ንግግር ኢንጂኒየሩን ጎድቶታል። በዚህም የተነሳ ራሱን ለማጥፋት ተገዷል። የእኔ ድምዳሜ እሱ ነው። አብይ የማያውቀው የእውቀት ሚዛን የለም። መለፍለፍ ልምድ አድርጎታል። ቃልም ተግባርም በሚዛን ሲሆን መልካም ነው። እንዲሁ ራስን እንደ (chameleon ) ከከባቢ ጋር እየለዋወጡ ቢዘላብድት ዋጋ የለውም። የሚገርመኝ ነገር ባለስልጣኖች እየቆዪ የንጉስ አይነት መልክና ባህሪን ይላበሳሉ። መታመም ነው። ንጉስ ድሮ ቀረ። ይህን አስቀድመው ያዪት እውቁ የወረሂመኖው ሸህ ሁሴን ጅብሪል እንዲህ ብለው ነበር።
  ያምናን ቀን አማሁት ላፌ ለከት የለው፤
  የዘንድሮው መጣ እጅ እግር የሌለው፤
  ቀን ይወጣል ብየ ብጠብቅ ባስጠብቅ፤
  እንኳን ቀን ሊወጣ ጨለማ ነው ጥቅጥቅ፡፡
  ይህ ግጥም የሚያሳየው ትሻልን ትቼ ትብስን እንዲሉ አይነት ነው። ብቻ የጋራ የሆነ ድላችንን እያንቋሸሽን የአንድ ቀን አውሎ ንፋስ የሚደረምሰውን የክልልና የቋንቋ አጥር ስንገነባ ኖረናል ተብለን አፈር ይመለስብናል። አታድርስ ነው። ድንበር ተሻጋሪ ሥራ ከመስራት ላስን አጥቦና አሳንሶ መሞት! እንትፍ ይቅርብኝ!
  አድዋ የጀግኖች የድል ሥፍራ። አድዋ የብዙሃን መቃብር ቦታ። አድዋ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ጮራ። ኑሪ ለዘላለም ለህያዋን ተስፋ ለወደቁልሽ ሰማእታት የክብር ሥፍራ!!

Speak Your Mind

*