ፍትህን ሰቀለው በፍትህ ስም የፕሮፓጋንዳ ዳንኪራ – የጨለማው ሳምንት!!

የ“ፍትህ” ወይስ የጨለማ ሳምንት? (ርዕሰ አንቀጽ) “ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ጸጥ ይላል!” ይህ የተጻፈው በአንድ የጎንደር እስር ቤት ውስጥ ነው። የተጻፈው በግድግዳ ላይ ሲሆን በብዕር ወይም በቀለም አይደለም። ፍትህ ከተጓደለባቸው አንዱ የእጁን ጣት በመብጣጥ በደሙ ነው። ፍትህ የተዛባባቸው ይህንኑ አባባል ልክ እስር ቤት እንደገቡ ይሳለሙታል። በብዙ የአገሪቱ ማጎሪያዎች ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት ገላጭ ሃረጎች ይጻፋሉ። ፍትህን አደባባይ […]

Read More...

ህወሓት: በነፃ ፕሬስ መቃብር ላይ የቆመ አገዛዝ!

ኢትዮጵያ በፕሬስ ነፃነት ከዓለም 150ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች! አገሪቱ የነፃ–ሚዲያ ባለቤት የምትሆነው በህወሓት መቃብር ላይ ነው! ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን ምክንያታዊ በሆኑ ነገሮች መግለጽ የሚችልና ፖለቲካዊ ንቃት ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገው ትግል፤ ካለ ነፃ ፕሬስ ተዋፅኦ ስሙር ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ገዥው ኃይል የግሉ ፕሬስ ለአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና አሳታፊነት ያለው የፖለቲካ ሥርዓት […]

Read More...

ዕርቅና ድርድር ቢያይዋቸው፤ ቢያይዋቸው!

(ርዕሰ አንቀጽ) ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታትና ከዚያም በፊት ስለዕርቅ ያልተናገረ የፖለቲካ ቡድን የለም ለማለት አይቻልም፡፡ ደርግ ስለ ዕርቅ ተጠይቆ አልሰማም አለ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም የአገዛዝ መንበሩ ላይ ከመቆናጠጡ ጀምሮ ስለ ዕርቅ ይወራል፡፡ አዳዲስ የሚፈለፈሉ የተቀናቃኝ ድርጅቶች በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ስለ ዕርቅ ያወራሉ፡፡ የገባውም ያልገባውም ስለ ዕርቅ ይናገራል፤ ይሰብካል፤ ያስተምራል፤ … ይህንን ሁሉ አልፎ “እኔም ያገባኛል” በማለት […]

Read More...

የአጋንንት ፖለቲካ – ውጣ!!

(ርዕሰ አንቀጽ)

ልብ ማለት ያቃተን ለምን ይሆን? የማንሰለጥነውስ ለምንድን ነው? በፖለቲካ ትግል ውስጥ ዕድሜ ገፍተን የማንበስለው እስከመቼ ነው? አድሮ ቃሪያ፣ አድሮ ጥሬ … እንዲሉ በጫጫታ ትውልድን የምናሰቃየው ስለ ምንድን ነው? ብዙ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል። ይህ በድህነትና በችጋር የሚቃጠለው ህዝብስ ማን ያስብለት? ማን ይድረስለት? በእነማን ብርሃን ይመልከት? ማን ከጨለማ እንዲወጣ ይምራው? ሩብ ምዕተ ዓመት እንደተባላን እንቀጥል? ያሳዝናል? ያስለቅሳል፣ […]

Read More...

“ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”

(ርዕሰ አንቀጽ)

ኢትዮጵያ ድንቅ አገር ናት። ይህ ማስደነቋ ደግሞ ከሕዝቧ መደበላለቅ ጋር ውበቷን እጅግ አጉልቶታል። ከዛሬ 40ዓመት በፊት የተጀመረው ጎሣ፣ ዘር፣ … ላይ ትኩረት ያደረገው ገዳዳ የግራ ፖለቲካ ኢትዮጵያ አላት የተባለውን የፖለቲካ ችግር ሲፈታ ሳይሆን ይበልጡኑ ሲያወሳስበውና ሕዝብን ግራ ሲጋባ እዚህ ደርሰናል። በዚያ ርዕዮት የተጠመቁ ሕዝብን ሲያስፈጁ እንጂ ለሕዝብ ጥቅም ሲያመጡ አልታዩም፤ በዚያ የጎሣ ፖለቲካ ጥርሳቸውን የነቀሉም […]

Read More...

ለህወሃትና አገልጋዮቹ “አንቱታን” ነፈግን

ለአንባቢያን ማስታወሻ

የኢትዮጵያ ልዩ መጠሪያዎች ከሚባሉት መካከል “ሰው አክባሪነት” አንዱ ነው፡፡ በበርካታው የአገራችን ባህል ሰዎች በዕድሜያቸው የአንቱነትን ማዕረግ ይጎናጸፋሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በሥራቸው፣ በሙያቸው፣ በሕዝብ ዘንድ ባላቸው ከበሬታ ይህ የአንቱነት ማዕረግ ይሰጣቸዋል፡፡ በዕድሜያቸው በጣም ልጆች የሆኑ እንኳን ባላቸው መንፈሣዊ አገልግሎት ወይም ልዕልና በታላላቆቻቸው ሳይቀር አንቱ ይባላሉ፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን አንቱ ብሎ መጥራት ለኢትዮጵያዊ የሚነገረው ወይም የሚማረው ግብረገብ አይደለም፡፡ እንደ […]

Read More...

የጻድቃን “መፍትሔ ሃሳቦች” – ልመና? ጥገና? ወይስ ህወሃት ቁጥር 2?

(ርዕሰ አንቀጽ)

የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅና አለአግባብ ለመበልጸግ ያሰቡ አውሮጳውያን በአሜሪካ አካባቢ ያሉትን አገሮች በጥጥና በሸንኮራ አገዳ እያለሙ መጠነሰፊ ሃብት ለማጋበስ በሰላም የሚኖሩ አፍሪካውያንን በግፍ እያጋዙ ዓለማችን እስካሁን ዓይታ የማታውቀውን ዓይነት የባርነት ሥርዓት ለበርካታ ዓመታት አካሂደዋል፡፡ ከአፍሪካ ወደ አሜሪካ በግፍ የተጋዙት ወገኖች በመንገዳቸው ያሳለፉት መከራና ከዚያም ለማሽን እንኳን የሚሰጠው ዕረፍትና ጥገና እነርሱ ተነፍገው ለመቶዎች ዓመታት ከምንም ጋር የማይወዳደርና […]

Read More...

የህወሃት አውሬነት፣ ከውልደት እስከ ህልፈት? ወይስ አገር “እስክትፈርስ”?

(ርዕሰ አንቀጽ)

* ይብላኝ ለእናንተ ለአውሬው ቀንድና ግምባሮች! ፈቃደኛ ስለመሆኑ ባደባባይ ባልተጠየቀው የትግራይ ህዝብ ስም ራሱን ተገንጣይ ብሎ ሰይሞ አገር የሚገዛው ህወሃት፣ ከቀን ወደ ቀን ግፍ እየመከረ ነው። በአገር ስም እስከ አፍንጫው በታጠቀው ጠመንጃና በዘረፈው ሃብት በመተማመን በያቅጣጫው ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ነው። እስር ቤት አጉሮ  እያሰቃየ ነው። ያልፈጸመውና የማይፈጽመው ሰቆቃ የለም። ህጻን፣ አዋቂ፣ አዛውንት፣ እናት፣ አባት ሳይመርጥ የጥይት […]

Read More...

የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!

(ርዕሰ አንቀጽ)

ከልብ በመነጨ፣ ፍጹም በሆነ የወገን ፍቅር በሶማሊያ በውትድርና ላሉ ወገኖች ፈጣሪ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንመኛለን። በማያውቁት ጉዳይ የበረሃ ጥሩር ለሚገርፋቸውና የነፍሳቸው ዋጋ በውል ለማይታወቀው ወገኖቻቸን እንኳን አደረሳችሁ ከማለት በላይ ሁሉም ወገኖች ድምጽ እንዲሆኗቸው እንጠይቃለን። በወር 30 ዶላር አበል ህይወታቸው ላለፈና አሁንም እያለፈ ለሚገኙት ሃዘናችን ትልቅ ነው። ትርጉም በሌለው ጦርነትና ለወደፊት ንጹሃን ዋጋ የሚከፈሉበት የፖለቲካዊ ቁማር ስትራቴጂ […]

Read More...

ይህ ረሃብ “ፖለቲካዊ ችጋር” ነው!!

“በቀን ሦስቴ እንመግባችኋለን”

ህወሃት ለአገራችን የቀመመው የበቀልና የተላላኪነት ፖለቲካ ገና ጦሱ አልጀመረም። ግን ሊመጣ ግድ ነው። በንጉሡ ወቅት ተርበናል። በደርግ ጊዜ ተርበናል። ኢህአዴግ ከመጣ ጀምሮ የታዩት ርሃቦች ግን ለየት ያሉ ናቸው። ስለዚህ ርሃቡም ሆነ ችጋሩ ፖለቲካዊ ነው ቢባል ያስማማል። ኢሣ የግጦሽ ሳር ሲያጣ ወደ ጎረቤቶቹ ያመራ ነበር። አፋር ተመሳሳይ ችግር ሲገጥመው ከብቶቹን እየነዳ ችግርን አሳልፎ ይመለስ ነበር። መጠነኛ […]

Read More...