ከሠላሳ ሰባት ዓመት በፊት የተካሄደው የሞስኮ ኦሊምፒክ ሲነሣ ቀድሞ የሚመጣው የሚወሳው ረዥም ርቀት ሯጩ ምሩፅ ይፍጠር ነው፡፡ የድል ቁርጠኝነት የተሞላበት አሯሯጡ የመላው ዓለምን ምናብ ሰንጎ መያዙ አይረሳም፡፡ በሞስኮ ኦሊምፒክ በሁለቱ ርቀቶች በ5,000 ሜተርና በ10,000 ሜትር ለተቀናቃኞቹ ዕድል ሳይሰጥ ተፈትልኮ የሮጠበትና ያሸነፈበት መንገድ ‹‹ይፍጠር ዘ ሺፍተር›› (ማርሽ ለዋጩ ምሩፅ - አካለ ማርሹ ምሩፅ) የተባለበትን ዳግም ያረጋገጠበት ነበር፡፡ በሞስኮ ድሉ ከተመሰጡና አርአያ ከሆነላቸው መካከል በወቅቱ የሰባት ዓመት ልጅ የነበረው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ውድድሩን በትራንዚተር ሬዲዮ ጆሮውን ደቅኖ ሲከታተል አንድ ቀን የርሱን ዱካ እንደሚከተል አልሞ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን የኦሊምፒክ ብርሃን ከዘጠና ሦስት ዓመት በፊት የዳሰሰው በፓሪስ ኦሊምፒክ አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኰንንና የክብር … [Read more...] about “ሐሩርም ይሁን በረዶ እኔ ከማሸነፍ የሚገታኝ አንዳች ኃይል የለም” – “Yifter the Shifter”!
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
የእምዬ ምኒልክ ውለታ
ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ስመ ገናናው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከዚህ አለም በስጋ ካለፉ 103 ዓመት ሲሆናቸው አባ መላ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ደግሞ ዘጠና አመት ሆናቸው። ዳግማዊ አጤ ምኒልክና አባ መላ በስጋ ካለፉ ወደ አንድ ክፍለ ዘመን የሚጠጋ ዘመን ቢቆጠርም ስለታላቅነታቸውና ስለአሻራቸው ግን ዛሬም ገና አውርተን አልጠገብንም። በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ትዕዛዝ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ለኢትዮጵያውያን አስፈላጊ የሆኑ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ባቡር [1893]፣ ስልክ [1882]፣ ፖስታ [1886]፣ ኤሌክትሪክ [1889]፣ አውቶሞቢል [1900]፣ ባህር ዛፍ [1886]፣ የውሃ ቧንቧ [1886]፣ ዘመናዊ ህክምና [1889]፣ ሆስፒታል [1890]፣ የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች [1904]፣ ባንክ [1898]፣ ገንዘብ … [Read more...] about የእምዬ ምኒልክ ውለታ
የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ
የጣና በለስ ፕሮጀክት አጭር ታሪክ የጣና በለስ ፕሮጀክት ልማታዊ ግቦች/ህልሞች ምን ነበሩ? የጣና በለስ ፕሮጀክት በአፄው ስርዓት ተጠንስሶ፥ በደርግ አብቦ፥ በህወሀት/ኢህአዴግ እንዴትና ለምን ፈራረሰ? ዛሬ በጣና በለስ ላይ የተጋረጠው አዲስ እና አስደንጋጭ አደጋስ ምንድን ነው? መፍትሄውስ? መግቢያ የአባይ ተፋሰስ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ተፋሰሶች የላቀ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው ልዩ ቦታ በመሆኑ በርካታ ጥናቶች ተደርገውበታል። የመጀመርያው የአባይና ጣና ዳሰሳ ጥናት የተካሄደው በእንግሊዞች ነበር። ቀጣዩ ዝርዝርና ጥልቅ ጥናት የተካሄደው በአጼ ኃይለሥላሴ ልዩ ጥያቄ ሲሆን ምክንያቱም አወዛጋቢው የእንግሊዝና ጣልያን በ1925 ዓ.ም የተፈራረሙት ውል ነበር። ይህ የወራሪ ሃይሎች ውል ጣልያን ኤርትራ የሚገኘውን ቅኝ ግዛቷንና ሶማሌ ያለውን ቅኝ … [Read more...] about የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ
ኮንሶ – የግፍ ምድር!
አንደኛዋ ባለቤታቸው ሶስት ጊዜ ቀዶ ጥገና አድርጋለች። ሌላኛዋ ባለቤታቸው ከአንድ ልጇ ጋር ሁሉም እስር ላይ ናቸው። እመጫትም ከእርጥብ ልጇ ጋር ታስራለች። እነዚህ ማሳያ እንጂ በኮንሶ ከእስር የተረፉ ተሰደዋል። በወረዳው ያሉት 43 ትምህርት ቤቶች እስር ቤቶችና የወታደሮች ካምፕ ሆነዋል። ወደ አጎራባች ቀበሌ ወይም ጫካ የመሸጉ ሰዎች ህይወታቸውን የሚገፉት በመከራ ነው። ይህ ሁሉ ምሬት ሲሰማ ክልሉ ምንም ነገር እንደሌለ ነው የሚናገረው - ኮንሶ ግን ፍጹም ግፍ የሚፈጸምባት ሆናለች! ህዳር 27 ቀን 2016 ቪኦኤ ያናገራቸው ሁለት የኮንሶ ነዋሪዎች “ኮንሶዎች የሚኖሩት በሌላዋ ኢትዮጵያ ነው” ይላሉ። በኮንሶ መተንፈስ አይቻልም። መቃወም አይፈቀድም። ጥያቄ ማቅረብ ክልክል ነው። የሚማርበትን ዩኒቨርሲቲና የራሱን ስም ለጥንቃቄ ሲል በመደበቅ አጭር ቃለ ምልልስ ያደረገው የኮንሶ ተወላጅ … [Read more...] about ኮንሶ – የግፍ ምድር!
ህወሃት እጅ ላይ የንጹሃን ደም እየተንተከተከ ነው!! የምትኮሩ በዚህ ኩሩ
ህወሃት የታሪኩ ካስማና ማገር ከአስከሬን ጋር የተጣበቀ ስለመሆኑ የሚመሰክሩበት የሩቅ ሰዎች አይደሉም። አብረውት በበረሃ የነበሩ፣ አብረውት አመራር ሲሰጡ የኖሩ፣ “በሚያራምዱት አቋም” ከድል በፊትና በኋላ የተለዩት በተለያዩ ሚዲያ ላይ እንደመሰከሩት ህወሃት ደም ምሱ፣ አስከሬን ትራሱ ነው። በነዚሁ የቅርብ ሰዎቹ የተሰሙት ምስክርነቶች ስም፣ ቦታ፣ ጊዜ በመጥቀስ በወቀቱ እዚያው እንደነበሩ በማረጋገጥ እንጂ እንዲሁ በመላ አልነበረም። እነሱ ለአብነት ተነሱ እንጂ ሰለባዎች በየጊዜው አዳዲስ መረጃ ይዘው ብቅ ማለታቸው የተለመደ ነው። እዚህ ላይ ሌሎችም አይረሱም። ቅድሚያ ስለ ሌሎቹ። በቦታው የነበረ የዓይን እማኝ፤ ደደር 1983 የጅጅጋ ሆቴል ባለቤት ዓለምዘውድ እንዴት ሞተች? ዓለምዘውድ ቁመቷ ረጅም፣ ሰውነቷ ሙሉ፣ አሣ የምትመስል ጠይም፣ ደግና ርኅሩኅ እንደነበረች የሚያውቋት … [Read more...] about ህወሃት እጅ ላይ የንጹሃን ደም እየተንተከተከ ነው!! የምትኮሩ በዚህ ኩሩ
“ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ” እናት
የለቅሶ ሳግ በያዘው አንደበት የመረረ ሃዘን ይሰማል። ተናጋሪዋ የሚሰሩት ድራማ ወይንም ዘጋቢ ፊልም ሳይሆን በትክክል የደረሰባቸውን ነው። የልጃቸው አስከሬን እንደ ምናምንቴ በማዳበሪያ ተደርጎ ነው የተሰጣቸው። ልብ ይነካል። ያማል። ጉዳዩ ከሃዘንም በላይ ይሆናል። አንድ ልጃቸው "መመኪያዬ" የሚሉት ተገደለባቸው፤ ሌላኛው ክፉኛ ተደብድቦ ታሟል፤ ሁለቱ ታስረዋል። እኚህ የ65 ዓመት አዛውንት ሲያልቅ አያምር ሆነና ባዶ ሆኑ። "ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ" አሉ። አስከትለው አስከሬኑ መበላሸቱንና ደም ይፈሰው እንደነበር ገለጹ። ወግ አይቀር ተቀበረ። አሁን አሁን "ወዴት እየሄድን ነው" ከማለትም ያለፈ ይመስላል። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የወረዳው አስተዳዳሪ "በአሁኑ ሰዓት እንዲህ ያለ ችግር የለም" ማለታቸው፣ ዋና አስተዳዳሪውና የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምላሽ ለመስጠት አለመፈለጋቸው ሌላው … [Read more...] about “ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ” እናት
መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያ መድረክ
ለኢትዮጵያ የፓለቲካ ቅራኔ መፍትሄው እርቅና መግባባት መሆኑን ከሚጠቁሙና ከዚያ አልፈው የሽምግልናና የማግባባት ስራ ከሚሰሩ ስብስቦች አንዱ "መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ነው። ዛሬ ከመድረኩ ሁለት አባላት በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን የ"መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ሰብሳቢ ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ እና የመድረኩ አባል ዶ/ር ገበየሁ እጂጉ ናቸው። ያዬ አበበ ፎረም 65 አስተባባሪ … [Read more...] about መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያ መድረክ
Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
Ato Emmanuel Abraham who had served his country in a number of important diplomatic and ministerial posts for nearly four decades and half (1931-1974) has died at a great age of 103 on Wednesday. Emmanuel was ambassador to Britain and Italy and cabinet minister and director general at the Ministry of Foreign Affairs and director general of the Ministry of Education and Fine Arts, Minister of Posts, Telegraphs and Telephones; Minister of communications and Transport; and finally, minister of … [Read more...] about Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
ኢሰመጉ ከየት ወዴት?
አምስት ዓረፍተ ነገሮች፤ ኢሰመጉ መንፈሳዊ ተልእኮ ያለው መንፈሳዊ ድርጅት ነው፤ ዓላማው በሰው ልጆች መሀከል የሚከተሉትን ተልእኮዎች መዝራት ነው፡-- 1.1. እኩልነትንና ነጻነትን 1.2. ፍቅርንና ስምምነትን 1.3. ፍትሕንና ሕጋዊነትን 1.4. ሰላምንና ማኅበረሰባዊ እድገትን 1.5. የእውነትንና የእውቀትን ብርሃን ማስፋፋትን ኢሰመጉ የተቋቋመው በሁለት ምክንያቶች ነው፤-- 2.1. የደርግ አገዛዝ ወድቆ አዲስ መንግሥት በአዲስ ሥርዓት ይመሠረታል በሚል ተስፋ አዲሱ ሥርዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እንዲመራ ለመርዳት ነበር፤ 2.2. የኢትዮጵያን ሕዝብ በመብት ጉዳይ ለማንቃትና ራሱን ከተገዢነት ወደገዢነት ደረጃ እንዲለውጥ ለማስቻል ነበር፡፡ ለትውልድ የሚተላለፍና ስምን ሲያስጠራ የሚኖር ሥራ ለመሥራት ሀብት ጥሩ መሣሪያ ነው፤ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው … [Read more...] about ኢሰመጉ ከየት ወዴት?
“… የጦር ኃይል … እና የብእር ኃይል …” ሃዲስ አለማየሁ
" ... ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን እስካለንበት ድረስ ታሪኩን መለስ ብለን ብንመለከት በሰው ዘር ላይ ግዛታቸውን ለመዘርጋት፣ ሰውን ባካልም ሆነ በመንፈስ ለመግዛት፣ ሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ሲታገሉ እናያለን፡፡ ከነዚህ አንዱ የሀይለኞች፣ ያጥቂዎች፣ የጦር ኃይል፣ ሁለተኛው የደራሲያን የብእር ኃይል ናቸው፡፡ "የጦር ኃይል በየጊዜው፣ በየቦታው የሚነሱ ኃይለኞች ሰራዊት አደራጅተው፣ የጦር መሳሪያ አከማችተው፣ ሰውን እየጨቆኑ ለግል ድሎታቸውና ፍላጎታቸው አገልጋይ የሚያደርጉበት እውር ሀይል ነው፡፡ የብእር ኃይል በየጊዜው በየቦታው የሚነሱ ታላላቅ ደራሲያን ከስው ተለይተው፣ ከብእርና ከወረቀታቸው ጋር በየቤታቸው ተዘግተው፣ ምስጢረ ፍጥረትን እየመረመሩ፣ አዳዲስ ነገር እየፈጠሩ፣ ሰውን ከድንቁርና ሰንሰለት ተፈትቶ፣ ከእንሰሳ ባህርያት ጠርቶ፣ የመንፈስና የአካል ነጻነት አግኝቶ፣ ስርአት ያለው … [Read more...] about “… የጦር ኃይል … እና የብእር ኃይል …” ሃዲስ አለማየሁ