“ቸቸላ” - በጎንደር የአማራ የልብ እሳት ማብረጃ ማማ!! ፋሲል ከነማ - ቶራ ቦራ! ማስታወሻ፤ ቶራ ቦራ አፍጋኒስታን ውስጥ ያለና ቢንላደን የሚደበቅባቸው ተራራዎችና የዋሻ ምሽጎች ናቸው። ፋሲል ከነማም የቶራ ቦራ ምሳሌ ነው። ቶራ ቦራ ብዙ ጊዜ ይደበደባል ግን ጉዳት አይደርስም። ቢደርስም ይህ ነው የሚባል አይደለም። ፋሲል ከነማም ምሽግ ነው! ቶራ ቦራ! በተቃራኒው ዱሮ ትልቅ የፖለቲካ ዋሻ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ቶራ ቦራነቱ ቀርቶ ሜዳ ሆኗል። ማንም እንደፈለገ የሚፈነጭበት ግልብ ሜዳ! ሁሉም ባይሆኑም አስገራሚና ሊፋቅ የማይችል የምስረታ ታሪክ ያላቸው ክለቦች አሉን። አሁን አዲስ አበባ ስታዲየም የሚንከላወሱት ብቻ ሳይሆኑ በመላው አገሪቱ፣ በየሰፈሩ፣ በየከተማው ... ተቋቁመው የከሰሙት ክለቦች የምስረታ ታሪክ የሚያጠናው ቢገኝ ከቅሪላው ጀርባ ያለውን ጉዳይ … [Read more...] about “ፋሲል ከነማ” – የትውልድ ዓመጽ አርማ!
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
ነጠላ ተባራይ ንፍቅ ስነ-ስሌት [ካልኩለስ በአማርኛ]
ይህ መፅሀፍ ለፊዚክስ ሂሳባዊ ዝግጅት በሚል በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ ፕረስ የታተመው የጥራዝ ፩ ተከታይ በመሆን፣ ለሳይንስ እና ምህንድስና ትምህርት ኣገልግሎት ተጨማሪ ሂሳባዊ ፅንስ-ሃሳቦችን ይሰጣል። ስለሆነም፣ በቅድሚያ ኣጭር ኣልጀብራዊ (Algebraic) እና ስነ-ዘዌያዊ (Trigonometric) ክለሳ ከሰጠ በሁዋላ፣ ስለ”ተግባር” (Function) በሰፊው ያብራራል። ቀጥሎም፣ ዋና የስነ-ስሌት መሰረት በሆነው ለከት (Limit)፣ ስነ-ቅርፅ (Geometry) እና የቀጥተኛ መስመር ዝንባሌ (Slope) በመጠቀም የ”ለውጥ ቅልጥፍና” (Rate of Change) እና ለማንኛውም የተግባር ዝብ (Curve) ዝንባሌ የሚያገለግለውን በስነ-ስሌት ድናን (Derivative) በመባል የሚታወቀውን ያብራራል። የድናን ኣጠቃቀም እና ፋይዳን በተለያዩ የትምህርት ቅርንጫፎች ያሳያል። ለዚህም፣ ከሁለት … [Read more...] about ነጠላ ተባራይ ንፍቅ ስነ-ስሌት [ካልኩለስ በአማርኛ]
የቆሻሻ ፖለቲካ ተምሳሌት – ቆሼ!! “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው”
የግፍ ክምር ናዳው ምን ያህል የሚከፋ ይሆን? አዲስ አበባ ቃላት የማይገልጹዋት፤ ስሟ ግብሯን የማይወክል የግፍ ከተማ ናት፡፡ በአንድ በኩል ሥጋ በል ለሆኑ የቤት እንሰሳዎቻቸው የዕለት ተዕለት ምግብ ከሱፐርማርኬት የታሸገ ሥጋ ገዝተው የሚመግቡ ባለጠጎች፤ በሚስታቸውና በልጆቻቸው እንዲሁም በደርዘን ውሽሞቻቸው ሥም የተንጣለሉ ቪላ ቤቶችንና ግዙፍ ህንፃዎችን የገነቡ የገዥው ኃይል ማኅበራዊ መሰረት የሆኑ የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ የከተማ ዘራፊዎች (Marauders’ city) “ወጋ ትበለይኪ” እያሉ የሚምነሸነሹባት፤ ደሃ-ገፊ መሐል አሟቂ፤ የቁስ ሰቀቀን የተጫናቸው የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ዘዋሪ ልሒቃን ከተማ ናት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዕለት ምግባቸውን ከቆሻሻ ገንዳ የሚለቅሙ አንጀታቸው በረሃብ የታጠፈ ጐስቋላ ምንዱባን በጐዳና የሚኖሩባት፤ የወር ደመወዛቸውን ለአልቦ-አንጀት (ርህራሄ የለሽ!) … [Read more...] about የቆሻሻ ፖለቲካ ተምሳሌት – ቆሼ!! “ድህነት ዋናው ጠላታችን ነው”
የማህበረሰብ ጠንቅነት ዝንባሌን እንዴት ማወቅና መጠንቀቅ እንችላለን?
ላለፉት በርካታ አመታት እኛ በውጭና በሀገር ዉስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያ ዉስጥ የተሻለ መንግሥታዊ አስተዳደር እንዲመጣና ባጠቃላይ ፍትህ እንዲሰፍን ያላሰለሰ ጥረት ስናደርግ ቆይተዋል። ይሁን አንጂ በተለያዩ ተቆጥረዉ በማያልቁ ምክንያቶች፣ አብዛኞቹ ደግሞ እራሳችን በፈጠርናቸዉ ድክመቶች እስካሁን የከፈልናቸዉ መሥዋቶች፣ ድካማችንና ልፋታችን የታለሙለትን ያህል ግብ ሊመቱና ፍሬያማ ሊሆኑ አልቻሉም። በዚህም የተነሳ ብዙዎቻችን በመሰላቸትና በምሬት ይመስላል፣ ከዋናዉ ጠላታችን ከወያኔ ጋር ከመታገል ይልቅ ምሬትና ብስጭታችንን ስርዓቱን በሚደግፉ የዉጭ ሃያላን መንግሥታትና ባመዛኙ ደግሞ ኃይላችንን እርስ በርሳችን በመነታረክ ላይ እያባከንን እንገኛለም (ተጠምደናል)። ከዚህ በፊት ስንጓዝበት ከነበረዉ የተሳሳተ ጉዞ ሳንማር አሁንም የቀድሞ ስተታችንን … [Read more...] about የማህበረሰብ ጠንቅነት ዝንባሌን እንዴት ማወቅና መጠንቀቅ እንችላለን?
የዓለም ሴቶች ማኅበርን በተመለከተ የእቴጌ መነን ቃል
ግርማዊት እቴጌ መነን ይህንን ቃል የተናገሩት ከዛሬ 80 ዓመት በፊት ሲሆን መግለጫውን ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ አውጥቶታል። (Copied from an Amharic Chrestomathy by Edward Ullendorff page 37) መረጃውን ያደረሱን Getachew Selassie; gashaselassie@gmail.com … [Read more...] about የዓለም ሴቶች ማኅበርን በተመለከተ የእቴጌ መነን ቃል
“ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!
“ … ወታደር ባለመሆኔ የጦርነቱን ውሎ ማተት አያምርብኝም፡፡ ያም ሆኖ የአድዋ ድል ዛሬ ብርቅ በሆኑብን ሁለት እሴቶች ረድኤት የተገኘ ይመስለኛል፡፡ እኒህ ሁለት እሴቶች መተባበርና መደማመጥ ናቸው፡፡ ጣልያኖቹ በጊዜው ወደ ጦርነት ሲገቡ ተስፋቸውን የጣሉት በመድፍና በጠመንጃቸው ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዝነኛ በነበሩበት የውስጥ መቆራቆስ ላይ ነው፡፡ የትግራይ ቅልጥም ሲመታ ሸዋ ያነክሳል ብለው አላሰቡም፡፡ በርግጥም በክፍለ ሀገሮች ውስጥ የተለያዩ ሽኩቻዎች ነበሩ፡፡ እኒህን ሽኩቻዎች አስረስቶ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ለአንድ አላማ ማሠለፍ ምኒልክነትን ይጠይቃል፡፡ “መደማመጥ ያልሁትን ላሳይ፡፡ አባ ዳኘው ከዛሬው የይስሙላ ፓርላማችን በተሻለ ሁኔታ ለልዩነቶች ቦታ የሚሰጥ ተንቀሳቃሽ ምክር ቤት በጦርነቱ ወቅት መፍጠር ችለዋል፡፡ ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ በውጊያው ዋዜማ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ … [Read more...] about “ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!
በአዲስ አበባ ከ45 ሺ በላይ ዕድሜያቸው ከ4-15 ዓመት የሆናቸው ህጻናት አደገኛ ሱሰኛ ሆነዋል
ሱስ አስያዥ ለሆኑ የተለያዩ ነገሮችና እፆች ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና፤ ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንድ ጥናት አሳሰበ፡፡ “ፊዩቸር ኬር” በተሰኘ ድርጅት የተሰራውና ሰሞኑን ይፋ የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው፤ በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ በርካታ ህፃናት የተለያዩ ሱሶች ተገዥ እየሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ሱሰኛ ህፃናት እስከ እብደት ሊያደርሱ በሚችሉ የአዕምሮ ጤና ችግር ሊጠቁ የሚችሉ ሲሆን ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችም የተጋለጡ ናቸው፡፡ ከሱሰኛ ህፃናቱ መካከል በተለያዩ መንገዶች ራሳቸውን የሚያጠፉ ህፃናት ቁጥርም እየተበራከተ መምጣቱን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ በተደረገው በዚሁ ጥናት መሰረት፤ በአገሪቱ ያሉ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ህፃናት እጅግ አደገኛ ለሆኑ ሱሶች ተጋልጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ከ45 ሺ በላይ ዕድሜያቸው ከ4-15 ዓመት የሆናቸው ህጻናት አደገኛ ሱሰኛ ሆነዋል
አድማሱ “ዛፍ” በቆረጠበት ጊዜ – (የዩኒቨርሲቲው ሥነ ውበታዊ ክስመት)
“እና - እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዐይኑ የታወረ፣ እግረ ኅሊናው የከረረ፤ ባሕረ ሐሳቡን ያልታደለ፣ የውበት ዐይኑ የሰለለ፣ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አይደለም አለ፡፡ ያልታደለ፤…” (“እሳት ወይ አበባ”) “እና - እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዐይኑ የታወረ፣ እግረ ኅሊናው የከረረ፤ ባሕረ ሐሳቡን ያልታደለ፣ የውበት ዐይኑ የሰለለ፣ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አይደለም አለ፡፡ ያልታደለ፤…” (“እሳት ወይ አበባ”) መግቢያ ታኅሣሥ 29 ቀን፣ 2009 ዓ.ም. በዓለ ገና፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ዕድገትና ደረጃን በሚመለከት በጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት በሚያስተምር ግለሰብ ዋና የመረጃ ሰጪነት፣ ዘጋቢ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ተላልፎ ነበር፤ የፕሮግራሙ አቀራረብም፣ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት አድማሱ ጸጋዬን … [Read more...] about አድማሱ “ዛፍ” በቆረጠበት ጊዜ – (የዩኒቨርሲቲው ሥነ ውበታዊ ክስመት)
አዲስ እንደ ቬኒስ
የማናውቀው ታሪካችን
ታሪካችንን ባለማወቃችን ሁሌም ወደኋላ በመገስገስ ላይ እንገኛለን፤ ሰሞኑን አንዳንድ ዜና መዋዕሎችን ማንበብ ጀምሬ እስካሁን አራት ያህል አንብቤአለሁ፤ ከዚህ በፊት እየተንገዳገድሁ በግዕዝ አንብቤአቸዋለሁ፤ ዛሬ የሲራክ አሳታሚ ድርጅት በአማርኛ እያሳተማቸው በመሆኑ ምስጋና ይድረሰውና ሳልንገዳገድ በአማርኛ እያነበብሁ ነው፤ በዚህ ንባቤ ውስጥ አንዳንድ ያገኘኋቸው ሀሳቦች ስለራሳችን ያለን እውቀት ምን ያህል ጎደሎ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፤ ለዛሬው ሁለት ሀሳቦችን ከላሊበላ ዜና መዋዕል፤ አንድ ደግሞ ከሱስንዮስ መርጫለሁ፤ እኔን እንዳስደነቁኝ ሌሎችንም ያስደንቃሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ አንደኛ፤ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በ1160 ዓ.ም. የነገሠው ገብረ መስቀል የሚባለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት "በነገሠ በአሥር ዓመቱ መራ ከተባለው አጠገብ የነበረውን ቤተ መንግሥት ወደሌላ ለማዛወር አስቦ … [Read more...] about የማናውቀው ታሪካችን